Telegram Web Link
꧁﷽꧂
ወንድሜ/እህቴ፡ በማንኛውም ጊዜ አላህን ስንጠይቅ በሙሉ እምነት ይሁን።
ምክንያቱም አላህ ያልጠየቅነውንም ጭምር እንዲሰጠን ነው።
እና እንዴት አላህን ጠይቀነው ሳይሰጠን ይቀራል ተብሎ ይታሰባል!እንጠይቅ..🙏

@abduljilal

@Abdu43211
ደግነት ጥንካሬ ነው። ቸር መሆን ቀላል አይደለም ፣ በተለይም እርስዎ ለሚሳደቡ ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ባለጌ መሆን ቀላል ነው ፡፡ ግን የደካማነት ምልክት ነው። ስለዚህ ጠንካራ መሆንን ይምረጡ እና በሄዱበት የደግነትና የመልካምነት ዱካ ለመተው ይሞክሩ!
______________________
አንብበን እውቀት ካገኘንበት እና ለምን የምናቀውን አናሳውቅ‼️ ስስታም አንሁን ያወቅነውን እናሳውቅ #ሼር_ያድርጉ

@abdu43211
Forwarded from ሀላል ፍቅር 2 (abdi)
ለራስዎ ደስታን ከማምጣት ምርጥ መንገዶች አንዱ በአካባቢዎ ላሉት ለሌሎች ደስታን ማምጣት ነው ፡፡ የዘፈቀደ የደግነትና የራስ ወዳድነት ድርጊቶች ረዥም መንገድ ይጓዛሉ ፡፡ ሰዎች ሁል ጊዜ ያስታውሱዎታል ፣ ይጸልዩልዎታል እንዲሁም ጀርባዎ ይኖራቸዋል ፡፡ በጣም አስፈላጊው አላህ ይወዳችኋል።
@yehaLilfeqer
​​‍ ​🌺የከነፍክላት ልጅ ለፍቅር ግንኙነት የማትፈልግህ ከሆነ...💔

🌹❶ የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር ዝግጁ እንዳልሆነች ትነግርሃለች።አንተን በፍቅረኛ ዓይን አታይህም።
ብዙ ሴቶች ያልጠበቁት ሰው ለፍቅር ጓደኝነት ሲጠይቃቸው፣ በቅድሚያ ዝግጁ አለመሆናቸውን ይገልጻሉ።
በሌላ አነጋገር “ላፈቅርህ አልችልም” ማለታቸው ነው።“ላስብበት፣ ጊዜ ስጠኝ” ካለችህ፣ የፍቅር ጥያቄ ታቀርባለህ ብላ አስባ እንደማታውቅ ያሳያል።
በጣም የምትግባቡ ጓደኞች ብትሆኑም፣ በፍቅረኛ ዓይን ላታይህ ትችላለች።

🌹ለዚህም ይሆናል የማሰብያ ጊዜ የጠየቀችህ። ስለዚህ ታስብበት። ጊዜ ስጣት። በሰጠሃት በቂ የጊዜ ገደብ ምላሽ ካላገኘህ፣ አፈግፍግ።

🌹ጥሩ ጓደኞች ልትሆኑ ትችላላችሁ፤ ፍቅረኞች ግን ልትሆኑ አትችሉም።
የጓደኝነትንና የፍቅረኝነትን ድንበር ጠንቅቀህ ማወቅ ይኖርብሃል።
“እንዴት እንደዚህ ታስባለህ? የማይሆን ነገር ነው!” ካለችህ፣ የጓደኝነትን ትርጉም
ባለመረዳትህ፣ በጓደኝነትና በፍቅረኛነት መካከል ያለውን ድንበር ባለማወቅህ ወይም አውቀህ በመጣስህ አልተደሰተችም ማለት ነው።

🌹“ጓደኛዬ” ብላ ብዙ ነገሮችን ስትነግርህ፣ ሚስጥሯን ስታካፍልህ፣ አንተ በሌላ ነገር ትተረጉመዋለህ ብላ አልነበረም።
ሴቶች ለጓደኝነት ከብዙ ነገር የበለጠ ክብርና ዋጋ ይሰጣሉ።
ፍቅረኛ መሆን ደግሞ አለመግባባት ሲፈጠር ጓደኝነትን ሊያሳጣ ይችላል።
ስለዚህ ጓደኝነት ወደ ፍቅረኝነት እንዲሸጋገር የማይፈልጉ ሴቶች አሉ።

🌹➋ ሁል ጊዜ ደዋዩ አንተ ብቻ ነህ?
እሷ ስትደውልላትም አታነሳም?

🌹 ለዚህ ምክንያት

🌹❶ ልታናግርህ አትፈልግም።

ደጋግመህ መደወልህ አሰልችቷታል
ድምፅህን መስማት አትፈልግም።

🌹➋ ትዝ አትላትም...መደወልህን ብታውቅም፣ መልሳ የደወልችልህ መስሏት ረስታሃለች።

አንድ ጊዜ ደውለህ ሳታነሳ ስትቀር መልሰህ ደውልላት።ተፈላጊነቷን ከፍ ለማድረግ አውቃ ዝም ትልህ ይሆናል።

🌹 ነገር ግን ከሁለተኛም ድወል በኋላ ካላናገረችህ፣ መልሰህ
እንዳትደውል።ከሁለት “ሚስድ ኮል”
በላይ መተው የለብህም።
እንደማትፈልግህ በግልጽ እየነገረችህ፣ ለምን ያንተን ጊዜና የሷን ትዕግስት ታቃጥላለህ? ከፈለገችህ ራሷ መልሳ ትደውላለች። ስሜትህን ተቆጣጠር።

🌹ደጋግመህ ስለደወልክላትና ትዕግስት ስላስጨረስካት የምትሸነፍልህ
ከመሰለህ ተሳስተሃል።

🌹ደጋግሞ እየደወለ ከሚያስቸግር ሰው በላይ የሚያበሳጭ ነገር የለም።
ስለዚህ ይበልጥ እንድትጠላህና እንድትሰለችህ ተጨማሪ ምክንያት አትስጣት።
በስልክ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችም አትነዝንዛት።

🌹➌ ዓይን ዓይንህን አታይም።
ከአንተ ጋር ንኪኪም አትፈጥርም። ብዙ ወንዶች ይህን ምልክት አያስተውሉትም።

🌹አንድ ሴት ከወደደችህ ዓይኖቿን ከዓይኖችህ አትነቅልም። አጠገብህም መሆን በጣም ያስደስታታል። በርግጥ አንዳንዴ ሴቶች ለሚወዱትም ወንድ ቅርብ ሆነው መገኘት አይፈልጉም።ብዙ መቀራረብ ሊያስፈራቸው ይችላል።
እንደገና ደግሞ በጣም ቀረበችኝ ዓይን ዓይኔን አየችኝ ብለህ፣ የተሳሳተ ግምት ውስጥ እንዳትገባ።

🌹አንዳንድ ሴቶች በተፈጥሯቸው ከወንድ ጋር ተቀራርበው ማውራትና መሳሳቅ ይወዳሉ።
የመዳራት ዓይነት ባህሪም ሊያሳዩ ይችላሉ።ይህ ማለት ግን ያን ወንድ በፍቅር ዓይን ያዩታል ማለት አይደለም።

🌹 ስለማትፈራህና እንደ አንድ ጓደኛ ስለምታምንህ ሊሆን ይችላል በግልጽነት እንደፈለገች የምትሆነው።

🌹ስለዚህ የተሳሳተ ግምት ወስደህ ፍቅረኛ እንድትሆንህ ከመጠየቅህ በፊት ትክክለኛ ፍላጎቷን በደንብ ለማወቅ ሞክር።እየወደደችህ ዓይን ዓይንህን የማታይህ ከሆነ ደግሞ ሲውል ሲያደር መቀየሯ አይቀርም።

🌹ዓይን ዓይንህን ባታይም፣ ባትተሻሽህም፣ ሌሎች “የእወድሃለው” ምልክቶችን በማሳየት ፍቅሯን ልትገልጽልህ ትችላለች።

🌹➍ ሌሎች ወንዶች ምን ያህል ቆንጆ እንደሆኑ ትነግርሃለች። ይህን የምታደርገው አንተን ለማስቀናት አይደለም። የድሮ ፍቅረኛህ ብቻ ነች አንተን ለማስቀናት ስለሌሎች ወንዶች
ውበት የምትናገረው።

🌹 አዲስ የተዋወቅካት ሴት ወይም ጓደኛህ ስለሌሎች ወንዶች ቆንጆነት በፊትህ የምታወራ ከሆነ አንተን በፍቅረኛ ዓይን ሳይሆን በጓደኛ ዓይን ነው የምታይህ።
ለሴት ጓደኞቿ ሐሳቧን ሳትፈራ እንደምትገልጽ ሁሉ ላንተም የተሰማትን
ታዋራሃለች—ለፍቅረኛነት ያስበኛል ብላ ስለማትጠብቅ።

🌹➎ አንተ ከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት እንድትጀምር ሁኔታዎችን ታመቻቻለች?

🌹እንደዚህ ማድረጓ

🌹❶ እላይ እንደተጠቀሰው በጓደኛነት ዓይን ነው የምታይህ። ስለዚህ ፍቅረኛሞች እንሆናለን የሚል ሐሳብ በአዕምሮዋ ውስጥ የለም።

🌹➋ ጠጋ፣ ጠጋ ማለትህ ካስፈራትና ጓደኛነታችሁን ማጣት ካልፈለገች፣ ማድረግ ያለባት አንተን ከሌላ ሴት ጋር ማስተዋወቅ ነው።

🌹በሁለቱም መንገድ ካየነው መልዕክቷ ግልፅ ነው፤ አንተን በፍቅረኛነት
አትፈልግህም።💔

@abdu43211🍂👀
​​🍃🌹🍃....

♥️. . .ፍቅር መስጠት ብቻ ሲሆን ያማል
ይመስለኛል የኛ ህመም ሰው ይቀይራል
የጠነከሩትን ያደክማል ቢሆንም በናት እና በፍቅር ተስፋ አይቆረጥም!!❤️
🌺♥️🌺♥️🌺♥️🌺♥️🌺♥️🌺♥️🌺♥️

@abdu43211🍃👀
Forwarded from 💐🕍 አብዲ ቲዩብ๑ 💐۞๑๑۩ 💐 🕌abdi Tube ๑ 💐 (عبد الجلال منصور محمد)
በሚያዩት ላይ በመመርኮዝ የራስዎን መደምደሚያ ማዘጋጀት ቀላል ነው ፡፡ አታድርግ ፡፡ ያንን ፈተና ተቋቁሙ። ለምን? ምክንያቱም በአንድ ሰው ጫማ ውስጥ ካልተመላለሱ ትክክለኛውን ሁኔታ በጭራሽ አያውቁም። ያስታውሱ ፣ አላዋቂዎች የሚያዩት በዓይኖቹ ብቻ ነው ፡፡ በልብዎ እና በአዕምሮዎ ማየት ይማሩ!
______________________
አንብበን እውቀት ካገኘንበት እና ለምን የምናቀውን አናሳውቅ‼️ ስስታም አንሁን ያወቅነውን እናሳውቅ
ለ 10 ሰው #ሼር_ያድርጉ

@abdu4321🍃👀
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال منصور محمد)
በዚህ ረመዳን መጾም መቻላቺን እንዴት እንደተባረክን ያሳያል ፡፡ ያለፈው ዓመት ከሞላ ጎደል ከወደቀበት ሁኔታ ጋር እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ ፣ ስንት ሰዎች ሞተዋል ሆኖም ግን አሁንም አላህ ጠብቆናል እናም በዚህ የተባረከ ወር እንድንደርስ እና እንድንጾም ፈቀደልን ፡፡

አልሀምዱሊላህ።
__________________
አንብበን እውቀት ካገኘንበት እና ለምን የምናቀውን አናሳውቅ‼️ ስስታም አንሁን ያወቅነውን እናሳውቅ
ለ 10 ሰው #ሼር_ያድርጉ


@hebre_muslim🍃👀
Forwarded from 💐🕍 አብዲ ቲዩብ๑ 💐۞๑๑۩ 💐 🕌abdi Tube ๑ 💐 (عبد الجلال منصور محمد)
Surah Al-Insan (الدَّهْرِ), verses: १

هَلْ أَتَىٰ عَلَى ٱلْإِنسَٰنِ حِينٌ مِّنَ ٱلدَّهْرِ لَمْ يَكُن شَيْـًٔا مَّذْكُورًا

በሰው ላይ የሚታወስ ነገር ሳይኾን ከዘመናት የተወሰነ ጊዜ በእርግጥ አልፎበታል፡፡
verses: २

إِنَّا خَلَقْنَا ٱلْإِنسَٰنَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَٰهُ سَمِيعًۢا بَصِيرًا

እኛ ሰውን (በሕግ ግዳጅ) የምንሞከረው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው፡፡ ሰሚ ተመልካችም አደረግነው፡፡
verses: ३

إِنَّا هَدَيْنَٰهُ ٱلسَّبِيلَ إِمَّا شَاكِرًا وَإِمَّا كَفُورًا

እኛ ወይ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ ሲኾን መንገዱን መራነው፤ (ገለጽንለት)፡፡

@abdu4321👀🍃
Forwarded from 💐🕍 አብዲ ቲዩብ๑ 💐۞๑๑۩ 💐 🕌abdi Tube ๑ 💐 (عبد الجلال مانو محمد)
የፍጥረታት ሁሉ ነፍስ በእጅህ የሆነች ቀኗ ስትደርስ የምትወስድ <አል ቃቢድ> ሆይ! ሩሀችን ተወስዳ መቃብር የገባን ቀን እዘንልን በህይወታችን ነፍስ የምትዘራ ሲሳይን የምትዘረጋ <አል ባሲጥ>ሆይ! ኑሯችንን አታጥብብን ሀያታችንን የጭንቅ አታድርግብን የፈለግከውን ዝቅ የምታደርግ<አል ኻፊድ> ስትሻ ደግሞ ከፍ አድርገህ የምታስቀምጥ <አር ራፊዕ> ከአንተ ውጭ ማንም የለምና ከዘቀጥንበት አውጣን ከወደቅንበት አንሳን የተዋረደን ለክብር የምታበቃ <አል ሙዒዝ> የተከበረን የምታዋርድ <አል ሙዚል> ነህና ከተከበርን በኀላ አታዋርደን ነውራችንን ገልጠህ መሳቂያ መሳለቂያ አታድርገን🤲🤲

💛 @yesunasetoche

ዱአችን መቅቡል የሚሆንበት ለሊት ይሁንልን !!!

🌴መልካም አዳር ይሁንላችሁ🌴

@hebre_muslim
@Abdu4321
@abdu43211
Forwarded from 💐🕍 አብዲ ቲዩብ๑ 💐۞๑๑۩ 💐 🕌abdi Tube ๑ 💐 (عبد الجلال مانو محمد)
አጂጂጂብ

ልቦና ያለውን ሰው ሁሉ የምታስለቅስ
ቆንጆ ታሪክ


ከረሱል (ሰዐወ) የህይወት ማህደር!
መነበብ እና ለሌሎች መተላለፍ የሚገባው !
ነብዩ (ሰዐወ) ጠዋፍ እያደረጉ ሳለ አንድ
ዓእራብይ /የአረብ ገጠሬ/ …‘ያ ከሪም!’ /ቸሩ
ፈጣሪ ሆይ እንደማለት/… እያለ ሲጣራ
ሰሙት። እርሳቸውም ከኋላው ሆነው …’ያ
ከሪም!’… አሉ። ዓእራብዩም አቅጣጫ
በመቀየር …’ያ ከሪም!’… እያለ መጣራቱን
ቀጠለ ነብዩም (ሰዐወ) ከኋላው ተከትለው
…’ያ ከሪም!’… አሉ።
ዓእራብዩም ፊቱን ወደ እርሳቸው በማዞር:-

“አንተ ባለግርማ እና በሻሻ ፊት ሆይ!…
ዓእራብይ ስለሆንኩ ነው የምታሾፍብኝ?…
በአላህ እምላለሁ! የፊትህ ሞገስ እና በሻሻነት
ባልነበረ ወዳጄ ሙሐመድ (ሰዐወ) ዘንድ
ወስጄ እከስህ ነበር!” አላቸው።
ነብዩም (ሰዐወ) ፈገግ ብለው:- “አንተ አረብ
ወንድሜ ሆይ! ነብይህን አታውቀውም ማለት
ነው?” አሉት
ዓእራብዩም “አዎን!” ሲል መለሰላቸው።
“ለመሆኑ በእርሱ ላይ ያለህ እምነት
ምንድነው?” ሲሉ ጠየቁት
ዓእራብዩም:- “በነብይነቱ አመንኩኝ! አይቼው
ግን አላውቅም፣ ረሱልነቱን ተቀበልኩኝ!
አግኝቼው ግን አላውቅም።” ሲል
መለሰላቸው።
ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ ዓእራብይ ሆይ!
የዱንያው ነብይህ እና የአሄራ አማላጅህ እኔ
መሆኔን እወቅ!” አሉት።

ዓእራብዩም የነብዩን(ሰዐወ) እጅ በፍጥነት
መሳም ያዘ
ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ አረብ ወንድሜ
ሆይ! ሌሎች ህዝቦች ንጉሶቻቸውን
እንደሚያደርጓቸው አታድርገኝ፤ አላህ (ሱወ)
ኩራተኛ እና አጉራዘለል አድርጎ አላከኝም፤
ይልቁንም አብሳሪ እና አስጠንቃቂ አድርጎ
በእውነት ልኮኛል።” አሉት
በዚህን ጊዜ ...

ጅብሪል ወደ ነብዩ መጣና:- “ሙሐመድ
ሆይ አላህ (ሱወ) ሰላምታን ያቀርብልሀል!
በክብር እና ልቅናም ከሌሎች አስበልጦሀል፤
ለዚህ ለዓእራብይ:- የአላህ ቸርነት እና ቻይነት
እንዳያዘናጋው!፣ ነገ በትንሹም ይሁን በትልቁ፣
በልምጩ ይሁን በቅሉ እንደሚተሳሰበው
ንገረው”… አላቸው።

ዓእራብዩም:- “አንቱ የአላህ መልእክተኛ
(ሰዐወ) ሆይ! ጌታዬ ይተሳሰበኛል ማለት
ነው?” ብሎ ጠየቃቸው

“አዎን ከፈለገ ይተሳሰብሀል!” አሉት

“እንግዲያውስ በአሸናፊነቱ እና በልቅናው
ይሁንብኝ! የሚተሳሰበኝ ከሆነ እኔም
እተሳሰበዋለሁ!” አለ።

ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ አረብ ወንድሜ
ሆይ! ጌታህን በምን ትተሳሰበዋለህ?” አሉት።
“ጌታዬ በወንጀሌ ከተሳሰበኝ እኔ በምሕረቱ
እተሳሰበዋለሁ፣ በጥፋቴ ከተሳሰበኝ እኔ በይቅር
ባይነቱ እተሳሰበዋለሁ፣ በስስታምነቴ
ከተሳሰበኝ እኔ በቸርነቱ እተሳሰበዋለሁ!”…
አለ።

ነብዩ (ሰዐወ) ፂማቸው እስኪረጥብ ድረስ
አለቀሱ።
ጅብሪል ወደ ነብዩ ወርዶ:- “ሙሐመድ ሆይ!
አላህ ሰላምታን ያቀርብልሀል። ለቅሶህንም
ቀንስ! የአርሽ ተሸካሚ መላኢካዎችን ተስቢህ
ከማድረግ አዘግይታቸዋለችና ይልሀል።

ለዓእራብዩ ወንድምህ ደግሞ:- እንዳይተሳሰበን
ንገረው! እኛም አንተሳሰበውም! እርሱ የጀነት
ጎረቤትህ ነው!።”… አላቸው።
አላህ በታላቋ ጀነተል ፊርደውስ ውስጥ
የነብዩን (ሰዐወ) ጉርብትና ከሚያገኙት
እንዲያደርገን እንለምነዋለን።

ያ አላህ ይህንን መልእክት አንብበው
ለሚያስተላልፉ ሁሉ ከነቤተሰቦቻቸው
ምሕረትህን ለግስ መመንዳትንም
አትንፈጋቸው …ያ ከሪም!።

ከአላህ ውጭ በእውነት የሚመለክ አምላክ
የለም! ሀይልም ሆነ ብልሀት በርሱ ቢሆን
እንጂ አይገኝም!።

‘አላሁመ ሰሊ አላ ሙሐመድ ወ አላ አሊ
ሙሐመድ’ …ጌታዬ ሆይ ምሕረትህን
እለምንሀለሁ ወዳንተም ንሰሀ እገባለሁ!።
ከመካከላችን ሰደቀተል ጃሪያን የሚፈልግ
ማነው? ከሞትን በኋላ እንኳ በቀብራችን
ውስጥ ሆንነን አጅር የምንቋደስበትን!።
እንግዲያውስ ይህንን መልካም ስራ በነፍሳችን
ላይ አናስመልጥ!
}} በነብዩ (ሰዐወ) ላይ አስር ሶላዋትን
እናውርድ ለአስር ሰዎችም መልእክቱን
እናስተላልፍ የቂያም ለት በሚዛናችን ላይ
ሚሊየን ሰላዋት ሆኖ እናገኘዋለን

@abdu4321🍃👀🍃
ጥሩ ህይወት ለመምራት
የሚረዱ መርህዎች
○ ሰውን አትጥላ ፤ ልብህን ኑፁህ አድርግ
○ አትጨነቅ ፤በአላህ ተመካ
○ ቀለል ያለ ኑሮ ኑር
○ ባለህ ነገር ተደሰት ፤በተሰጠህ ነገር አመስጋኝ ሁን
○ አላህን በብዛት አስታውስ፤ልብህ እርጋታን ታገኛለች
○ ፈገግታን አብዛ
○ በፍቅር ኑር ፤ለአላህ ብለህ ውደድ
○ እውቀትህን ለሌሎች አካፍል ፤ አንድም የቁርሀን አንቀፅ እንካን ቢሆን
○ ዱዓን አብዛ ፤ በረካን እንድታገኝ

@abdu43211
Forwarded from 💐🕍 አብዲ ቲዩብ๑ 💐۞๑๑۩ 💐 🕌abdi Tube ๑ 💐 (عبد الجلال مانو محمد)

"ብዙ ሰዎች ስኬት ማለት ገንዘብ ይመስላቸዋል ግን ስኬት ማለት ውስጥ ሰላም ሲሆን ቀልብህ ሰላም ሲሆን ነው። ይህን ደግሞ ልታገኘው የምትችለው በእስልምና ነው!!!"

@abdu4321
አላህ ለይለተል ቀድርን ይወፍቀን

አሚን🙌
Forwarded from 💐🕍 አብዲ ቲዩብ๑ 💐۞๑๑۩ 💐 🕌abdi Tube ๑ 💐 (عبد الجلال مانو محمد)
ዶ/ር ዛኪርን በተመለከተ ኢንተርፖል ለአራተኛ ጊዜ በህንድ መንግስት የቀረበለትን የክስ ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

@abdu4321

"ብቸኝነት በተሰማህ ሰዓት አንድ ነገር አስተውል። አላህ ሁሉንም ሰው ከአጠገብህ አርቆ ለአንተ እና ለሱ ጊዜ መስጠቱ ነውና ሰዓት ለዱዓ ተጠቀምበት።"

👀🍃 @abdu43211👀🍃
2024/09/23 19:27:44
Back to Top
HTML Embed Code: