Telegram Web Link
አሠላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ
ነገ የረመዳን ዋዜማ የሻዕባን ማሟያ ነው!

በሁሉም የሳውዲ አካባቢዎች ጨረቃ አልታየችም። ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንዳደረሱን በተሚዝ አካባቢ ያለው የጨረቃ መጠባበቂያ ማእከል ውጤት ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን ሆኖም ጨረቃ አልታየችም። በመሆኑም ነገ ሰኞ ሚያዝያ 4/2013 የረመዳን ዋዜማ የሻዕባን የመጨረሻ ቀን ይሆናል። ማክሰኞ ረመዳን 1 ይሆናል። ከሳውዲ ከፍተኛ ፍርድቤት ይፋ መግለጫ በመጠበቅ ላይ ነው።
አብዲ ቲዩብ መላውን ሙስሊም ማህበረሰብ እንኳን በሰላም አደረሳችሁ እያለ አላህ ተውበትና መልካም ስራን እንዲያገራልን እንለምነዋለን። ረመዳን ሙባረክ!!


@abduljilal
በረመዳን ቁርኣንን ለማክተም‼️
========================
1) አንድ ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~~~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 4 ገጽ መቅራት፣

2) ሁለት ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~~~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 8 ገጽ መቅራት፣

3) ሶስት ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~~~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 12 ገጽ መቅራት፣

4) አራት ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~~~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ ገጽ 16 መቅራት፣

5) አምስት ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~~~~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 20 ገጽ መቅራት!!
||


ረመዳን የቁርኣን ወር ነው።
ከአምስት ግዜ በላይ ብናከትምም በጣም ተወዳጅ ነው።

ምናልባት ይህ ፕሮግራማችን አንድ ቀን ወይም በሆነ ሰአት ላይ በተለያዬ ምክንያት ቢያልፈን፣
ከሌላኛው ቀን ወይም ግዜ ማካካስ መቻል አለብን።

አላህ ያግዘን።

@abduljilal
«ሰሑርን» በተመለከተ ጥቂት ጥቆማዎች‼️
===============================
✍️ ሰሑር ማለት በጾም ወቅት ትክክለኛው ጎህ ከመውጣቱ በስተፊት በሌሊቱ ክፍለ ግዜ ወደ ፈጅር አቅራቢያ የሚበላ ምግብ ነው።
ሰሑር ሱንና ነው። የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተግብረውታል።
1️⃣ጥቅል ነጥቦች፥
````

✔️ አነስ ኢብኑ ማሊክ ረዲየልሏሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል፥
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦
«تسحروا فإن في السحور بركة!»
"ሰሑርን ተመገቡ፣ ሰሑር በመመገብ ውስጥ በረከት አለ።"

[ቡኻሪ፥ 1921
ሙስሊም፥ 1095]
✔️ በሌላ ሐዲሥም ከዐምር ኢብኒል ዓስ በተገኘ ዘገባ ላይ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፥
«فصل ما بين صيامنا وصيام أهل الكتاب أكلة السحر!»
"በኛ ጾምና በኪታብ ባለቤቶች ጾም መካከል ያለው ልዩነት፤ ሰሑርን መመገብ ነው።"

[ሙስሊም: 1096]
እኛ ስንጾም ሰሑር እንመገባለን፣ አህለል ኪታቦች (የሁዳዎችና ነሷራዎች) ግን አይመገቡም።
✔️ አነስ ረዲየልሏሁ ዐንሁ ዘይድ ኢብኑ ሣቢት ረዲየልሏሁ ዐንሁ እንዲህ እንዳለ አስተላልፈዋል፥
«تَسَحَّرْنَا مَعَ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ثُمَّ قَامَ إِلَى الصَّلاةِ قُلْتُ كَمْ كَانَ بَيْنَ الأَذَانِ وَالسَّحُورِ قَالَ قَدْرُ خَمْسِينَ آيَةً!»
«ከነብዩ ﷺ ጋር ሰሑር ተመገብን። ከዚያም ወደ ሶላት ቆሙ!" አለ።
"በአዛንና በሰሑር መካከል ያለው ግዜ ስንት ይሆናል?" አልኩት! (አነስ ለዘይድ ነው የሚጠይቀው!)
(ዘይድም) ሃምሳ አንቀጽ (የሚያስቀራ ግዜ) ያክል! (ብሎ መለሰለት)»
[ቡኻሪ፥ 1821]
ይህ የሚያሳየው ሰሑርን ወደ ፈጅር ማዘግየቱ የሚወደድ መሆኑን ነው።
✔️ ዐብዱልሏህ ኢብኑል ሐሪሥ ረዲየልሏሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል፥
"ከነብዩ ﷺ ባልደረቦች መካከል አንዱ እንዲህ አለ፦
መልዕክተኛው ﷺ ሰሑር እየተመገቡ ሳለ ገብቼ ፥

«إنها بركة أعطاكم الله إياها؛ فلا تدعوه»
"እርሷ (ሰሑር) በረካ ናት (አለባት)። እርሷን አላህ ሰጥቷችኋል፣ እንዳትተውት።" አሉኝ አለ።

[ነሳኢይ ዘግበውታል።]
✔️ ሰልማነል ፋሪስ ረዲየልሏሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል፥
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦
«البركة في ثلاثة: في الجماعة، والثريد، والسَّحور»
"በሶስት ነገሮች ውስጥ በረካ አለ፥ በጀመዓ፣ በሠርድ (የምግብ አይነት [ስጋና ዳቦ ቅይጥ])፣ በሰሑር።"

[ጦበራኒይ ዘግበውታል።]
✔️ አቢ ሰዒዲኒል ኹድሪይ ረዲየልሏሁ ዐንሱ ባስተላለፉት ሐዲሥ ላይ ደግሞ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦
«السَّحور بركة؛ فلا تدعوه..!»
"ሰሑር በረካ ነው፣ እንዳትተውት።"
[አሕመድ ዘግበውታል።]
እንዲህም ብለዋል፥
«إن الله وملائكتة يصلون على المتسحّرين»
"አላህና መላእክቱ በሰሑር ተመጋቢዎች ላይ አክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ!" ]
[አሕመድ ዘግበውታል።]
*
2️⃣ሰሑርን ማዘግየት ይወደዳል!!
````````````````````

ሰሑር ያልተመገበ ሰው ጾሙ ትክክል ነው አይበላሽም፣ ግን ሱንናው አምልጦታል።
✔️ ስለዚህ ጉዳይ አቡበከር ኺሷስ "አሕካሙል ቁርኣን፥ 1/265" ላይ አስፍረዋል።
*
«فالسنة السحور، ولكن ليس بواجب، من لم يتسحر فلا إثم عليه، لكن ترك السنة، فينبغي أن يتسحر ولو بقليل، ليس من اللازم أن يكون كثيراً، يتسحر بما تيسر ولو تمرات أو ما تيسر من أنواع الطعام في آخر الليل»
"ሱንናው ሰሑር መመገብ ነው። ነገር ግን ግደታ አይደለም። ሰሑር ያልተመገበ በርሱ ላይ ወንጀል የለበትም። ነገር ግን ሱንናን ትቷል። በትንሽ ነገርም ቢሆን ሰሑር ሊመገብ ይገባል። ብዙ መሆኑ ግድ የሚል አይደለም። በሌሊቱ መጨረሻ ላይ በገራለት ነገር በተምሮችም ሆነ በገራለት የምግብ አይነት ሰሑር ሊመገብ ይገባል።..."

[ኢብኑ ባዝ፥ ኑሩን ዓለ ደርብ]"
✔️ እናታችን ዓኢሻእ ረዲየልሏሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች፥
«عَنْ عَائِشَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا أَنَّ بِلالا كَانَ يُؤَذِّنُ بِلَيْلٍ ، فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : ( كُلُوا وَاشْرَبُوا حَتَّى يُؤَذِّنَ ابْنُ أُمِّ مَكْتُومٍ ، فَإِنَّهُ لا يُؤَذِّنُ حَتَّى يَطْلُعَ الْفَجْرُ ) »
"ቢላል በሌሊት አዛን ያደርግ ነበር። ረሱልሏህ ﷺ እንዲህ አሉ፥ «ኢብኑ መክቱም (ዐብዱልሏህ) አዛን እስከሚል ድረስ ብሉ፣ ጠጡ፤ እርሱ ፈጅር ሳይወጣ አዛን አይልም።»"

[ቡኻሪ፥ 1919
ሙስሊም፥ 1092"
✔️ ኢማመ ነወዊይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፥
«اتَّفَقَ أَصْحَابُنَا وَغَيْرُهُمْ مِنْ الْعُلَمَاءِ عَلَى أَنَّ السَّحُورَ سُنَّةٌ , وَأَنَّ تَأْخِيرَهُ أَفْضَلُ ، وَدَلِيلُ ذَلِكَ كُلُّهُ الأَحَادِيثُ الصَّحِيحَةُ , وَلأَنَّ فِيهِمَا (يعني السحور وتأخيره) إعَانَةً عَلَى الصَّوْمِ , وَلأَنَّ فِيهِمَا مُخَالَفَةً لِلْكُفَّارِ...»
"ሰሑር ሱንና መሆኑንና እርሱን ማዘግየቱም በላጭ መሆኑን የኛ ባልደረቦቻችን (ሻፊዒይያዎች) እና ከዑለማዎች ሌሎችም ተስማምተዋል።
ይህንንም ሁሉም ትክክለኛ ሐዲሦች ያመላክታሉ።
በነርሱም ውስጥ (ሰሑር በመገብና በማዘግየቱ) ለጾሙ ይረዳል፣ በነርሱም ውስጥ ከሃዲያንን መቃረን አለበት።..."
[አል-መጅሙዕ፥ 6/406]
✔️ ለጂነቲ ዳኢማም ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቃ፣ በ10/284 ላይ ተመሳሳይ ይዘት ያለው መልስ አስፍራለች።

ሸይኽ ኢብኑ ባዝም ተጠይቀው የመለሱት በመጅሙዐቱል ፈታዋ ኢብኑ ባዝ፥ 15/281 ላይ ይገኛል።
*
ጽሁፉ እንዳይረዝም ነው።
ዐብዱልሏህ ኢብኑ ጀብሪንም ተጠይቀው የመለሱት አለ።

@abduljilal

@abdu43211
#የፃም_ህግጋት

#ክፍል_አንድ

📢መግቢያ📢

بسم الله الرحمٰن الرحيم
الحمد لله والصلاة والسلام على
رسول الله

የረመዷን ወር ፆም ታላቅ ዒባዳ (አምልኮ) ከመሆኑም ባሻገር አሏህ በልዩ ልዩ ነገሮች ልዩ አድርጎታል።

ከነዚህም ውስጥ አሏህ በሀዲስ አልቁድስይ እንዲህ ብሏል

"كل حسنة بعشر أمثالها إلى سبعمائة ضعف إلا الصوم فإنه لي وأنا أجزى به
رواه البخاري
#ትርጉም "ሁሉም ጥሩ ስራወች ከአስር እጥፍ እስከ ሰባት መቶ እጥፍ ይባዛሉ ፃም ሲቀር፣ ፃም ለእኔ ነው፣ ምንዳውን የምሰጠው እኔ ነኝ" ቡኻሪይ ዘግበውታል።


የረመዷንን ወር መፆም ግዴታ የሆነው በሂጅራ አቆጣጠር #በሁለተኛው_አመት ላይ ነው። ነብያችን ﷺ ዘጠኝ ረመዷኖችን ፁመው ነበር የሞቱት።

የረመዷንን ወር መፆም ግዴታ መሆኑን ዓሊሙም ጃሂሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው።

በመሆኑም ግዴታነቱን ያስተባበለ(የካደ) ለእስልም አዲስ ወይም ዑለማወች ከሚገኙበት ቦታ ርቆ ያደገ ካልሆነ በቀር ግልፅ የሆነን ቁርአን እንዲሁም የተረጋገጠን ሀዲስ መቃወም ስለሆነ መንገድ ያስታል።

ነገር ግን ግዴታ መሆኑን እያመነ ያለ ምንም ምክንያት ያፈጠረ ሀጢያተኛ ይሆናል እንጂ ከ እስልምና አይወጣም። ያፈጠራቸውንም ቀናት ቀዷእ ማውጣት ግዴታ ይሆንበታል።

የረመዷን ወር ፃም ግዴታ ለመሆኑ #የቁርአን_ማስረጃ

قال الله تعالى【 كتب عليكم الصيام】 البقرة 183
#ትርጉም: (በእናንተ ላይ ፆምን ግዴታ አድርጎባችኃል)

#ነብዩም_ﷺ እንዲህ ብለዋል

بني الإسلام على خمس شهادة أن لا إلٰه إلا الله وأن محمد رسول الله وإقام الصلاة وإيتاء الزكاة وحج البيت وصوم رمضان
رواه البخازي ومسلم

#ትርጉም "እስልምና የተገነባው በአምስት ነገሮች ነው(ማለትም እስልምናችን ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ነገራቶች አምስት ናቸው)።((እነሱም)) ከአሏህ በስተቀር በሀቅ የሚገዙት እንደሌለና ነብዩ ሙሀመድ ሶለ ሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን መመስከር ፣ ሶላት(በአግባቡ ጊዜያቸውን ጠብቆ) መስገድ ፣ዘካት(ምፅዋት) ማውጣት፣ ሀጅ ማድረግና የረመዷንን ወር መፃም ((ናቸው))" ቡኻሪይ ዘግበውታል ።

የረመዷንን ጨረቃ በ29 ነኛው የሻዕባን ወር ማታ ላይ መከታተሉ ግዴታነው (በፈርዱል ኪፋያ)መልክ ።

ምክንያቱም ወሩን መፆም መጀመር ግዴታ የሚሆነው ከሁለት ነገሮች አንዱ ከተከሰተ ነው ።
እነሱም⇩⇩
➊☞በ29 ኛው የሻዕባን ወር ማታ ላይ የረመዷን
ጨረቃ ከታየች

አልያም

☞የሻዕባን ወር 30 በመሙላቱ

#ምክንያቱም ሰይዳችን ﷺ እንዲህ ስላሉ

صوموا لرؤيته وأفطروا لرؤيته فإن غم عليكم فأكملوا عدة شعبان ثلاثين يوما
رواه البخاري ومسلم

#ትርጉም " ጨረቃን ያያቹህ እንደሆነ (በ29 ኛው የሻዕባን ወር ማታ ላይ) ፁሙ፣ ጨረቃን ያያቹህ እንደሆነም (በ29 ኛው የረመዷን ወር ማታ ላይ) አፍጥሩ ( ረመዷን አልቋል) ፣ ደመና ከሆነባቹህ (ጨረቃ ካልታያቹህ) የሸዕባንን ወር 30 ሙሉ።"
ቡኻሪይ እና ሙስሊም ዘግበውታል።

#ክፍል_ሁለት_ይቀጥላል ......

➥⇩⇩ሸር ማረግ እንዳይረሱ!!
ኢስላማዊ ሀዲሶችን ትኩስ ትኩሱን ያገኛሉ አላማችን ኡማውን ማገልገል ነው ለጓደኛዎ ሼር ያድር አንዲትም ቃል ብትሆን ከኔ የሰማቹትን ለሌሎች አስተላልፋ ብለዋል ረሱል ሰ ዐ ወ 👇👇👇👇👇
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Abduljilal
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Abdu43211

🌐💚💛❤️
----🌺🌺🌺--------
--------🌺🌺🌺-------
-------------🌺🌺🌺------

➠ክፍል ❶

➢የጾም ምንነት

➯ሲያም(ጾም) ማለት በአረብኛ ቋንቋ አገላለፅ ከአንድ ነገር መታቀብ ማለት ነው ፤ በሼሪአ ወይም በእስልምና ሕግ ፣ ከመጠጣት ፣ከወሲብ ግንኙነት እንዲሁም ሊያስፈጥሩ ከሚችሉ ማናቸው ነገሮች ጎህ ከተቀደደበት ማለትም ከንጋት ጀምሮ ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ መታቀብ ማለት ነው።

በቀጣይ ጊዜ ❷ ክፍል ይቀጥላል.........

-----🌸🌸🌸-------
---------🌸🌸🌸-----
--------------🌸🌸🌸------

@abduljilal
------🌺🌺🌺--------
----------🌺🌺🌺-------
---------------🌺🌺🌺-----

➠ክፍል ❷

➢የጾም ታሪካዊ አመጣጥ

➯የረመዷን ጾም አላህ (ሱ.ወ) በነብዩ ሙሐመድ ላይ #ﷺ ላይ ግዴታ ያደረገው እለተ ሰኞ በሻዕባን ወር በአረብኛው ወር አቆጣጠር ከሂጂሪያ ወይም ከስደት በሁለተኛው አመት ላይ ነበር ፤ ሲደነገግም በሱረቱል- በቀራ አንቀጽ (183- 185) እንዲህ ተብሎ ነበር የተደነገገው።

《يَا أَيُّهَاالَّذِينَ ءامَنُوا کُتِبَ عَلَيکُمُ الصِيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ<<١٨٣>>أَيَّامًا مَعْدُودَاتٍ فَمَنْ كَانَ مِنْكُمْ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِنْ أَيَّامٍ أُخَرَ وَعَلَى الَّذِينَ يُطِيقُونَهُ فِدْيَةٌ طَعَامُ مِسْكِينٍ فَمَنْ تَطَوَّعَ خَيْرًا فَهُوَ خَيْرٌ لَهُ وَأَنْ تَصُومُوا خَيْرٌ لَكُمْ إِنْ كُنْتُمْ تَعْلَمُونَ<<١٨٤>> شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنْزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ فَمَنْ شَهِدَ مِنْكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ وَمَنْ كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِنْ أَيَّامٍ أُخَرَ يُرِيدُ اللَّهُ بِكُمُ الْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ الْعُسْرَ وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ<<١٨٥>>


➥"እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ሕዝቦች ላይ እንደተፃፈ ሀሉ በእናንተም ላይ ተፃፈ (ተደነገገ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና " (183) "የተቆጠሩን ቀኖች ጽሙ ከእናነተም ውስጥ በሺተኛ ወይም በጉዞ ላይ የሆነ ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን መጾም አለበት በነዚያም ጾምን በማይችሉት ላይ ቤዛ ድሀን ማብላት አለባቸው (ቤዛ ለመጨመር) መልካምንም ሥራ የፈቀደ ሰው እርሱ (ፈቅዶ መጨመሩ) ለርሱ በላጭ ነው። መጾማችሁም ለናንተ የበለጠ ነው።የምታውቁ ብትሆኑ ትመርጧታላችሁ "(184) "(እንድትጾሙ የተፃፈባችሁን) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድ እና (እውነትን ከውሸት) ገላጮች (አንቀጾች) ሲሆን ቁርዕን የተወረደበትሽ ወር ነው ፤ ከእናንተ ወሩን የገኘ ሰው ይጥመው ፤ በሺተኛ ወይም በጉዞ ላይ የሆነን ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን መጾም አለበት ፤ አላህ በናንተ ጥሩን (ነገር) ይሻል ፤ በናንተ ችግሩን አይሻም ፤ ቁጥሮችንም ልትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ታከብሩት እና ታመሰግኑት ዘንድ (ይህንን ደነገግንላችሁ)" *ሱረቱል በቀራ 183- 185)

በቀጣይ ጊዜ ➌ክፍል
ይቀጥላል......

------🌸🌸🌸------
----------🌸🌸🌸-------
----------------🌸🌸🌸-----

@abduljilal
-----🌺🌺🌺--------
--------🌺🌺🌺-------
-------------🌺🌺🌺-----

➠ክፍል ➌

➢የጾም ለመጀመር የማረጋገጭ
ምልክቶች

➯የረመዳን ወር መግባቱ የሚታወቀው በሁለት ምልክቶች ሲሆኑ አንደኛው ከረመዳን ወር በፊት የነበረው ወር ማለትም ሻዕባን 30 ቀን በሚሞላበት ነው። ከሻዕባን 30ኛውን ቀን ቀጥሎ ያለው ቀን ከረመዷን ወር የመጀመሪያው ቀን ማለት ነው። ሁለተኛው የሻዕባን ወር 30ኛ ቀን ላይ የረመዷን ወር ጨረቃ ስትታይ ነው። የረመዷን ወር ጨረቃ በታየ በንጋታው የረመዷን ጾም መጀመር ግዴታ ይሆናል። ይህንን አስመልክቶ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ "ፆም የረመዷን ጨረቃ ስታዩ ጀምሩ የሸዋልን ጨረቃ ስታዩ ፍቱ ደመና ሁኖ ጨረቃን ማየት ካልቻላችሁ 30 ቀን መሙላቱን አረጋግጡ"።(ሙስሊም ዘግቦታል)

➬የረመዷን ወር ጨረቃ መታየቱ በአንድ ታማኝ ሙስሊም ምስክርነት ሊረጋገጥ ይችላል ፤ ማለትም ታማኝ ሙስሊም ጨረቃን አይቻለሁ ብሎ ከመሰከረ በአካባቢው የሚገኙ ሙስሊሞች ጾምን መጀመር ግዴታ ይኖርባቸውል። በዚህ መልክ ረመዷንን መፍታት ግን አይቻልም ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ ﷺ ረመዷን ለመጀመር በአንድ ታማኝ ሙስሊም ምስክርነት ሲያፀድቁት በፍቺው ላይ ከሁለት ሰዎች በሁለት በታት ስላላፀደቁ ነው።

ክፍል 4⃣ ይቀጥላል

-----🌸🌸🌸------
---------🌸🌸🌸-----
-------------🌸🌸🌸-----


@abduljilal
-----🌺🌺🌺-------
--------🌺🌺🌺--------
-------------🌺🌺🌺------

➠ክፍል ➍

➢የጾም ትሩፋቶች

➯እንደሚታወቀው የረመዷን ጾም ከአምልኮ ዘርፎች አንዱ ሲሆን ሙስሊሞች ፊታቸውን ወደ አላህ እንዲያዞሩ በመጾም ወደ አላህ እንዲቃረቡ የጾምን ጥቅሞች እና ቱርፋቶች የሚገልፅ እንዲሁም ሙስሊሞችን ለአምልኮሽ የሚያነሳሳ በርካታ የቁርአን አንቀጾች አሉ። ከነዚህም መካከል በሱረቱል አቅዛብ ላይ አንቀጽ 35 አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል።

إِنَّ الْمُسْلِمِينَ وَالْمُسْلِمَاتِ وَالْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ وَالْقَانِتِينَ وَالْقَانِتَاتِ وَالصَّادِقِينَ وَالصَّادِقَاتِ وَالصَّابِرِينَ وَالصَّابِرَاتِ وَالْخَاشِعِينَ وَالْخَاشِعَاتِ وَالْمُتَصَدِّقِينَ وَالْمُتَصَدِّقَاتِ وَالصَّائِمِينَ وَالصَّائِمَاتِ وَالْحَافِظِينَ فُرُوجَهُمْ وَالْحَافِظَاتِ وَالذَّاكِرِينَ اللَّهَ كَثِيرًا وَالذَّاكِرَاتِ أَعَدَّ اللَّهُ لَهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا:{٣٥}

➬"ሙስሊሞች ወንዶች እና ሴቶች ምዕመናን እና ምዕመናቱን ታዛዦች ወንዶች እና ታዛዦች ሴቶች እውነተኞች ወንዶች እና እውነተኛ ሴቶች ታጋሽ ወንዶች እና ሴቶች አላህ ፈሪዎች ወንዶች እና ሴቶች መፅዋች ወንዶች እና መፅዋች ሴቶት ፆሚዎች ሴቶችም ካልተፈቀደ ሥራ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ወንዶች እና ጠባቂዎች ሴቶች አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶች እና አውሺዎች ሴቶች አላህ ለነርሱ ምህረትንና ታላቅ ምንዳን አዘጋጅቶላቸዋል”። (አህዛብ 35)

➬ከዚህም በተጨማሪ ነብዩ ሙሐመድ ﷺ እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል "እናንተ ወጣቶት ሆይ ! ከእናንተ አካላዊ እና ቁሳዊ አቅም ያለው ሰው ያግባ ፤ ይህንን ጋብቻ አይኑን እነዲሰብርና ብልቱን እንዲጠብቅ ያደርገዋል። ቁሳዊ እና አካላዊ አቅም የሌለው ስው ይፁም። ይህንን ጾም ለርሱ ጋሻው ነው”። (ቡህሪ ዘግቦታል)

➬በተጨማሪም ነብዩ ሙሐመድ ﷺ ጾም እሳትን የሚከላከሉበት ጋሻ ነው ብለዋል። አቡ ኡማማ(ረ.ዐ) ለነብዩ ﷺ የአላህ መልክተኛ ሆይ ! እስቲ ጀነት ልገባበት የምችለውን ስራ ያመልክቱኝ ሲሉ ጠየቋቸው። "ነብዩም ﷺ ጾምን ያዝ እሱም ተወዳዳሪ የለውም" በማለት መለሱ።

ክፍል 5⃣ ይቀጥላል

-----🌸🌸🌸-------
--------🌸🌸🌸-------
-------------🌸🌸🌸------


@abduljilal
----🌺🌺🌺-------
--------🌺🌺🌺------
------------🌺🌺🌺-----

➠ክፍል ➎

➢የረመዳን ወር ቱርፋት

➱የረመዷን ወር በርካታ መልካም ነገሮች የሚገኙበት ወር ነው። ከነዚህ የረመዷን ወር ቱርፋቶች ከሆኑት መካከል አላህ (ሱ.ወ) የሰው ልጆችን ወደ ቀና መንገድ የሚመራ እና በቀልባቸው ውስጥ ላለው በሽታ መድኃኒት የሆነውን ቁርዐን ያወረደበት ወር ፤ ከ1000 ቀን የምትመበልጥ አንዲት ለይለተል-ቀድር የምትባል ሌሊት በውስጡ የምትገኝበት ፣ሰይጣን የሚታሰርበትና የገሀነም በሮች ተዘግተው የገነት በሮች የሚከፈቱበት በመሆኑ ነው።

➱ይህ የረመዷን ፆም ከእስልምና መሠረቶች መካከል አንዱ ሲሆን ጊዜያቶቹ የተመረጡ ጊዜያት ቀናቶቹ ትንሽ ሠርቶ ብዙ ትርፍ የሚገኝበት ቀናት ናቸው በአጠቃላይ ወደ አላህ (ሱ.ወ) ሊያቀርብ የሚችሉ የመልካም ስራዎች በሙሉ ዋዜማ ነው።

➱በእርሱ ውስጥ የሙእሚኖች ልብ ትከፈታለች፣ መስጊዶች በሙስሊሞች ተሞልተው ይደምቃሉ። ልብ ከተለያዩ ሀጢያቶች እና ንፋግነት ፀድቶ ለሰደቃ ፣ ለጾም ፣ ለሶላተ ተራዊ ፣ ለዚክር ፣ ለቁርዐን ፣ ለዱዐ ለስቲግፋር ዝግጁ ሆኖ ይታያል። በአጠቃላይ ይህ ረመዷን ጾም የትርፍ ወር በመሆኑ ወርቃማ ጊዜውን እና መልካም አጋጣሚውን በመጠቀም መልካም ሥራን እያንዳንዷን ጊዜ ሳናባክን መስራት ከእኛ የሚጠበቅ ይሆናል። አንጻራዊ በሆነ መልኩ ልንጠነቀቅ የሚገባን ነገር ቢሆን ሰይጣን እና ነፍስያ አንድ ላይ በመተባበር የሰው ልጆችን እምነት እንዲርቁ ፣ እንዳይጋሩ ፣ በከባድም ሆነ በቀላል ወንጀሎች እንዲዘፈቁ በማድረግ ዘላለማዊ የሆነውን ፀጋ የሚገኝበትን ገነት ለማሳጣት እና ለዘላለማዊ መከራ እና ሰቆቋ በማድረግ ገሀነም ወርደው የእሳት እስረኛ ሆነው ለዘላለም እንዲሰቃዩ ቀስ በቀስ የወንጀል ሱስ የሚያስይዝና ከመልካም ሥራ ወደ ኋላ የሚያስቀር በመሆኑ ሊንነቃበት ይገባል።


@abduljilal

-----🌸🌸🌸-------
--------🌸🌸🌸-------
------------🌸🌸🌸------
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (abdi)
ያስታውሱ ምርጥ ተግባራት በረመዳን
1. ለከንፈሮ እውነት
2. ለምላሶ ዚክር
3. ለአይኖ ቁርኣን
4. ለእጆ በጎ አድራጎት/መስራት
5. ለልቦ ተቅዋ እና
6. ለሰውነቶ ኢባዳ
ለ 15 ሰው ሼር ያድርጉ
____________________
አንብበን እውቀት ካገኘንበት እና ለምን የምናቀውን አናሳውቅ‼️ ስስታም አንሁን ያወቅነውን እናሳውቅ #ሼር_ያድርጉ

@abduljilal

www.tg-me.com/hebre_muslim
ረመዳን በዓመት አንድ ጊዜ እንደሚያብብ እንደ ብርቅዬ አበባ ነው ፣ እና ልክ እንደ ሽቶው ማሽተት እንደጀመርን እስከ ለሌላ ዓመት ይጠፋል."
አብዝተው ይጠቀሙበት
________________
አንብበን እውቀት ካገኘንበት እና ለምን የምናቀውን አናሳውቅ‼️ ስስታም አንሁን ያወቅነውን እናሳውቅ
ለ 10 ሰው #ሼር_ያድርጉ


@abduljilal
እንዲሁም በዚህ የረመዳን ወር የቁርአን ንባባችን እና ጸሎቶቻችንን እንደመጨመር ሁሉ እንዲሁ ባህሪያችንን ለማሻሻል እና ሊኖሩን የሚችሉ መጥፎ ልማዶችን ለማስወገድ እንትጋ ፡፡ የተሻልን ሰዎች ለመሆን ይህንን ቆንጆ ወር እንጠቀምበት ፡፡
________________
አንብበን እውቀት ካገኘንበት እና ለምን የምናቀውን አናሳውቅ‼️ ስስታም አንሁን ያወቅነውን እናሳውቅ
ለ 10 ሰው #ሼር_ያድርጉ


@abduljilal
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (abdi)
በጀናህ (ገነት) ውስጥ አል-ራያን ተብሎ የሚጠራ በር አለ ፡፡ እሱ ለጾሙ ሙስሊሞች ነው ፡፡ በዚያ አካባቢ ባለው የጀነት ደስታ የሚደሰቱት የረመዳንን ወር የፆሙት ብቻ ናቸው ፡፡
____________
አንብበን እውቀት ካገኘንበት እና ለምን የምናቀውን አናሳውቅ‼️ ስስታም አንሁን ያወቅነውን እናሳውቅ
ለ 10 ሰው #ሼር_ያድርጉ

@abduljilal
🌿" የምትጠቀምበትን ያክል ብቻ እወቅ የሚያጠግብህን ያህል ብቻ ብላ ፣ የሚያረካህን ያህል ጠጣ፣ ሁሉን ነገር ማጣት ሰቀቀን ቢሆንም ሁሉንም ነገር ማግኘትም ዕዳ ይሆናል። ምንም አለማወቅ ባዶነት ቢሆንም ሁሉን ማወቅ ደግሞ ሸክምም ይሆናል።

መዋረድ መጥፎ ቢሆንም መከበር ሀላፊነት አለው ። መከልከል ቅሬታ ቢፈጥርም ሁሉን ማድረግ መቻል ግን ይሰለቻልና እርካታ የለውም።

@abduljilal
ውድና የተከበራችሁ ሙስሊም ወገኖቼ እኔ ዛሬ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ ነው
👉አላህ ፍቃድ
ይህን ልጥፍ ወይም የተፖሰተውን ያነበበ ሁሉ በ አላህ ስም እጠይቀዋለሁ
👉❤️ ለነብያችን (ሠ.ዐ.ወ) የላቀውን ቦታ
👉 ለተጨነቀ ፈረጃን
👉 ለታመመ አፍያን
👉 ለታሠረ ፍትህን
👉ለተራበ ርዝቅን
👉 ለታረዘ ልብስን
አለም ላይ ላሉ ሙስሊሞች ሁሉ ፈረጃ እና እዝነቱን ያወድባቸው ዘንድ ዱዐ አድርጉልኝ
በ አላህ ስም እጠይቃችሁ አለሁ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ሙሉውን አንብበው ከዚያም መጨረሻ ላይ ያለውን ቁጥር አይተው ይወስኑ።

የአላህ መልእክተኛ (ሰአወ) እንዲህ ብለዋል ⇣ለምላስ ቀለል ብላ ሚዛን ላይ ከባድ ያለች አላህ ዘንድም የተወደደች ንግግር⇣
*ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም*
ቢያንስ ለ30 ሰዎች ላክ ቢሉትም (ቢያነቡትም) አምስ መቶ ቢሊዮን ሃሰናትን በአላህ ፈቃድ ታገኛለህ።
እንደዚሁ አንተ የላክላቸው ሰዎች እያንዳንዳቸው ለ30 ሰው ከላኩ አሁንም 4.680.000.000 ሃሰናት ታገኛለህ። መቼ እንደምትሞት አታቅምና ሰደቀተል ጃሪያ አድርጋት።
ለማሰራጨት ደቂቃ እንኳን አይወስድብህም።

የቅያማ ዕለት ትመሰክርልህ ዘነድ።

@abdu4321
2024/09/23 21:30:32
Back to Top
HTML Embed Code: