Telegram Web Link
#"በየቀኑ የምታደርጋቸውን ነገሮች ካልቀየርክ ህይወትህን መቼም አትቀይርም፤ ትልቁ የስኬት ሚስጥር ያለው የቀን ውሎህ ላይ ነው" የአመራር ጥበብ ምሁሩ ጆን ማክስዌል ሀሳብ ነው። ላንተ በዓመት ውስጥ ምርጡ ቀኔ ይሄ ነው የምትለው ምን እየሰራህ የዋልክ ቀን ነው? ያ ምርጥ ቀን ላይ ውሎህ ደስተኛ ካረገህ እና ወደ ስኬት የሚወስድህ ከሆነ ለምን ሁሉንም ቀን እንደሱ ለማድረግ አትሞክርም? ይሄን ማድረግህ የት እንደሚያደርስህ ካሰብከውማ ጆን ማክዌል ልክ ነው ትላለህ።

ማንኛውም አስተያየት
Any comment 👉 @abduljilal

@hebre_muslim
በሰዎች መካከል ልዩነት የሚፈጥረው አንዱ ለማድረግ የሚከብደውን ወይ የሚፈራውን ነገር ሌላኛው እየደበረውም ቢሆን ጨክኖ ማድረጉ ነው። ህይወት ቀላል እንዲሆን አትመኝ፤ ከባድ ቢሆን እንኳን አንተ ከሱ በላይ ከባድ ሆነህ ማሸነፍን አስብ!

መጀመሪያ ተመኝ እንድታገኝ! ከዛ የሚጠበቅብህን ሁሉ አድርግ ያኔ በህይወት ሚዛን አንተ የማታልፈው ፈተና የለም፤ ወዳጄ ብርሀን ማየት የሚፈልግ ሁሉ ጨለማውን ታግሶ ማሳለፍ አለበት!
#ኢንሻ_አላህ

ማንኛውም አስተያየት
Any comment 👉 @Abduljilal

@hebre_muslim
Watch "አብዲ ቲዩብ" on YouTube
https://youtube.com/shorts/SY0aivrYc0U?feature=share
'ትንንሽ ሀሳቦች ሁሌም ትንንሽ ናቸው ግን የትልቁን ቦታ ይይዛሉ' አዘርግ የሚባል ደራሲ አባባል ነው፤ እውነት ነው ከአላማችን ሊያስቀሩ የሚፈታተኑን ነገሮች ጥቃቅን ቢሆኑም ግዙፍ የሆነው ህልማችንን የመጋረድ አቅም አላቸው፣ መጋረድ የሚችሉት ግን አይምሯችንን እንዲቆጣጠሩት ስለምንፈቅድላቸው ነው።


@hebre_muslim
ቁጭ ብለህ እንዲህ ባደርግ እንዲህ ቢሆን አትበል! አድርገው! ወደ ተግባር ግባ! ወዳጄ ባህሩ ላይ ማፍጠጥ አያሻግርህም ተነስተህ ጀልባውን መቅዘፍ አለብህ።

ከአልጋህ ተነስ፣ ሰላትህን ስገድ ፣ ቁርዐንንም ቅራ ፣ ስፖርቱን ስራ፣ መፅሀፉን አንብብ፣ በጊዜህ ወደ ስራህ ግባ ፤ ወዳጄ የተግባር ሰው ካልሆንክ በሀሳብ መንሳፈፍ ነው ስራህ! ዳይ ተነስ!


ለበለጠ አነቃቂ ጽሁፎች ➤@hebre_muslim
የተከበራችሁ ውድ የአላህ ባሪያዎች ይህ ከላይ በምስሉ የምትመለከቱት ቢላል መስጂድ ይባላል በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን በጌቶ ወረዳ በውርባዘር መንደር እየተገነባ ይገኛል ሆኖም የአቅም ዉስንነት ገጥሞን የተወሰነ ጊዜ ግንባታዉ ቆሞ ነበር ሆኖም አሁን ሁላችንም ርብርብ እያደረግን ነዉ ለዚህ መልካም ስራ የሁላችንም ሀላፊነት እንደሆነ እናምናለን ስለዚህ አሁነ የሚያስፈልጉን እቃዎች 1,ቀለም ማስቀባት 2, ኮርኒስ ማሰራት 3,ሶላር ማይክ ሚያንቀሳቅስ 4, የቁም አና የደረት ማይክ ሌሎች ያልተገለፁ ነገሮች የማማላት ስራ የሁላችንም ስለሆነ ትብብር ታደርጉ ዘንድ በአላህ ስም እንጠይቃለን፣አካውንት ቁጥር 1000042868691 መሀመድ ገትር &ቀድሩ ዋበላ ለምታደርጉት መልካም ትብብር የመልካም በር ይከፈትላቹ ዘንድ አላህ እንማፀነዋለን

@hebre_muslim
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
۞ اللَّهُ نُورُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ مَثَلُ نُورِهِ كَمِشْكَاةٍ فِيهَا مِصْبَاحٌ ۖ الْمِصْبَاحُ فِي زُجَاجَةٍ ۖ الزُّجَاجَةُ كَأَنَّهَا كَوْكَبٌ دُرِّيٌّ يُوقَدُ مِن شَجَرَةٍ مُّبَارَكَةٍ زَيْتُونَةٍ لَّا شَرْقِيَّةٍ وَلَا غَرْبِيَّةٍ يَكَادُ زَيْتُهَا يُضِيءُ وَلَوْ لَمْ تَمْسَسْهُ نَارٌ ۚ نُّورٌ عَلَىٰ نُورٍ ۗ يَهْدِي اللَّهُ لِنُورِهِ مَن يَشَاءُ ۚ وَيَضْرِبُ اللَّهُ الْأَمْثَالَ لِلنَّاسِ ۗ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

አላህ የሰማያትና የምድር አብሪ ነው፡፡ የብርሃኑ ምሳሌ በውስጧ መብራት እንዳለባት (ዝግ) መስኮት፣ መብራቱ በብርጭቆ ውስጥ የኾነ፣ ብርጭቆይቱ ፍፁም ሉላዊ ኮከብ የምትመሰል፣ ምሥራቃዊው ምዕራባዊም ካልኾነች ከተባረከች የወይራ ዛፍ ዘይቷ እሳት ባይነካውም እንኳ ሊያበራ የሚቀርብ ከኾነች (ዘይት) የሚቃጠል እንደ ሆነ (መብራት) ነው፡፡ (ይህ) በብርሃን ላይ የኾነ ብርሃን ነው፡፡ አላህ ወደ ብርሃኑ የሚሻውን ሰው ይመራል፡፡ አላህም ለሰዎች ምሳሌዎችን ያቀርባል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡

@hebre_muslim
አሁን ካለህ በላይ ስኬት ከፈለግክ አሁን ካለህ በላይ ምን ለማድረግ ወስነሃል? ነው ጥያቄው ። የፈለግከውን ያሻህን መመኘት መፍትህ ነው እናም ምን ለማድረግስ ዝግጁ ነህ ?

አሁን ካለህ እጥፍ ከፈለግክ አሁን ካለክ እጥፍ ራስህን አዲስ ነገር ለመሞከር ፣ ለመሣሣት ክፍት አርግ !

ለበለጠ ➤@hebre_muslim
@hebre_muslim
በቅርብ ቀን ኢንሻአላህ
~
http://www.tg-me.com/hebre_muslim
📮 የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ቁርኣን መቅራቷ!

★ ሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድ፡-

“የወር አበባ ላይ ያለችን ሴት ከሒፍዟ ቁርኣን እንዳትቀራ የሚከለከል ማስረጃ #አናውቅም” ብለዋል፡፡ [ሸርሑ ሱነን አቢ ዳውድ]

★ ኢትዮጵያዊው ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ዐሊ ኣደምም እንዲሁ መቅራት #እንደምትችል አስፍረዋል፡፡ [ዘኺረቱል ዑቅባ፡ 4/570-571]

★ አልባኒና ፈርኩስም ይህንኑ መቅራት ትችላለች የሚለውን ሀሳብ ከመረጡ ዐሊሞች ውስጥ ናቸው፡፡

📌 ማሳሰቢያ፡-

እስካሁን የተወራው ቁርኣንን በእጅ ሳይነኩ #በቃል መቅራትን እንጂ ሙስሐፍ መንካትን የሚመለከት አይደለም፡፡ ሆኖም ግን እንደ #ሞባይል ካሉ መሳሪያዎች ላይ የሚገኘውን የቁርኣን አፕሊኬሽን ተጠቅሞ መቅራት እንደሚቻል በርካታ የዘመናችን ዑለማዎች ገልፀዋል፡፡
والله أعلم.
┄┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄
⭕️ ያመለጣችሁን ትምህርቶች ለማግኘት👇

@hebre_muslim
@hebre_muslim

⭕️ ለተጨማሪ የtelegram ቦታችንን :👇ይቀላቀሉን 👇
https://www.tg-me.com/hebre_muslimbot
https://www.tg-me.com/hebre_muslimbot
እመነኝ ወዳጄ አንተ ብቻ ጣር ልፋ በቻልከው አቅምህ ተንቀሳቀስ ለጊዜው ውጤታማ ላቶን ትችላለሁ ስኬትም ልትርቅህ ትችላለች አንድ ቀን ግን እራስህን በሴኬት ማማላይ እንደምታገኘውና አላህ የልፋትህ ውጤት እንሚሰጥህ አትጠራጠር ኢንሻ አላህ

ለበለጠ ➤ @hebre_muslim
@hebre_muslim
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
🛌 ከመኝታ በፊት የሚባሉ

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ ﴿١﴾ اللَّهُ الصَّمَدُ ﴿٢﴾ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ ﴿٣﴾ وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ ﴿٤﴾

(1) በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ (1) «አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡ (2)«አልወለደም፤አልተወለደምም፡፡ (3) «ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡» (4)

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ ﴿١﴾ مِن شَرِّ مَا خَلَقَ ﴿٢﴾ وَمِن شَرِّ غَاسِقٍ إِذَا وَقَبَ ﴿٣﴾ وَمِن شَرِّ النَّفَّاثَاتِ فِي الْعُقَدِ ﴿٤﴾ وَمِن شَرِّ حَاسِدٍ إِذَا حَسَدَ ﴿٥﴾

በል «በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ፡፡ (1) «ከፈጠረው ፍጡር ሁሉ ክፋት፡፡ (2) «ከሌሊትም ክፋት ባጨለመ ጊዜ፤ (3) «በተቋጠሩ (ክሮች) ላይ ተፊዎች ከኾኑት (ደጋሚ) ሴቶችም ክፋት፡፡ (4) «ከምቀኛም ክፋት በተመቀኘ ጊዜ፤ (እጠበቃለሁ በል)፡፡» (5)

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ النَّاسِ ﴿١﴾ مَلِكِ النَّاسِ ﴿٢﴾ إِلَٰهِ النَّاسِ ﴿٣﴾ مِن شَرِّ الْوَسْوَاسِ الْخَنَّاسِ ﴿٤﴾ الَّذِي يُوَسْوِسُ فِي صُدُورِ النَّاسِ ﴿٥﴾ مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ ﴿٦﴾

(1) በል «በሰዎች ፈጣሪ እጠበቃለሁ፡፡ (1) «የሰዎች ሁሉ ንጉሥ በኾነው፡፡(2) «የሰዎች አምላክ በኾነው፡፡ (3) «ብቅ እልም ባይ ከኾነው ጎትጓች (ሰይጣን) ክፋት፡፡ (4) «ከዚያ በሰዎች ልቦች ውስጥ የሚጎተጉት ከኾነው፡፡ (5) «ከጋኔኖችም ከሰዎችም (ሰይጣናት እጠበቃለሁ በል)፡፡»(6)

‘\ነብዩ(ሶ.ዐ.ወ) ዘወትር ከመተኛታቸው በፊት ሁለት መዳፎቻቸውን በማጋጠም ከላያቸው ላያ ትፍ ትፍ ይሉባቸዋል፡፡ ከዛም ከላይ ያሉትን ሶስቱን ሱራዎች ያነባሉ፡, በመቀጠልም በመዳፎቻቸው ከአካላቸው የቻሉትን ያክል ያብሱ ነበር፡፡ ከራሳቸው በመጀመሪያ ፊታቸውንና በፊታቸው በኩል ያሉ የአካል ክፍሎቻቸውን ይደባብሳሉ፡፡ ከዚያም ሌሎችን የአካል ክፍሎቻቸውን፡፡ ይህንኑ ሦስት ጊዜ በመደጋገም ይፈጽማሉ፡፡ ’

اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ مَنْ ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِنْدَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَيْءٍ مِنْ عِلْمِهِ إِلَّا بِمَا شَاءَ وَسِعَ كُرْسِيُّهُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَلَا يَئُودُهُ حِفْظُهُمَا وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ

አልሏሁ ላኢላህ ኢልላ ሁወል ሐይዩል ቀይዩም፣ ላተእኹዙሁ ሱነቱን ወላ ነውም፤ ለሁ ማፊስማዋቲ ወማ ፊል አርድ፤ ወንዘልለዚ የሸፈዑ ዒንደሁ ኢልላ ቢኢዝኒሂ ያዕለሙ ማበይነ አይዲይሂም ወማ ሀኸልፈሁም ወላ ዩሒጡና ቢሸይኢን ሚን ዒልሚሂ ኢልላ ቢማሻአ፤ ወሲዐ ኩርስዩዑሰማዋቲ ወል አርድ ወላ የኡዱሁ ሒፍዙሁማ ወሁወል ዐልዩል ዐዚም

አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)፡፡ መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡ ጥበቃቸውም አያቅተውም፡፡ እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡ (255).

{ آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنْزِلَ إِلَيْهِ مِنْ رَبِّهِ وَالْمُؤْمِنُونَ كُلٌّ آمَنَ بِاللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِنْ رُسُلِهِ وَقَالُوا سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا غُفْرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيْكَ الْمَصِيرُ } { لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا لَهَا مَا كَسَبَتْ وَعَلَيْهَا مَا اكْتَسَبَتْ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَا إِنْ نَسِينَا أَوْ أَخْطَأْنَا رَبَّنَا وَلَا تَحْمِلْ عَلَيْنَا إِصْرًا كَمَا حَمَلْتَهُ عَلَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِنَا رَبَّنَا وَلَا تُحَمِّلْنَا مَا لَا طَاقَةَ لَنَا بِهِ وَاعْفُ عَنَّا وَاغْفِرْ لَنَا وَارْحَمْنَا أَنْتَ مَوْلَانَا فَانْصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ }

አመነርረሱሉ ቢማ ኡንዚለ ኢለይሂ ሚንረቢሂ ወልሙእሚኑን ኩሉን አመነ ቢልላሂ ወመላኢከቲሂ ወኩቱቢሂ ወሩሱሊሂ ላኑፈሪቁ በይነ አሐዲን ሚን ሩሱሊህ ወቃሉ ሰሚእና ወአጠእና ጉፍራነከ ረብበና ወኢለይከል መሢር፣ ላዩከሊፋልላሁ ነፍሰን ኢልላ ውስአሃ ለሃ ማከሰበት ወዐለይሃ መክተሰበት ረብበና ላቱአኺዝና ኢንነሲና አው አኸጠእና ረብበና ወላ ተህሚል ዐለይና ኢስረንከማ ሐመልተሁ አለልለዚይነ ሚን ቀብሊና ረብበና ወላ ቱሐምሚልና ማላጣቀተ ለና ቢህወዕፋ እና ወግፊር ለና ወርሃምና አንተ መውላና ፈንሱርና አለል ቀውሚል ካፊሪን››

‹‹መልእክተኛው ከጌታው ወደርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖችም (እንደዚሁ)፤ ሁሉም በአላህ፣ በመላዕክቱም፣ በመጽሐፍቱም፣ በመልዕክተኞችም ከመልዕክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም (የሚሉ ሲሆኑ) አመኑ፡፡ ሰማን፤ ታዘዝንም፡፡ ጌታችን ሆይ! ምህረትህን (እንሻለን)፡፡ መመለሻም ወዳንተ ብቻ ነው፡፡ አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳት፤ ለርሷ የሰራችው አላት በርሷም ላይ ያፈራችው (ኃጢያት) አለባ፡፡ (በሉ)፡- ጌታችን ሆይ! ብንረሳ፣ ወይም ብንስት አትያዘን፤ (አትቅጣን)፤ ጌታችን ሆይ!! ከባድ ሸክምን ከኛ በፊት በነበሩት ላይ እንደጫንከው በእኛ ልይ አትጫንብን፤ ጌታችን ሆይ! ለእኛም በእርሱ ችሎታ የሌለንን ነገር አታሸክመን፤ ከኛም ይቅርታ አድርግ፤ ለኛም ምህረት አድርግ፤ እዘንልንም፤ ዋቢያችን አንተ ነህና፤ በከሃዲዎች ህዝቦች ላይም እርዳን፡፡›› (አል-በቀራህ: 285 to 286) .”
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
ክፍል 2⃣

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

بِاسْمِكَ رَبِّيْ وَضَعْتُ جَنْبِيْ، وَبِكَ أَرْفَعُهُ، فَإِنْ أَمْسَكْتَ نَفْسِيْ فَارْحَمْهَا، وَإِنْ أَرْسَلْتَهَا فَاحْفَظْهَا بِمَا تَحْفَظُ بِهِ عِبَادَكَ الصَّالِحِيْنَ.

‘ቢስሚከ ረብቢ ወዳእቱ ጀንቢ ወቢከ አርፈኡህ ኢን አምስከተ ነፍሲ ፈርሐምሃ ወኢን አርሰልተሃ ፈሀፈዝሃ ቢማ ተሀፈዝ ቢሂ ኢባደከ አስሳሊሂን

ጌታዬ ሆይ! በስምክ ጎኔን አሳርፌያለሁ፡፡ በስምህም አነሳዋለሁ፡፡ ነፍሴን በዚያው ካስቀራሀት እዘንላት፡፡ ከላክካት ደግሞ መልካም ባሮችህን በምትጠብቅበት (ስልትህ) ጠብቃት፡፡’

اَللَّهُمَّ إِنَّكَ خَلَقْتَ نَفْسِيْ وَأَنْتَ تَوَفَّاهَا، لَكَ مَمَاتُهَا وَمَحْيَاهَا، إِنْ أَحْيَيْتَهَا فَاحْفَظْهَا، وَإِنْ أَمَتَّهَا فَاغْفِرْ لَهَا. اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ الْعَافِيَةَ.

‘አልሏሁምመ ኢንነከ ኸለቅተ ነፍሲ ወአንተ ተወፋሃ ለከ መማቱሃ ወመሀያሃ ኢን አህየይተሃ ፈህፈዝሃ ወኢን አመትተሃ ፈግፊር ለሃ አልሏሁምመ ኢንኒ አስአሉከል ዐፊያህ

አላህ ሆይ! ነፍሴን ፈጥረሃታል፡፡ የምትገድላትም አንተው ነህ፡፡ ሞቷም ህይወቷም ላንተ ነው፡፡ ህያው ካደረግካት ጠብቃት፡፡ ከገደልካት ደግሞ ምህረትህን ለግሳት፡፡ አላህ ሆይ! ጤንነትን እጠይቅሃለው፡፡ .’

اَللَّهُمَّ قِنِيْ عَذَابَكَ يَوْمَ تَبْعَثُ عِبَادَكَ. (3×)

‘አልሏሁምመ ቂኒ አዛበከ የውመተብአሱ ዒባደከ

አላህ ሆይ! ባሮችህን በቦት ቀስቅስበት ወቅት ከቅጣትህ ጠብቀኝ፡

بِاسْمِكَ اللَّهُمَّ أَمُوْتُ وَأَحْيَا.

‘ቢስምከልሏሁምመ አሙቱ ወአህያ

አላህ ሆይ! በስምህ እሞታለሁ፤ ነፍስም እዘራለሁ፡፡ ’

سُبْحَانَ اللهِ (33×) وَالْحَمْدُ لِلَّهِ (33×) وَاللهُ أَكْبَرُ (33×).

ሱብሐነልላሂ ወልሃምዱ ሊልላሂ ወልላሁ አክበር

አላህ ሆይ! ጥራት ይገባህ- ሠላሣ ሶስት ጊዜ፤ ‹‹ለአላህ ምስጋና ይገባው››ሠላሣ ሶስት ጊዜ፤ ‹‹አላህ ከሁሉም የላቀ ነው››ሠላሣ ሶስት ጊዜ፡፡

اَللَّهُمَّ رَبَّ السَّمَاوَاتِ السَّبْعِ وَرَبَّ الْعَرْشِ الْعَظِيْمِ، رَبَّنَا وَرَبَّ كُلِّ شَيْءٍ، فَالِقَ الْحَبِّ وَالنَّوَى، وَمُنْزِلَ التَّوْرَاةِ وَاْلإِنْجِيْلِ وَالْفُرْقَانِ، أَعُوْذُ بِكَ مِنْ شَرِّ كُلِّ شَيْءٍ أَنْتَ آخِذٌ بِنَاصِيَتِهِ. اَللَّهُمَّ أَنْتَ اْلأَوَّلُ فَلَيْسَ قَبْلَكَ شَيْءٌ، وَأَنْتَ اْلآخِرُ فَلَيْسَ بَعْدَكَ شَيْءٌ، وَأَنْتَ الظَّاهِرُ فَلَيْسَ فَوْقَكَ شَيْءٌ، وَأَنْتَ الْبَاطِنُ فَلَيْسَ دُوْنَكَ شَيْءٌ، اقْضِ عَنَّا الدَّيْنَ وَأَغْنِنَا مِنَ الْفَقْرِ.

‘አልሏሁምመ ረብበስሰማዋቲስ ሰብዒ ወረብበል ዐርሺል ዐዚም ረብበና ወረብበ ኩልለ ሸይኢን ፉሊቀል ሐቢ ወንነዋ ወሙንዚላት ተውራተ ወልኢንጂሊ ወልፋርቃኒ አዑዙቢክ ሚን ሸርሪ ኩልሊ ሸይኢን አንተ አኺዙን ቢንሲየቲሂ አልላሁምመ አንተል አወሉ ፈለይስ ባዕደከ ሸይኡን ወአንተል አኺሩ ፈለይስ ባዕደከ ሸይኡን ወአንተዝዛሂሩ ፈለይስ ፈውቀከ ሸይኡን ወአንተል ባጢኑ ፈለይስ ዱነከ ሸይኡን አቅዲ ዐንና ደይነ ወአግኒና ሚነልፈቅረ

የሰባቱ ሰማያት አምላክ÷ የታላቁ ዓርሽም አምላክ የሆንከው አላህ ሆይ! አምላካችን፣ የሁሉም ነገር አምላክ፣ ፍሬዎችን የምትፈለቅቅ፣ ተውራትንና ኢንጂልን፣ ፋርቃንንም ያወረድክ የሆንክ አላህ ሆይ! ከሁሉም ነገር ክፋት በአንተ እመበቃለሁ፡፡ ሁሉንም ነገር መቆጣጠር ትችላለህ፡፡ አላህ ሆይ! አንተ የመጀመሪያው ነህ፡፡ ከአንተ በፊት ምንም ነገር የለም፡፡ የመጨረሻውም ነህ፡፡ ከአንተ በኋላ ምንም ነገር አይኖርም፡፡ አንተ ግልጽ ነህ፡፡ ከአንተ በላይ ምንም ነገር የለም፡፡ ድብቅ ነህ፡፡ ከአንተውጭም ምንም ነገር የለም፡፡ እዳችንን አስወግድልን፡፡ ከድህነት ገላግለህ ክብረትን ለግሰን፡፡ ’

الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِيْ أَطْعَمَنَا وَسَقَانَا وَكَفَانَا وَآوَانَا، فَكَمْ مِمَّنْ لاَ كَافِيَ لَهُ وَلاَ مُؤْوِيَ.

‘አልሐምዱ ሊልላሂ አልለዚ አጥአመና ወሰቃና ቀከፋና ወአዋና ፈከም ሚምመን ላ ካፊየ ለሁ ወላ ሙእዊየ

ላበላንና ላጠጣን, ለተንከባከበንና ላስጠጋን አላህ ምስጋና ይገባው፡፡ ተንከባካቢና አስጠጊ የሌላቸው ስንት ሰዎች አሉ!
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
ክፍል 3⃣


┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

اَللَّهُمَّ عَالِمَ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ فَاطِرَ السَّمَاوَاتِ وَاْلأَرْضِ، رَبَّ كُلِّ شَيْءٍ وَمَلِيْكَهُ، أَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَـهَ إِلاَّ أَنْتَ، أَعُوْذُ بِكَ مِنْ شَرِّ نَفْسِيْ، وَمِنْ شَرِّ الشَّيْطَانِ وَشِرْكِهِ، وَأَنْ أَقْتَرِفَ عَلَى نَفْسِيْ سُوْءًا أَوْ أَجُرُّهُ إِلَى مُسْلِمٍ.

‘አልሏሁምመ አሊመል ገይቢ ወሸሸሃደቲ ፋጢሪስሰማዋቲ ወልአረዲ ረብበ ኩልለ ሸይኢን ወመሊከሁ አሸሃዱ አንላኢላህ ኢልላ አንተ አዑዙቢከ አሸሃዱ አንላኢላህ ኢልላ አንተ አዑዙቢከ ሚን ሸርሪ ነፍሲ ወሚን ሸርሪ ሸሸይጣኒ ወሺርኪሂ ወአን አቅተሪፍ ዐላ ነፍሲ ሱአን አው አጁርረሁ ኢላ ሙስሊም

ሩቅንም ቅርብንም አዋቂ÷ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ÷ የሁሉም ነገር አምላክና ገዥ የሆንከው አላህ ሆይ! ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፡፡ ከነፍሴ ተንኮል÷ ከሸይጧንና ከአጋሮቹ ተንኮልም÷ በራሴ ወይም በሙስሊሞች ላይ መጥፎ ከመፈፀምም በአንተ እጠበቃለሁ ’

« يقرأ الم تنزيل السجدة وتبارك الذي بيده الملك » .

ሱራህ አሰጅዳን እና ሱራ አል ሙልክን ይቅሩ.

اَللَّهُمَّ أَسْلَمْتُ نَفْسِيْ إِلَيْكَ، وَفَوَّضْتُ أَمْرِيْ إِلَيْكَ، وَوَجَّهْتُ وَجْهِيَ إِلَيْكَ، وَأَلْجَأْتُ ظَهْرِيْ إِلَيْكَ، رَغْبَةً وَرَهْبَةً إِلَيْكَ، لاَ مَلْجَأَ وَلاَ مَنْجَا مِنْكَ إِلاَّ إِلَيْكَ، آمَنْتُ بِكِتَابِكَ الَّذِيْ أَنْزَلْتَ وَبِنَبِيِّكَ الَّذِيْ أَرْسَلْتَ.

‘አልሏሁምመ አስለምቱ ነፍሲ ኢለይከ ቀፈውወድቱ አምሪ ኢለይከ ወወጅጀህቱ ወጂሂ ኢለይከ ወአልጀእቱ ዛህሪ ኢለይከ ረግበተን ወረህበተን ኢለይከ ላመልጀአ ወላ መንጃ ሚንከ ኢልላ ኢለይከ አመንቱ ቢኪታቢከልለዚ አንዘልተ ወቢነቢይይከልለዚ አርሰልተ

አላህ ሆይ! ነፍሴን ለአንተ አስረክቢያለሁ፡፡ ጉዳዩን ሁሉ ወደ አንተ አስጠግቻለሁ፡፡ ፊቴን ወደ አንተ አዙሪ ያለሁ፡፡ ጀርባዬን ወደ አንተ መልሻለሁ፡፡ (እርካታህን ለማግኘት) በመጓጓት፤ (ቁጣህን) በመፍራት፡፡ መመላሻም፣ ከአንተ (ከቅጣትህ) ነፃ መውጫም ወደአንተ ከመመለስ ውጭ ሌላ መንገድ የለም፡፡ ባወረድከው ኪታብ፣ በላከው ነብይም አምኛለሁ፡፡
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:

((لا تعلموا العلم لتباهوا به العلماء، ولا لتماروا به السفهاء، ولا تخيروا به المجالس، من فعل ذلك فالنار النار))

📚 رواه ابن ماجة وابن حبان

የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–

[ እውቀትን ዑለማዎች ላይ ለመኩራራት፣ ቂሎችን(መሃይሞችን)ለመሞገት፣ መቀመጫ ቦታ ለመምረጥ አትማሩ። ይህን ያደረገ ሰው እሳት! እሳት! (ትጠብቀዋለች)።]

📚ኢብን ማጀህ እና ኢብን ሒባን ዘግበውታ።
👇
👉 @hebre_muslim
📌ማንቂያ!!!

#ሙቅ ውሃ "በየቦታው ስለ ማፍሰስ"


👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆


#ሸይኽ ኢብን ባዝ (ረሂመሁላህ) ተጠየቁ ፡
ሙቅ ውሃን በምናፈስበት ጊዜ #ቢስሚላህ እንላለንን፣ ይህም ጂን ቦታው ላይ ይኖራል ብሎ በመፍራት ነው !

መልስ፡-

"አዎን! 👉 #ቢስሚላህ ይበል ምን አልባት ቦታው ላይ ጂን ካለ እንዲነቃ ለማድረግ ነው

" ከዛም ሽይኹ እንዲህ አሉ" በርግጥም #በአንድ ወቅት አንድን ሰው ጂን ይዞት በሚቀራበት ቦታ ተገኝቼ ነበር ።

#ሩቃ የሚያደርገው ሰው በሰውየው ላይ ለተደበቀው ጂኒ "ለምን ያዝከው "አለው
#ጂንውም "የሞቀ ውሃ በአንዱ ልጄ ላይ ደፋና ገደለው "አለ

#የሚቀራው ሰውዬ ደግሞ "እሱ ልጅህ በቦታው መኖሩን ስላላወቀ ነው" አለው

#ጂኒው ደግሞ "ለምን ቢስሚላህ አይልም ነበር እንዲያሳውቀው(እንዲያነቃው)"

#ሽይኽ ዘይድ አል መድኸሊ (ረሂምሁሏህ) እንዲህ አሉ ፡-

"ለማንኛውም የሞቀ ውሃ በፍሳሽ ትቦዎችም ይሁን በመሬት ላይ አይደፋም ምክንያቱም መሬት በነዋሪዎች የተሞላች ነች!!

ምናልባትም #በጂኖች አለም ወይም #በትንንሽ ፍጡሮች ላይ ያርፋል በዚህም ለበቀል ይነሳሱና ይይዙታል።

📌ስለዚህ አንድ ሰው #የሞቀን ውሃ መድፋት ከፈለገ #በቀዝቃዛ ውሃ ቅዝቃዘው የማያስቸግር እስኪሆን ያብርደው ከዛም ከፈለገ የፍሳሽ ትቦዎች ውስጥ ፣ ከፈለገ መሬት ላይ ያፍሠው" ንግግራቸው እዚህ ጋር አለቀ ረሂመሁሏህ!
፟፟======================================================
#ጉዳዩ አደገኛ ነው ሙስሊሞች ሆይ ነቃ በሉ ለወንድሞቻችሁ ለእህቶቻችሁ ለእናቶቻችሁ አድርሱላቸው ስንትና ስንት እህቶች በዚህ ሰበብ ችግር ውስጥ ይገባሉ !

https://www.tg-me.com/hebre_muslim
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
رَبِّ اجْعَلْنِي مُقِيمَ الصَّلَاةِ وَمِن ذُرِّيَّتِي ۚ رَبَّنَا وَتَقَبَّلْ دُعَاءِ

«ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ፤

رَبَّنَا اغْفِرْ لِي وَلِوَالِدَيَّ وَلِلْمُؤْمِنِينَ يَوْمَ يَقُومُ الْحِسَابُ

«ጌታችን ሆይ! ለእኔም ለወላቼም ለምእመናንም ሁሉ ምርመራ በሚደረግበት ቀን ማር፡፡»
🌙 እንኳን ለ1443 ዓ.ሒ ረመዳን አደረሳችሁ


T.me/hebre_muslim
2024/06/26 04:21:59
Back to Top
HTML Embed Code: