Telegram Web Link
ልብ ስታዝን አይን ታነባለች
ሀዘኔታችን ግን ድንበር አልፎ ከፈጣሪ እንዳያጣላን
# እንግዳዬ

ከሰማይ ጣቃ ጨርቅ
በልክሽ ያጌጠ ፥ ካባ ሰፍቻለሁ
ከቀዥቃዣው ንፋስ
ጠረኑን ዘግኜ ፥ ቤቴን አጥኛለሁ፡፡
በዳመና ጉዝጓዝ
መምጫ መንገድሽን ፥ አሳምሬዋለሁ
ለጎጆ'ችን ድምቀት
ከፀሀይ ቆንጥሬ ፥ ንጋት ሰቅያለሁ፡፡
ታዲያ በምን ሰበብ...
ምን ምክንያት አድርገሽ
እንዲህ ስጠብቅሽ ፥ ልቅር ትይኛለሽ???
ይገርምሻል ውዴ...
ጨለማ እንኳን ባቅሙ
ከልቤ ተረድቶ ፥ እንግዳዬ እንደሆንሽ
ጨረቃዋን ጋርዶ
አካሉን ዘርግቷል ፥ አልጋ ሊያበጅልሽ
ይልቅ ቶሎ መጥተሽ
ጨለማሽ ላይ ተኝ ፥ ኮከብሽን ለብሰሽ፡፡

#abdi

[ 4 U]
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
​​😘ማፍቀርም ሆነ መፈቀር የማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ባህሪ ነው። ፍቅር መስዋትነት ነው ላፈቀሩት ሰው ደስታ ፣ሰላም ፣ምቾት፣እረፍት ሲሉ የራስን ደስታ አቶ ራስን አሳልፎ እስከመስጠት ድረስ የሚከፈለውን ዋጋ ነው።
የእውነት ያፈቀረ ሰው ለኔ ለኔ ከሚል ስሜት የፀዳ ፥ ለኔ ከማለት ይልቅ ለወደደው ሰው ራሱን ሳይሰስት መስጠት ነው
ለኔ።🌹🌺♥️
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
@abdu43211
📍#መልካም ስራዎችህን ከስትንፋስህ በላይ ትኩረት አድርገህ #ጠብቃቸው
ምክንያቱም አንድ ቀን እስትንፋስህ ያቆማል መልካም ስራህ ግን #ህያውና #ዘውታሪ ሆኖ ይኖራል::
_____ለነገ ይህን ተመኘሁላችሁ
መልካም ጁምዐ ይሁንላችሁ

@abdu43211
Forwarded from وبيجوت Tube (La Adry)
አሰላሙ አለይኩም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ሰሚራ ነኝ

...ዛሬ በስልካቹ ምን አይነት notification ገባላቹ ???

ስትጓጉት የነበረው የኡስታዞቻችን ውይይት አልተቋረጠም! በውስጥ መስመሬ ብዙዎቻቹ #ተቋረጠ እንዴ ስትሉኝ ነበር በፍፁም አልተቋረጠም በዚ አጋጣሚ ከ 1K SUBSCRIBE አልፈናል ሁላችሁንም ከልቤ አመሰግናለው ትልቅ ብርታትና ሞራል ሆኖናል በድጋሚ ጀዛከላህኸይረን።

...ዛሬ አንድ Video ፖስት አድርገናል የ video እርእስ ደሞ ነሺዳ በኢስላም እይታ ይላል በኢስላሚክ ነሺዳ ዙርያ ሁለት ኡስታዞች ተወያይተዋል #ኡሱስታዝ_ኤልያስ_አህመድ እና #ኡስታዝ_አቡበከር_አህመድ(አቡኪ) ናቸው

..... ኡሱስታዝ ኤልያስ አህመድ ባሁን ጊዜ ስላሉት ነሺዳዎች ሰፋ ያለ ትንተና ከሰጠ በኃላ ነሺዳ ክልክል ስለመሆኑ ነግሮናል ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ደሞ ስለ ነሺዳ ሰፋ ያለ ትንተና ከሰጠን በኃላ ሙነሺዶችን አበረታቶ አሪፍ ስራ መሆኑን ነግሮናል ይበልጥ ዝርዝሩ ከራሳቸው አንደበት እናድምጥ...

...በግረ መንገዴ አንድ ነገር ልናገር በውስጥ መስመሬ ብዙዎቻቹ "ገጠር አካባቢ ያለን ሰዎች ኔትወርክ ያስቸግረናል ከቻላቹ ቢያንስ እንክዋን የተወያዩትን ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም ዋና ዋና አሳቡን ፃፉልን" ያላችሁኝ ወንድም እህቶች አላቹ ታድያ ጥያቄያቹን ተገቢ ነውና ኢንሻ አላህ በቅርቡ የተወያዩትን በፁሁፍም ማቅረብ እንጀምራለን።

በጨረሻም ወንድም እህቶቼ የዛሬውን የኡስታዞች ውይይት ይኸው ሊንኩን ከታች ታገኙታላቹ ግቡና አድምጡት ሌላም ጊዜ የሚፖሰቱትን ውይይቶች እንዲደርሳቹ በቀይ የተፃፈወን የ #SEBSCRIBE ምልክቱን በመጫን ሰብስክራይብ አድርጉ #LIKE #SHER ማድረጋችሁንም አትርሱ❤️😍

የቴሌግራም አድሚኖችም እንደተለመደው ልክ እንደዚ ቀደሙ በሁሉም ቻናል ላይ ፖስቱ ሼር አድርጉልን💚

👇👇👇

https://youtu.be/cfPl7lxUF4g
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (abdi)
💜 ለመጀመሪያ ጊዜ ያየህን አካል
ሺህ ጊዜ አንተን ለማየት እንዲመኝ
ማድረግ የምትችለው በስነ-ምግባርህ
ብቻ ነው ።
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (abdi)
💜 አንድ አንድ ሰው ታላቅ ሆኖ
ሳይሆን በዙሪያው የከበቡት ሰዎች
ትናንሽ ስለሆኑ ታላቅ መስሎ ይታያል ።
ይቅርታ🙏 የአብሮነት መሰረት ነው
አብሮነት ደግም ሰላም 🕊ተምሳሌት ነው
ሰላምም የፍቅር💖 ማሳያ ነው
ስለዚህ ሁሌም ይቅርታ🙏
ሁሌም አብሮነት👨‍👨‍👦‍👦
ሁሌም ሰላም🕊
ሁሌም ፍቅር💖
🦋መልካም የአብሮነት ና የፍቅር ቀን 🦋
@abdu43211
@hebre_muslim
ልብ ይበሉ

🔸ጌታና አምላክ ነው ተብሎ የሚታመንን አካል ልደት ማክበር ካፊርነትን በራስ ላይ መመስከርና በሙሉ ልብም ያለማሰብ ምልክት ነው

🔸ከአላህ በስተቀር እውነተኛ አምላክ አለመኖሩን እያወቁና እየመሰከሩ በዓሉን መደገፍና ብሎም መሳተፍ የዐቂዳ ችግርና ድክመት ነው

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ اللَّهُ الصَّمَدُ
لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ وَلَمْ يَكُنْ لَهُ كُفُوًا أَحَدٌ


✍🏻 ኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም
@abdu4321
@abdu43211
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ክፍል 2⃣ በቅርቡ





ሼር አድርጉና የ አጅር ተካፋይ ይሁኑ

@abdu43211
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሏሁ ሡብሀነሁ ወተዐላ ምንዳችሁን ያብዛላችሁ
እያልኩ እኚህን ቻናሎች ለ አላህ ብላችሁ ቢያንስ ለ 1⃣0⃣ ሠዎች አጋሩልኝ

1⃣ @hebre_muslim

2⃣ @abdu43211

3⃣ @abdu4321 አስተያየት ካለ👇👇

@ab_di1
ድህነት ክብርህን አይቀንሰውም!

እርግጥ በጣም ደሃ ሰው ልትሆን ትችላለህ። ነገርግን ነቢዩ (ዐሰወ) የአንተን ያህል እንኳን ንብረት አልነበራቸውም። የቀትር ማረፊያቸው የዘንባባ ዝንጣፊ ከሰውነታቸው ላይ ሰንበር ይሰራ ነበር። እንግዳ ከመጣባቸው ደግሞ ትራሳቸውን ለቀው መሬት ላይ ይሆናሉ። ሲሞቱ ሰላሳ መስፈሪያ ስንዴ የተበደሩትን የከፈሉላቸው አቡበክር (ረዐ) ነበሩ።

ታዲያ ድህነት ከክብራቸው ምን ቀነሰ? እነዚህን መናኝ ነቢይ ነገ በቂያማህ ቀን የአደም ልጆች ንጉሳኑ መኳንንቱ ባለፀጎቹ ሁሉ ምልጃ ይጠይቋቸዋል። አላህም ከሱጁዳቸው አስነስቶ የፈለከውን ጠይቅ! የሚላቸው እነሱን ነው። ይህ ክብር ከአንተ በላይ ደሃ ለነበረ ነቢይ የተሰጠው ነው።

ምናልባት በኢብራሂም (ዐሰ) ዘመን የነበረውን የባቢሎን ንጉሥ ስሙን እንኳን አታውቀው ይሆናል። ኢብራሂም ግን የወንድምህ ወይም የአጎትህ ስም ነው። ስደተኛውን ኢብራሂምን (ዐሰ) አውቀህ ንጉሡን ለምን ረሳሁ ካልክ ምክንያቱም መልካም ዝና አላህን በመፍራት ብቻ ስለሚገኝ ነው።

ከዚህ ምን ትማራለህ? በእርግጥ ድህነትህ ደረጃህን አይቀንስም። በሃብትህም ክብርህ አይጨምርም። ከፍም ዝቅም የሚያደርግህ ተቅዋህ ነው። አላህን የማይፈራ ሰው ሃብታም ቢሆንም በስራው የረከሰ፥ ሹመኛም ቢሆን በክብሩ የቀለለ ነው። ተቅዋ ያለው ደግሞ ደሃም ቢሆን አላህን በመፍራቱ ብቻ በሰዎችም የታፈረ ሆኖ ታገኘዋለህ። ለመከበር ከፈለክ ሀብትህ እስኪካብት አትጠብቅ። ተቅዋህን ብቻ አሳምር። በዓለማት የተከበሩት ሁሉ ከአንተ በላይ ደሃ ናቸውና።

@abdu43211
አሠላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ወድና የተከበራችሁ የ ሀላሌ ቻናል ቤተሠቦች የረበና ሠላም በእናንተ ላይ ይሁን
ጁማችን ምሽቱም ያማረና የተዋበ ይሁንላችሁ🙏🙏🙏🙏
❤️
❤️
❤️
❤️
@abdu43211
እንደነገርኩሽ ነው ...
       ****
በሃሰት ከተማ ፣
እውነት እንግዳ ናት ፣ ልክ እንደሚባለው
ለስኬት አልባዎች ፣
ስለስኬት ማውጋት ፣ እራሱ ውድቀት ነው
እንደነገርኩሽ ነው ...
ሰው ድክመቱን አውቆ ፣
ላለመቀበል ሲል ፣ የእምነቱን እዳ
ከ ኡስታዞች ዓይን ስር ፣
ጉድፍ ይፈልጋል ፣ ላለመቀበል ሲል!!
       *###**
(አብዱ ጀላል)
@abdu43211
🌹🍃🕊...ጊዚያዊ ማንነት

ዛሬ ይሄ ጎደለ ደግሞ ይሄ ሞልቷል
ዛሬ ይሄ ገረጣ ደግሞ ይሄ ወዝቷል
ማለት እንደቀድሞው አንደበቴ ትቷል

ሽፍንፍን አድርጎ እውነታን ደብቆ
ቁጥብነት ለምዶ ከግልፅነት ርቆ
ምን እንዳልተከፋ ለይስሙላ ስቆ

የሀቅ ምርኮኛ እንዳልነበር ትላንት
ዛሬ እውነትን ክዶ እንዳፈራ ጠላት
ሳር ቅጠሉ አውቆታል
ከማወቅ ባለፈም ምስክር አፍርቷል

አይኔ ውሸታም ነው ምላሴም አስመሳይ
ጥርሴም ሀሰተኛ ደስታን ገላጭ መሳይ
ልቤም ወረተኛ ለቃሉ ያልተገዛ
የሚያድረው ከቅርብ የሚያልመው እዛ

ለምን ሆነ ብሎ ማን ደፍሮ ጠየቀ
እንዲህ ነው አሉ እንጂ እየተሳለቁ
ጠየኩ ያሉስ ቢሆን መች ምላሽ አገኙ
ልቤ ያቀዋልና አመንኩት ባለው ሰው
…ስንቴ እንደተሞኘ

ስለዚህ አንድ ቀን ይሄ ጊዜ አልፎ
የተስፋዬ ሻማ ቦግ ብሎ በርቶ
…ፅልመቴ ተገፎ
ራሴን እስክሆን በቀድሞው ማንነት
ጊዜያዊ ምርጫዬ ሆኗል ብቸኝነት።


💖⚘➣ @❥ ♥️💍
••●🍃🌹🍃●••

@abdu43211
❤️የእናት ፍቅር ማለት አንድ ሰብዓዊ ፍጡር የማይቻለውን ነገር እንዲያደርግ የሚያስችል ነዳጅ ነው
እናት የሌሎች ሁሉ ቦታ ልትሆን የምትችል ሲሆን ሌላ ማንም ሊወስድባት የማይችል ቦታ ናት😍😍

መልካም መልካሙን ለእናቶች
እናቴ ወድሻለው❤️❤️❤️❤️
እናቱን የሚወድ እስኪይስጥ
❤️
@abdu43211
2024/09/24 01:27:33
Back to Top
HTML Embed Code: