Telegram Web Link
📌 እግር ኳስ ጨዋታ ማየት⁉️
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች
♻️ :

📌ጥያቄ📌
📌 ኳስ ጨዋታ #በTv መከታተል እንደ ሸርዓ እንዴት ይታያል⁉️

መልስ
እግር ኳስ ጨዋታን #ማየትና መከታተል የሚከተሉት #መጥፎ ነገራቶች ስለሚገኙበት ብዙ ኡለሞች #የተከለከለ ነው ይላሉ ምክንያቱም ወደ መጥፎ ነገር #የሚያዳርሰው ነገር ራሱ ሀራም ነውና። ከነዚህም መጥፎ ነገራቶች መካከል:—

አብዛኛው ጨዋታ #በቁማር የሚካሄድ መሆኑ ፣
የአብዛኞቹ ተጨዋቾች #ሀፍረት ገላ የተገለጠና በጨዋታም ውስጥ #የሚገለጥ መሆኑ ፣
በዳኝነትም ይሁን በተመልካችነት ወንድና ሴቶች #የሚቀላቀሉበት መሆኑና፣
#የሙዚቃ መሳሪያዎች ያለው መሆኑ ሀራም ያደርገዋል።

♻️ ምንጭ :— 📚የሳዑዲ የዒልም ጥናትና የፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ ፣ 15/238 ፣ 📚ኢብኑ ኡሰይሚን ፣ ፈታዊል ኢስላሚያህ ፣ 4/431

◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
🖋
✒️https://www.tg-me.com/hebre_muslim
ለነገሮች በጣም የምትጓጓ ከሆነ ያ ነገር እንዳይሳካ መንገድ እየከፈትክ ነው፤ ቢሳካ ራሱ እንደጠበከው አትደሰትም። በጓጓህ ቁጥር አይምሮህ ውስጥ የዛ ነገር ምስል አለመጠን ይገዝፍና የተግባር ሰው መሆን ይከብድሀል።

ለህይወት ጣዕም እንድታጣ ያደረገህ መጓጓት ነው፤ አሁንም እየጓጓህ የሀሳብ ሰማይ ላይ መንሳፈፍ ካላቆምክ ብዙ ነገር ታጣለህ! ወዳጄ አጥብቀህ ፈልግ ግን አትጓጓ አለዚያ ስህተትህ በዝቶ ከመንገድ ትቀራለህ!

@abduljilal
https://www.tg-me.com/hebre_muslim
📌ሙስሊም ሴት ልጅ ሜክአፕ መስራት ትችላለችን? መሠራትስ⁉️

በመጀመሪያ ደረጃ #ሜክአፕ መሰራት #ቆዳን የማይጎዳና #ለባልና ለዘመዶች እንጂ አጂነቢ ወንዶች❗️ ፊት እስካልሆነ ድርሰ የሚከለከል አይሆንም። ሴት ልጅ አደባባይ ይዛው አትውጣ እንጂ ማንኛውንም #የመዋቦያ ነገር መጠቀም ትችላለች።

ከዚህ በመነሳት ሜክአፕ መስራትም ከዚህ ውስጥ ይገባል። ማለቴ የምትሰራው ልጅ #አጂነቢ ወንድ ፊት ልታሳየው እንደሆን #እስካላወቀች ድረስ ብትስራ አትከለከልም። ከዚህም በላይ ለምንድን ነው የምትሰሪው ብላ #መጠየቅም ግዴታ አይሆንባትም። ነገር ግን #ከራሷ መጥቶ ለአጂነቢ ነው ምናምን ብላ ከነገረቻት መስራት አትችልም፣ ምክንያቱም በመጥፎ ነገር ላይ #መተባበር ነውና።

♻️ ምንጭ :— 📚 ኢብኑ ዑሰይሚን
@hebre_muslim
አመለካከትህ፣ በራስ መተማመንህ፣ የጊዜ አጠቃቀምህ፣ የገንዘብ አያያዝህ፣ ለራስህ የምትሰጠው ቦታ፣ አላማህን ማወቅና በእቅድ መመራት ስትጀምር ብዙ ለውጥ ታያለህ!

ራስህ ላይ ስትሰራ እመነኝ ወዳጄ ኪስህ የሚገባው ገንዘብ፣ የፍቅር ግንኙነትህ ወይ የቤተሰብ ግነኙነትህ፣ መንፈሳዊ ህይወትህና በዙሪያህ ያሉ ነገሮች በሙሉ ይቀየራሉ! ህይወትህ የሚለወጠው አንተ ስትለወጥ ብቻ ነው! አስተውል ይህ የሚሆነው በ አላህ እገዛ ነው

@hebre_muslim
🙂ደስተኛ መሆን ከፈለግክ ነገን አጠብቅ ብር ሳገኝ ፣ ሳገባ ፣ ዲግሪ ስይዝ ፣ ስራ ስይዝ ብቻ የሆነ ነገር ሳገኝ አትበል ደስታ የምታገኘው ሳይሆን የምትሆነው ነገር ነው ። ደስተኛ ለመሆን ደግሞ ቁልፉ ነገር ያጣኸውን ወይ የሌለህን ነገር ሳይሆን ያለህን ነገር አይተህ ማመስገን ነው። @abduljilal
public poll

አልኸምዱሊላህ🙏 – 11
👍👍👍👍👍👍👍 69%
Ismail, @Alamduilih, ABDU, 🌹إِنَّ مَعَ ٱلْعُسْرِ يُسْرًۭا…, @ROMI_MAN_3335_J, لاتحزن أن الله معنا, @the_anuu, Amuci, Siham Yusuf, @Aditiya7, @hasan1516171

ምስጋና ለ አለማቱ ጊታ – 5
👍👍👍 31%
@Alehamdulill, مكي.يمر, @robdumf, Endu, @UMU_JANNAH

👥 16 people voted so far.
🧠ራሴን ለመለወጥ ብዙ እየለፋው ነው ግን እስካሁን ውጤት አላየውም የምንል ከሆነ ይሄን ማወቅ አለብን፤ ለውጥ ሂደት ነው! ጊዜ ይፈጃል ባንዴ ተለውጦ በዙሪያው ያሉትን ሰዎች ለማስገረም የሚጥር ሰው አንድ ድንጋይ ወርውሮ የሾላ ፍሬ ለማርገፍ ከሚጥር የዋህ ሰው በምንም አይለይም። ታገስ! ካልታገስክ ለውጡን አታየውም 𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐔𝐬 @hebre_muslim🧠ራሴን ለመለወጥ ብዙ
public poll

ኢን'ሻ-አላህ 👍 – 19
👍👍👍👍👍👍👍 83%
@IBNUAMAAN, @Zulfaye, Haki, ሀስቢየላህ, @Neharrr, Musa Zeynu, @u_add, Bint Jemal, Jemil, @abduljilal, Nejat, @UMU_JANNAH, 0927608364, Abdulkadir, @the_anuu, @ahadu_gifti, Musa.temam, Ssssss, @hasan1516171

💪መርኸባ – 4
👍 17%
@Alamduilih, @YUFE17, Siham Yusuf, @Aishtu_0

👥 23 people voted so far.
ታላቁ ሶሀቢይ ኢብኑ መስዑድ እንዲህ አሉ :
" በሁለቱ መድሀኒቶች ላይ አደራችሁን (አጥብቃችሁ ያዟቸው) : እነሱም #ቁርኣንና_ማር ናቸው።"
እንዲህም ይል ነበር :
"#ማር ከሁሉም አካላዊ በሽታ መድሀኒት ሲሆን #ቁርኣን ደግሞ በልቦች ውስጥ ላለ በሽታ ሁሉ መድሀኒት ነው።"
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈

የtelegram ቻናላችንን :👇ይቀላቀሉን
https://www.tg-me.com/hebre_muslim
https://www.tg-me.com/hebre_muslim
📌ሀይድ ላይ ያለች ሴት ቁርአን መቅራቷ⁉️
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች

📌ጥያቄ📌
📌 #ሀይድ ላይ ያለች ሴት #ቁርአን መቅራት ትችላለችን⁉️

መልስ
በዚህ ጉዳይ ላይ ዑለሞች መካከል ልዩነት ቢኖርም #አመዛኙና_በላጩ ግን #ሀይድም ላይ ይሁን #ኒፋሳ (የወሊድ ደም) ላይ ያለች ሴት እንደማንኛውም ሰው ቁርአን #መንካት ባይፈቀድላትም ቁርአን በቃሏ #መቅራት ትችላለች። ቁርአን መቅራት እንደሌለባት የሚያመለክተው #ሀዲስ በጣም #ዶዒፍ ነው።

📌 #የጀነበ ሰው በቃሉም ቢሆን መቅራት መከልከሉ የሚቆይበት ጊዜና ለመታጠብ የሚቆየው ወቅት #አጭር ስለሆነ ነው፣ #ሀይድና ኒፋሳ ግን #ብዙ ጊዜ ስለሚቆይ ያን ሁሉ ጊዜ በቃል እንኳን ከቁርአን #እንድትርቅ ማድረግ ይሆናልና በጀናባ ቂያስ አድርጎ #ማመሳሰል አይቻልም።

♻️ ምንጭ :— 📚ኢብኑ ባዝ ረሂመሁሏህ ፣ ኑሩን ዓለደርብ በሬድዬ የፈትዋ ፕሮግራም
@abduljilal
https://www.tg-me.com/hebre_muslim
📌በሀይድ ወቅት ጀናባ መሆን⁉️
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች

📌ጥያቄ
📌#ሀይድ ላይ ያለች ሴት #ብትጀንብ ወዲያው መተጠብ ግዴታ አለባት ወይስ ሀይዷን #ስትጨርስ ነው⁉️ አስተታጠቡስ መጀመሪያ የትኛውን ነው የምትታጠበው⁉️

መልስ
የጀነበችው ሀይድ ላይ #እያለችም ይሁን ሀይድ ከማየቷም #በፊት ጀንባ ከዛ ሳትታጠብ ሀይድ ብታይም መታጠብ ያለባት ሀይዷን #ስትጨርስ ነው፣ ለሁለቱም #አንድላይ ነው የምትታጠበው፣ ለዚህም ደግሞ ሁለቱንም #አብራ መነየት ትችላለች። ካልሆነም አንድኛውንም ብትነይት ለሁለቱም #ያብቃቃላታል። ለምሳሌ ለሀይድ ብላ ብትታጠብ ጀናባውም አብሮ ይወርዳል።

♻️ ምንጭ :— 📚 ኢማሙ ሻፊዒይ፣ ኪታቡል ኡም፣ 📚 ኢብኑ ቅዳማ፣ ኪታቡል ሙግኒ
@abduljilal
https://www.tg-me.com/hebre_muslim
📌ረመዷን መች ነው⁉️
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች
♻️

📌ጥያቄ📌
📌 ብዙ ጊዜ በየማህበራዊ ሚዲያው የሚተላለፍ አንድ ሀዲስ አለ ፣ እሱም ረመዷን መች እንደሆነ #ለመጀመሪያ ጊዜ ለወንድሙ የተናገረ #እሳት ከሱ ሀራም ትሆንበታለች ይላልና ይህ ሀዲስ ትክክለኛነቱ እንዴት ነው⁉️

መልስ
ይህ ሀዲስ #በየትኛውን የሀዲስ ኪታብ ላይ በጭራሽ ሊገኝ #ይቅርና በተቀጠፋ ሀዲሶች መዝገብ ውስጥ እንኳን #የማይገኝ በነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ላይ #የተቀጠፈ ሀዲስ ነው።ይህን ሀዲስ በየትኛውም መልኩ #ማሰራጨትም ሆነ #ማስተላለፍ የተከለከለ ነው።

♻️ ምንጭ: ኢማሙ ሲዩጢይ ፣ ተድሪቡ ራዊ (1/ 327)

◈•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•◈
🖋
✒️https://www.tg-me.com/hebre_muslim
ከየት እንደመጣ እንኳን በቅጡ የማታውቀውን ጉልበት እና ጥንካሬ ማግኘት ከፈለግክ ልብህን ንፁህ አድርገው ክፋት ፣ ተንኮል ፣ ምቀኝነት ፣ ሀሜትን አራግፈህ በፍቅር ፣ በደስታ እና በትሁትነት ልብህን ሙላ ያኔ ቢሰራ ቢሰራ ለደቂቃ እንኳን ድካም የማይሰማው ሰው ትሆናለህ። ሀሳብ እንጂ ስራ አያደክምም ➤ @abduljilal
public poll

በትክክል – 8
👍👍👍👍👍👍👍 73%
@Halumi17, @u_add, Sssss, Nasser, ለሁሉም ነገር አልሀምዱሊላ ያረቢ አተው ሶብርስጠኚ, ያርቢ የቤተስቦችን ነገር አደራያኢላሂ, S, الحمد لله على كل حال

እሺ 👍👍👍👍 – 3
👍👍👍 27%
@JIRACHISAANRABBI, @the_anuu, Umu Hayider

👥 11 people voted so far.
📌 ለመተጫጨት ፎቶ መላላክ ⁉️
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች
♻️

📌ጥያቄ📌
📌 ለመተጫጨት ተብሎ መልካቸውን ቀድሞ #ለመተያየት ሲባል በአካል መገናኘት ካልቻሉ በፌስቡክም ሆነ በዋትሳብ #ፎቷቸውን ቢላላኩ እንዴት ይታያል⁉️

መልስ
ምንም ያክል #ፎቶ_ሀራም ቢሆንም ማጨት የሚፈልግ ወንድም ሆነ ሴት የሚያጩትን ሰው #በአካል በማግኘት #ፊቱንና_እጁን እንዲሁም ብዙ ጉዜ የሚታየውን የሰውነት አካል ማየት ይችላሉ። ነገር ግን በአካል መገናኘት ባይችሉና መልካቸውን መተያየት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘና የሚከተሉት መስፈርቶች ከተሟሉ ፎቶዋን መላክ ትችላለች ፣ እሱም እንደዛው: እነሱም:

1⃣ የምትልክለት ሰው መልካን ካየ በኃላ ከተመቸቺው ለማግባት #ቁርጠኛ የሆነ አቋም #ያለው እንጅ ዝም ብሎ #ያቺንም_ያቺንም የሚያማርጥ መሆን የለበትም። ይህን ማረጋገጥ አለባት። እንዲሁ ለጠየቃት #ሁሉ መስጠት የለባትም። እሷን ለማግባት ቁርጠኛ አቋም ያለው መሆን አለበት።

2⃣ የምትልክለት #ፎቶ ከፊቷና ከእጇ እንዲሁም በአብዛህኛው ግልፅ ከሚሆነው ሰውነት አካሏ #ውጭ ያለውን ሰውነታን የሚያሳይ ፎቶ መሆን #የለበትም

3⃣ ሰውዬውም #ታማኝ ሰው መሆን አለበት። አለበለዚያ ፎቶውን ከላከችለት #በኃላ ለሌላ ሰው #ሊያሰራጨውና በሷ ፎቶ ስምም #መጥፎ ነገር ሊሰራበት ይችላልና ለመጥፎ ነገር እንደማይጠቀመው #እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል።

4⃣ ፎቶውንም እሱ #ብቻ እንጅ ሌላ #አጂነቢ እንደማያየው መረጋገጥ አለበት። ካየው በኃላም #ሊያጠፋው ይገባል። እሱ ጋር መቀመጥ #የለበትም። ምክንያቱም አንዲትን አጂነቢ ከአንድ ጊዜ #በላይ አስፈላጊ ከሆነም ከሁለት ጊዜ በላይ መመልከት #ስለማይችል።ስለዚህ እነዚህ ካለይ ያሉት መስፈርቶች ካልተሟሉ #በስተቀር ፎቶን መላላክ አይፈቀድም።

♻️ ምንጭ :— 📚ኢብኑ ኡሰይሚን ፣ ፈታዊል ኢስላሚያህ ፣ 3 / 128
_______________
© @abduljilal
*ያለፈዎትን ፈትዋዎች ለመከታተል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/hebre_muslim
⚠️👉ጥቆማ👈⚠️
_______________
በውስጥ መስመር የፈትዋ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ለምትሳተፋ የቻናሉ አባላት በሙሉ:—

⭕️ የምትጠይቋቸው ጥያቄዎች አጭር ፣ ግልፅና #ያልተንዛዙ ቢሆኑ ይመረጣል፣

⭕️ መፃፍ #የማትችሉ ወይም በፅሁፍ መግለፅና ማብራራት #የሚያስቸግር ጥያቄ ያላችሁ ካልሆነ በስተቀር በፅሁፍ እንጅ በድምፅ #ሪከርድ አድርጋችሁ ባትልኩ ተመራጭ ነው (በተለይ #ሴቶች) ፣

⭕️ ለጠየቃችሁት ጥያቄ ወዲያው በፍጥነት ምላሽ ባለመስጠታችን በቅድሚያ በአላህ ስም #ይቅርታ እየጠየቅን ፣ የጥያቄያችሁ መልስ ከሚዘገይባቸው #ምክንያቶች መካከል:
ከሌሎች ተሳታፊዎች ለሚጠየቁ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት #ቢዚ በመሆን፣
ጥያቄው የቀረበላቸው #ኡስታዞችን ምላሽ በመጠበቅ፣
ለሚመለሱት ምላሾች #ታማኝነት ይበልጥ ይጨምር ዘንዳ የኪታብ #ምንጮችን በማፈላለግ ቢዚ በመሆንና በመሳሰሉት ምክንያቶች መሆኑን ተረድታችሁ #በትእግስት እንድትጠብቁ እየጠየቅን በተቻለ ፍጥነት ምላሽ ለመስጠት ጥረት እናደርጋለን፣

⭕️ የተወሰኑት እንጅ ሁሉም የጠየቃችኃቸው ጥያቄዎች በሙሉ #በዒልም_ካዝና ቻናል ላይ ከማይለቀቁበት ምክንያቶች መካከል:
ከዚህ በፊት የተለቀቁ #ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ሆነው ሲገኙ ፣
የጥያቄው ይዘት #በአደባባይ ወይም ለሁሉም ሰው መቅረብ የሌለበት መሆኑ ሲታመን ፣
በቻናሉ ቢለቀቅ ከጥቅሙ ይልቅ #ጉዳቱ ያመዝናል ተብሎ ሲታመን ፣ እና በመሳሰሉት ምክንያቶች በአንዱ ወይም ከዛ በላይ ባሉ ምክንያቶች መሆኑን እንድትገነዘቡ ስንል እናሳስባለን።
__________________
© አብዱ
® የ ህብረ ሙስሊም ቻናል መስራችና አድሚን
©@abduljilal
®https://www.tg-me.com/hebre_muslim
ፈጣሪ ሆይ 'መቀየር የማልችላቸውን ነገሮች እንድቀበል እርዳኝ፤ መቀየር የምችላቸውን እንድቀይር ድፍረቱን ስጠኝ ከሁሉ በፊት ግን ሁለቱን መለየት እንድችል ማስተዋሉን ስጠኝ።' እርካታ የሞላው ህይወት ለመኖር ወሳኝ ዱዐ ነው
ኢንሻ አላህ

@hebre_muslim
📌 ደም መለገስ በኢስላም⁉️
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች

📌ጥያቄ📌
📌 ደም መለገስ በኢስላም እንዴት ይታያል⁉️

መልስ
ደም መለገስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን #መስፈርቶች ካሟላ ችግር የለውም ፣ ይቻላል። እነሱም:—

1⃣ ደሙን የሚለግሰው ሰው ደሙን በመለገሱ ምክንያት #የሚጎዳ እና #የሚታመም አለመሆኑ መረጋገጥ አለበት። ምክንያቱም #ራስን መጉዳት በሸሪዓችን ስለማይፈቀድ ፣

2⃣ ደሙ የሚለገስለት አካል ህይወቱ ወይም ህመሙ በደሙ ላይ #የተመረኮዘ ከሆነና ይህን ደም ካልተጠቀመ #የሚሞት ወይም የከፋ ጉዳት #የሚያስከትልበት ከሆነ ፣

3⃣ ደሙን ከለጋሹ አካል የሚያወጣው ዶክተር ከተቻለ #ሙስሊም ዶክተር ካልተቻለ ደግሞ ካፊርም ቢሆን ብቻ #ታማኝና ደሙን ለሌላ አላማ አይጠቀመውም ተብሎ የሚታሰብ #ዶክተር ከሆነ ችግር የለውም። ይፈቀዳል።

♻️ ምንጭ :— 📚ሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ኢብራሂም ፣ መጅሙዑል ፈታዊ ፣ 📚ኢብኑ ባዝ ፣ መጅሙዑል ፈታዊ
______________
© @abduljilal
*ያለፈዎትን ፈትዋዎች ለመከታተል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@hebre_muslim
#ያንተ_ለውጥ_በአጭር_ጊዜ_ሰዎችን_ሁሉ_እንዲያስገርም_አጠብቅ፤ እውነተኛ ለውጥ ጊዜ ይጠይቃል፣ የማይቆም ጥረት ይጠይቃል፣ ያንተን ትዕግስት ይጠይቃል፤ ፍራንክ ኦሽን "ድምፅህን አጥፍተህ ጠንክረህ ስትሰራ ስኬትህ በራሱ ጊዜ ጮሆ ይናገራል" ይለናል። ወዳጄ በትዕግሥት ተሞልተህ ለውጥህን ቀጥል!

@hebre_muslim
#በህይወታችን ሁሌም እኛ የፈለግነውን ለማግኘት ስንል እንጥራለን አላህን እንለምናለን ግን ሳይሳካልን ይቀራል ከዛም አላህ እኔን እረስቶኛል ወደሚል ድምዳሜ እንደርሳለን ወዳጄ እውነታው ግን እሱ አይደለም ፈጣሪ አንተ ከጠየከው በላይ ሰጦሀልና ቆም ብለህ ፈጣሪህን አመስግን

@Hebre_muslim
#እንዴ ያንተ ባይሆንማ በተኛህበት ትቀር ነበር፤ ስንቶች በተኙበት ቀሩ? ስንቶች በዚህ ለሊት ከመሬት በታች በመቃብር አደሩ? ለምን መሰለህ? ቀናቸው እንዲሆን አላህ አልፈቀደማ! እኛ ግን ተፈቅዶልናል ዛሬ የኛ ነው!
አልኸምዱሊላህ
#ዳይ_ወደ መልካም ስራ

@hebre_muslim
አረ ተው አትፍታት

ትዝ ይልሀል ያኔ ገና ስታገኛት
አንቺን ካላገባው ከንቱ ነው ሂወቴ ብለህ የነገርካት
ለማድረግ አስቤ የልጆቼ እናት
እሺ በይኝ ውዴ ልቤም ይረፍበት
አስታውስ ያንን ቀን ቃል የገባህበት
መርሀባ ብለህም ኒካህ አስረህላት
ገና ከጅምሩ ምነው ታስፈራራት
ካሉት እንስቶች መርጠህ አግብተሀት
ምነው ምን ተገኘ ተንቀባረርክባት

ያየሀቢቡና ያሉትን አልሰማህም ምርጥ ብሎ ማለት መልካም የሆነው ነው ለቤተሰቦቹ

አንተን ብላ መታ ቤቴ ቤቴ ስትል
አንተ ግን ተቀየርክ አደረካት ጣልጣል
በል አያዋጣህም ውጪ ውጪ ማየቱ
ሀላፊነት ወስደህ ቤትህን መምራቱ
ቀጥተኛው መንገድ እሱ ነው እውነቱ
አይጠቅምህም እውነት ቤትህን ማፍረሱ
ፍቺ ቢፈቀድም ተጠልቷልኮ እሱ
ፍቺ ቢፈቀድም ተጠልቷልኮ እሱ

- እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! ሴቶችን ያስገደዳችሁ ኾናችሁ ልትወርሱና ግልጽን መጥፎ ሥራ ካልሠሩ በስተቀር ከሰጣችኋቸው ከፊሉን ልትወስዱ ልታጉላሏቸውም ለእናንተ አይፈቀድም፡፡ በመልካምም ተኗኗሩዋቸው፡፡ ብትጠሉዋቸውም (ታገሱ)፡፡ አንዳችን ነገር ብትጠሉ አላህም በእርሱ ብዙ ደግ ነገርን ሊያደርግ ይቻላልና፡፡

📙 ቁርዐን 4:19

@abfuljilal
#በስራችን_ወይም_በህይወታችን_ማሳካት ምንፈልገውን ስኬት ለማሳካት ቀን ከሌሊት ከለፋን ከጣርን አንድ ቀን ስኬት በራሷ ጊዜ በራችንን ታንኳኳለች ስኬት ወደኛ እንድትመጣ አልያም እንድትሄድ ወሳኞቹ እኛው እራሳችን ነን ያላቋረጠ ጥረት በማድረግ ስኬት እስከምትመጣ እርግተኛ ሁነን እንጠብቃት 😉

@Hebre_muslim
2024/06/29 00:23:43
Back to Top
HTML Embed Code: