Telegram Web Link
✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧
#ቢላል_ኢብኑ_ረባሕ_ክፍል_ሁለት
✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧
www.tg-me.com/abdu4321

ትላንት ስለ ሐበሻ ለቢላል ታሪክ መንደርደርያ የሚሆነንን አጠቃላይ ሁኔታ በጥቂቱ አይተናል፡፡ ዛሬ ደግሞ ስለ ቢላል ወላጆች እና ቤተሰቦች ለቢላል ታሪክ መንደርደርያ እንዲሆን ጥቂት እናወጋለን፡፡ መልካም ጊዜ

#የቢላል_ኢብኑ_ረባሕ_ወላጆች
ከኢስላማዊ የትምህርት ዘርፎች መካከል #ዒልመል_አንሳብ (የዘር ሐረግ እውቀት) የሚባል ትምህርት ክፍል አለ፡፡ ይህ የትምህርት ክፍል በኢስላም ውስጥ ያለፉ ባለ ጉልህ ሚና ሰዎች የዘር ሀረግ በዋናነት የሚያጠና ሲሆን ብዙሃኑ ዓረቦች በመሆናቸው አብዛኛዎቹ የተጠኑት የዘር ሐረጎች ዓረባውያን ናቸው። ቢሆኑም የዓጀሞች አልተጠናም ማለት አይደለም፡፡ በዚህ በኩል ኢማሙና ወሙጅተሂዱ መዝሃቢና ኢማሙ ሻፊዒይ የዒልመል አንሳብ ጥልቅ እውቀት እንደነበራቸውና በዘመናቸው ያሉትን ሰዎች ሳይቀር የዘር ሐረጋቸውን ቆጥረው አባታችን አደም ድረስ ያደርሱ እንደነበር በርካታ መዛግብት አትተዋል፡፡ ይህ የእውቀት ዘርፍ ዝርያን መጠበቅ ላይ ጉልህ አስተዋፅኦ ቢያበረክትም አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል ለማለት ያስደፍራል፡፡ ይህን ያልኩት ያለ ነገር አይደለም፡፡ የታሪክ ምሁራን የበርካታ ሶሐበቶችን (ዓረቦቹን) የዘር ሐረግ እስከመጨረሻው ሲቆጥሩ የሌላ ሐገር ተወላጆችና ዝርያቸው #ሄማውያንና #ያፌታውያን የሆኑትን ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ሳያስቀምጡ ቀርተዋል፡፡ ታድያ ይህ ከቢላል ጋር ምን አገናኘው ካላችሁ የቢላል የዘር ሐረግ ከአባታቸው ጀምሮ ውዝግብ የፈጠረና ከአያታቸው በላይ ያለው ደግሞ ምንም አይነት ተጨባጭ መረጃ የሌለው ማለትም የዚህ የዕውቀት ዘርፍ ብርሃን የቢላል ሐረግ ላይ አለማብራቱ ያገናኘዋል እላችኋለሁ፡፡ የቢላል ወላጅ አባት #ረባሕ በሌላ ዘገባ #አቢ_ረባሕ የቢላል ወላጅ እናት ደግሞ #ሐማማ ትባላለች፡፡ ቢላል አንዳንድ ጊዜ #ኢብኑ_ሐማማ ተብሎ በእናቱ ይጠራ እንደነበር የሚጠቁሙ መረጃዎች ቢኖሩም ስለምን በእናቱ ይጠራ እንደነበር የተገለፀ ነገር ግን የለም፡፡ የቢላል ወላጆች ከሐበሻ ተነስተው እንዴት ሒጃዝ ውስጥ መኖር እንደጀመሩና በምን ምክንያት ወደ ባርነት እንደገቡ ተጨባጭ መረጃ ባይኖርም አንዳንዶች ደከም ባለ መረጃ ተመርኩዘው የቢላል ወላጆች ከመአከላዊ ሐበሻ በአክሱሙ ጠቅላይ ነጋሽ ስር ሆኖ የመንን ያስተዳድር ወደነበረው ነጋሽ (ንጉስ) አብረሃ የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት ተጉዘው በኋላም በንጉሱ በምግብ አብሳይነት ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ ነፃ ሰዎች ነበሩ ይላሉ፡፡ ከዚያም አብረሃ ካዕባን ለማፍረስ ወደ መካ ባቀና ጊዜ አብረው ተጉዘው ከአዕዋፉ ጥቃት ከተረፉትና በቁረይሾች ተማርከው ባርያ ከሆኑት ሐበሾች ውስጥ ሆኑ ብለው ያክላሉ፡፡ በዚህም ባልና ሚስቱ ከበኑ ከዕብ ከሚመዘዘው #የበኑ_ጁመሕ ጎሳ አባላት የሆኑ ሰዎች ዘንድ ተማርከው በባርነት ገቡ ብለው ያትታሉ፡፡ ቀድሜ እንዳልኩት ይህ ታሪክ መረጃው በጣም ደካማ ነው፡፡ መላው የታሪክ ፀሃፊያን ግን የቢላል ወላጆች የዛን ግዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኖሩት ሳባውያን ዘር የተገኙ እንደሆኑ በአንድ ድምፅ ያረጋግጣሉ፡፡ ስለሆነም ቢላል የተወለደበት ቦታ ሌላኛው ውዝግብ የተፈጠረበት ጉዳይ ቢሆንም ዘሩ ግን ሐበሻዊ መሆኑ አጠራጣሪ ወይም አወዛጋቢ አይደለም ልል እወዳለሁ፡፡

#ይቀጥላል...............
---------------------------------------------------
በዚህ ቻናል👇
✔ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
✔ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
✔ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
✔ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።

ለመቀላቀል ይህን ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇

www.tg-me.com/abdu4321
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ሟር ሟር

✍@abdi_tube_3_bot
አላህ ሆይ!..

ማንነቴን አስታውሰኝና ወዳንተ አዙረኝ።  ከኔነቴ ነቅለህ ወዳንተነትህ አቅርበኝ። ድክመቴን አሳውቀኝና በልቅናህ ባዶነቴን ሙላው!!!

:¨·.·¨: ❀
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
https://www.tg-me.com/abuki4321

┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
አላህ ሆይ!..

፨ ስላለፈው ጉድለታችን ሁሉ ማረን፣
፨ የቀረውን አሳምርልን፣
፨ ዉዴታህን፣ ምህረትህን፣ ጀነትህን አትንፈገን።

#ያማረ_ጁሙዓ ይሁንላችሁ😍❤
:¨·.·¨: ❀
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
https://www.tg-me.com/abdu43211

┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
▷ኢብኑ ተይሚያ ስለ ኒቃብ ግዴታነት ሲናገሩ እንዲህ አሉ፦ ሴት ልጅ ፊቱዋን እና እጆችዋን እንዲሁም እግሮችዋን ፈፅሞ ለአጅነቢ(ለባዕድ ወንድ)ልትገልጥ አይገባም (ልትሸፈን ይገባል)።
➛አል ፈታዋ 114-22
▮
ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ እንድህ ይላሉ ፦ ሴቶች ላይ ኒቃብ መልበስ ዋጂብ (ግዴታ) ነው ።
ምንጭ፦ ( ፈትዋ ኑሩን አለ ደርብ )
​​"ሀፍሲ"
ክፍል አንድ
ፀሐፊ፦ ኑዕማን ኢድሪስ

... "አብዛኞቹ ወጣቶች ለራሳቸዉ ያላቸዉ አመለካከት የወደቀ ከመሆኑ የተነሳ የዘቀጠ የህይወት እርከኖች ለማሳለፍ ተገደዋል። ... " የዐመሉን ሷሊህ ጀመዓ ሀላፊ የሆነዉ ወጣት ኡስማን ጀመዓዉ በሚያደርገዉ ወርሀዊ ሹራ ላይ በቁጭት እየተናገረ ነዉ። ጀመዓዉ ምንም እንኳ በአምስት አባላቶች የሚንቀሳቀስ ማህበር ቢሆንም ብዙ ወጣቶችን ከሱሰኝነት አላቋል። በእድሜ የገፉ አረጋዉያንን መርዳትና የደሰሰ ጎጇቸዉን መጠገን የወጣቶቹ የእለት ተእለት ተግባር ነዉ። ኡስማን የጀመዓዉ መስራችና አሚር ነዉ። ሁሉም ያከብሩታቱት ይታዘዙታል፤ በጀመዓዉ የሚሰሩ ስራዎቹ ሁሉ የሱ የመጨረሻ ዉስኔዎች የተላለፉበት ናቸዉ። ንግግሩን ቀጥሏል "... ወጣትነት ትልቅ ፈተና ነዉ። እኛን አላህ ጠብቆን እንጂ ምናልባትም ከሱሰኞቹና አልባሌ ቦታ ከሚዉሉት ልንሆን እንችል ነበር አልሐምዱሊላህ ስለዚህ መስራት አለብን ከመጥፎ ነገር ጠባቂዉ አላህ ቢሆንም እኛ ሰበብ ልንሆን ግድ ይለናል። ደግሞ እንችላለን! (በቁጭት) የምትጨምሩት ሀሳብ ካለ ..." አለና ሁሉንም በአይኑ ቃኘ። "ሀፍሲ ሀሳብ አለሽ?" ብሎ የጀመዓዉ ገንዘብ ያዥ የሆነችዉን ሀፍሷን ተመለከተ። ሀፍሷ እጅግ በጣም ዉብና በሁሉም ሰዎች ተወዳጅ የሆነች ልጅ ናት። ወንዶች በዉበቷ ይፈዙባታል። በዚህ አመት የማግባት እቅድ የሌለዉ ወጣት እሷን ሲመለከት ዛሬዉኑ ካላገባኃት ብሎ ሀሳቡን ይቀይራል፤ ያገባም ቢሆን ለሁለተኝነት ይመኛታል። ሁለተኛ የማግባት አቅሙ ከሌለዉ ደግሞ ወይኔ ባላገባሁ ብሎ ይቆጫል። ቆንጆ መባል ብቻ አይገልጻትም። ሴቶች በአለባበሷ ይቀኑባታል። እሷ የለበሰችዉን አይነት ልብስ ፈልገዉ ይገዛሉ እንደሷ ግን አያምርባቸዉም። "ዋናዉ ከመስቀያዉ ነዉ" ይባል የለ። ልብሱ የሷ ድምቀት ሳይሆን እሷ ለልብሱ ዉበትና ድምቀት ነች።

... ሀፍሷ በኡስማን የቁጭት ንግግር ተመስጣ ነበር። አስተያየት የመስጠትም ሀሳብ ሆነ በሱ ሀሳብ ላይ የምትጨምረዉ ሀሳብ አልነበራትም። ነገር ግን የተሰጣትን እድል ለመጠቀም ያክል "ቢስሚላህ ..." ብላ ንግግሯን ጀመረች "... ኡስማን በሰጠዉ ሀሳብ ሁሉ እስማማለሁ። መስራት እንዳለብን ይሰማኛል። ከአንችልም መንፈስ ወጥተን እንችላለንን ማንገብ አለብን። እኛ ወጣቶችን በአስተሳሰብ እንቀይራለን ብለን እስከተሰባሰብን ድረስ ራሳችንን ቀይረን ለስራ እንነሳሳ፤ ለተቸገሩና ለአረገዉያኖች ደግሞ ስጡ የተባልነዉ ከሰጪዎች ተቀብለን እንድረስላቸዉ። ... በዚህ ወር እንሰራለን ብለን ያቀድናቸዉን ስራዎች ለመስራት ሁላችንም ወደስራ እንግባ። አላህ ይገዘን።" ብላ ንግግሯን ቋጨች። ኡስማንና ሙቤ ትኩር ብለዉ በተመስጦ እያዮዋት ፈዘዉ ነበር። ነገሩ ወንዶቹ እነሱ ብቻ ሆኖ እንጂ በሚሊኒየም አዳራሽ ሙሉ አስር ሺ ወንዶችን ሰብስበን እሷ መድረክ ላይ ወጥታ ንግግር ብታደርግ ሁሉም በንግግሯ ይመሰጡ ነበር። ሀፍሲ ዉበቷ ብቻ ሳይሆን አንደበቷ ይማርካል። ...ከአምስቱ አባላቶች ዉስጥ ሳሪና ሙቤ የሀፍሲ ጓደኞች ሲሆኑ፤ ነኢማ ደግሞ በኡስማን በኩል የተገኘች የጀመዓዉ አባል ናት።
.
... "ኢንሻ አላህ በቀጣይ ወር ሹራ እስክንገናኝ ሁላችንም የተሰጠንን ስራ በአግባቡ እንስራ። ሳሪ ደግሞ የጀመዓዉ አባል ሆኖ ለመስራት የተስማማዉን ጓደኛሽን ቀጣዩ ሹራ ላይ እንዲገኝ ይዘሽዉ ነይ! ማን ነበር ስሙ?" ብሎ ሳሪን ጠየቃት "ዴቭ" አለችዉ። "ኢንሻ አላህ በቀጣይ ወር ዴቭና ሸኽ አጃኢቡን ጨምረን ሰባት ሁነን የምነሰባሰብ ይሆል። የዛሬዉን ሹራ በዚህ ጨርሰናል" አለ። (ሸኽ አጃኢቡ የጀመዓዉ አማካሪ፤ ለጀመዓዉ አባላት ደግሞ መካሪ አባት ናቸዉ)

... ሁሉም ከቢሮዉ በመዉጣት ላይ እንዳሉ ዑስማን ከተቀመጠበት ተነስቶ "ሀፍሲ" ብሎ ተጣራ። ሀፍሲ ወደኃላ ዘወር ስትል ወደ ወንበሮቹ ተመልሳ እንድትቀመጥ በእጁ ጋበዛት። "ሳሪ ዉጭ ጠብቂኝ" ብላ ወደ ዉስጥ ተመለሰች።
.
... አንገቱን እንደማቀርቀር አደረገና ፀጉሩን በእጆቹ እያሻሸ "ሀፍሲ ምናልባት እንደሌሎቹ ወንዶች ቃላትን አሽሞንሙኜ ዉበትሽን ላላደንቅ እችላለሁ። ነገር ግን አንድ ጥያቄ ነዉ የጠየቅኩሽ ሳትመልሽልኝ ሶስት ወር አለፈሽ። አሉታዊም ይሁን አዎንታዊ ምላሽሽን በጉጉት እየጠበቅኩ ነዉ። ... ሀፍሲ ላገባሽ እፈልጋለሁ። ታገቢኛለሽ?" ብሎ ጠየቃት.......


#ክፍል_ሁለት...⓶ ይቀጥላል

@abdu43211
♥️ ንፁህ የሆነ ትዳር :
ውበቱ ሀብት ሳይሆን
በዲን ላይ የፀናው ፍቅር ነው!

@abdu43211
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 1 month. If it remains inactive in the next 7 days, that account will self-destruct and this channel will no longer have an owner.
Forwarded from Al_Faaruuq_bot
ይህን ምርጥ ቻናል እንደምትወዱት እርግጠኛ ነኝ በቅርቡ ተከፍቶ ተወዳጅነት ያተረፈው ቻናል ነው እናንተም ተጠቀሙበት
♻️በዚህ ቻናል የሚተላለፉ የፅሁፍ አይነቶች;— ♻️
① ወደ አማረኛ የተተረጎሙ አጫጭር ፈትዋዎች፣
② በውስጥ መስመር ለሚላኩ ዲናዊ ጥያቄዎች የተሰጡ የኡለሞች ምላሾች፣
③ እጥር ምጥን ያሉ የቀደምት ኡለሞች ድንቃድንቃ ንግግሮቻቸው፣
④ አዝናኝና ፈገግ የሚያደርጉ ግን ቁም ነገር አዘል አጫጭር የዑለሞች ፈትዋ
⑤ አጫጭርና ቀላል ተከታታይ የዓቂዳና የፊቅህ ፅሁፎች
➅ ከጀናዛው ማጠቢያ ክፍል ተከታታይ ደእዋ
➆ የረሱል ﷺ ጣፋጭ ሀዲሶች

✔ እና ሌሎችም ይቀርባሉ። ይከታተሉ፣ ለወንድምና እህትዎ ያስተላልፉ፣
ሰዎችን ወደ ጥሩ ነገር ያመላከተ ልክ እርሱ እንደሰራው ነው የሚቆጠርለት።"
ሀሳብና አስተያየት ካላቹህ
@Faaruuq1 አድርሱን ቻናሉን ለመቀላቀል ከታች አስገባኝ ሚለውን ጠቅ አርጉት


አስገባኝ አስገባኝ አስገባኝ
አስገባኝ አስገባኝ አስገባኝ
በጣም ተጠግተህ ብታየው ልቤን አንተ እንዳለህበት ታውቅ ነበር ታውቃለህ አላህ ከሠጠኝ መልካም ነገሮች ትልቁና ዋነኛው አንተ መሆንህን አሰብኩ በደስታ ፈገግ አልኩ አሁንም አስታወስኩት ይበልጥ አስደሠተኝ ከልቤ ሳኩ ታውቃለህ አደል ከምንም ነገራቶች በላይ የሚያሥደስተኝ ጠዋት ከእንቅልፌ ተነስቼ አንተ የኔ እነደሆንክ ማሠቡ ነው ያአላህ ታድዬ እያንዳንዱ ነገር ለአንድ ነገር ሰበብ ነው ዝናብ እነዲጥል ደመና ይኖራል አበባ እንዲያብብ ደግሞ ዝናብ ያስፈልገዋል አዬ አንተ ልክ እነደዚ ነህ ለኔ መኖር አንተ እንደምታስፈልገኝ ታውቃለህ? በሂወቴ ወሳኝ ሠዎች ስለነሡ ጥቂት ጥቂቶቹን ለመፃፍ እርሳስ አውጥቼ መፃፍ ጀመርኩ አንተጋ ስደርስ ግን በእስኪርቢቶ መፃፍ እንዳለብኝ ተሰማኝ ምክንያቱም አንተ መቼም እንደማትቀየር አውቃለሁ፡፡ [__]ታውቃለህ ምን ያህል እንደምተማመንብ ምን ጊዜም እንደምወድህ ምን ጊዜም እንደማፈቅርህ ብዙ ጊዜ አላህ ለሰዎች የተለያዩ ስጦታዎችን ያዘንብላቸዋል ግን እንደኔ ስጦታ ለማንም አላደለውም! [__] ለኔ ከስጦታዎች ሁሉም በላጩ ስጦታዬ ነህ ፍቅር ማለት መቀበል ብቻ ሳይሆን መስጠትም እንደሆነ ካንተ ተምሬያለሁ ማውራት ብቻ ሳይሆን መተግበርንም ጭምር ሁሌም በልቤ ውስጥ ትኖራለህ በጣም አፈቅርሀለሁ👸 የኔ ንጉስ🤴 ###ያንተዋ-ምጥን (____) ❤️❤️❤️❤️

✍m.L
ምርጥ እውነተኛ ና አስተማሪ ታሪክ ከባለታሪኩ ከጥታ የተስተላለፈ ታሪክ ለናተ በፅሁፍ አድረሰንላቹሀል ፀሀፊ ቢላል ነጃሺ እና ኢማን አህመድ (ኢሙ )

#በ ሀላሌን ቻናል የቀረበ
👉 ልብ አንጠልጣይ እዉነተኛ ታሪክ👈


።።።።።።።።።። ሲሀም።።።።።።።።።።።።


ክፍል አንድ

ፀሀፊ ቢላል ነጃሺ (special )



ከእንቅልፌ ላይ ሳለሁ ድምፅ ተሰማኝ በር ይንኳኳል ተነስ ቁርስ ደርሷል የሚል ነበር የተሰመኝ ድምፅ የእናቴ ነበረ
እሺ መጣሁ ብዬ ከ አልጋዬ ላይ ተነስቼ ወደ መታጠቢያ አመራሁ
ወጫው በጣም ይበርዳል ክረምትም ስለነበር ዳምኖ ገና የነጋም አይመስልም
ተጣጠብኩ ና ወደ ሳሎን ቁርሴን ለመብላት ገባሁ.....


ፋሪስ እባላለሁ የምኖረዉ አዲስ አበባ ሲሆን
ከቤተሰቦቼ ጋ ነዉ የምኖረዉ ቤት ዉስጥ ከ እኔ ጋ 7 ነን እናት ና አባቴ የቤቱ ታላቅ ዩሱፍ ይባላል ሁለተኛዉ ደግሞ ሙሀመድ ይባላል
ሶስተኛዋ ደግሞ ሪና ትባላለች የቤተሰቡ ተወዳጅና አዝናኝ ቀበጥም ነች
አራተኛ ደግሞ እኔ ነኝ
የመጨረሻዋ ሀያት ትባላለች በጣም ቆንጆ ናት በእናቴ ነዉ የወጣችዉ ከሁሉም በላይ ነዉ የምወዳት .
ያዉ ኑሮአችንም ቢሆን አባቴ የመርካቶ ነጋዴ ነዉ ምንጣፍ ነዉ የሚሸጠዉ
ታላቅ ወንድሜ ዩሱፍ ዶክተር ነው
ሙሀመድ የ ሀዋሳ ዩንቨርሲቲ የሁለተኛ አመት ተማሪ ነዉ ለረፍት መጥቶ ነዉ
ሪና ማለትም የቤቱ 3ተኛ ልጅ ከ11ኛ ክፍል ወደ 12ተኛ ተዘዋዉራለች
እኔ ደግሞ ማትሪክ ተፈታኝ ነበርኩ አሁን ዉጤት እየጠበኩኝ ነዉ ነጠር ግን አሁን ክረምት ስለሆነ አባቴን ስራ አግዘዋለሁ ዩሱፍ ግን ለምን ታሰራዋለህ የክረምት ትምህርት አታስገባዉም እያለ ከአባቴ ጋ ይጨቃጨቃሉ ...

ቁርሳችንን እየበላን ሳለ አባቴ ፋሪስ ዛሬ አንተ ነህ ሱቅ የምትከፍተዉ ከነጋ የሆነ ነገር ሸቶኝ አሞኛል ስለማልሄድ አንተ ሂድ ና ሱቅ ክፈት አለኝ
እኔም መርሀባ እሄዳለሁ አልኩ ..
ያዉ የእናት ና የአባትን ሀቅ መጠበቅ አለብን ቁርአኑም ቢሆን ከ አሏህ ሀቅ ቀጥሎ የእናትና የአባት ሀቅ ነዉ እንኳን እንቢ ኡፍ ! አትበሉአቸዉ አይደልየሚለዉ ..
እንደጨረስኩ ልብሴን ለብሼ ወደ መርካቶ ለመሄድ መንገዴን ጀመርኩ ግን ሳየዉ በጣም ዳምኖል ትንሽ እንደሄድኩኝ ዝናብ መዝነብ ጀመረ እኔ ግን ስለረፈደብኝ
መንገዴን ቀጠልኩ ድንገት ቀና ስል አንድ ልጅ ጥላ ይዛ አየሁኝ እየሮጥኩ እናት እናት
ስላት ዞር ብላ አቤት አለችኝ.... 😱 ያየሁትን ማመን አልቻልኩም ምላሴ ተሳሰረ ልቤ በጣም በፍጥነት ይመታ ጀመረ እራሴን እስከማላቅ ድረስ ምስጥ ብዬ ቀረሁ በጣም ዉብ ነበረች ፈገግተዋ ልብን ይስባል ...
እእእ ወንድም ምን ልርዳህ አለቺኝ
እእእ ... እእእ ዝናቡን ስላልቻልኩት ታስጠልይኛለሽ አልኩአት
እሺ ችግር የለዉም እንካ ጥላዉን ረጅም ስለሆንክ ያዘዉ ብላ ሰጠችኝ ተቀብዬ መራመዴን ቀጠኩ ስለሷ እያሰብኩኝ የት እንደደረስኩ ሳላቀዉ
ወዴት ነዉ የምትሄደዉ ብላ ስጠይቀኝ ከእንቅልፉ እንደነቃ እእእ እ መርካቶ ስላት የመርካቶ ታክሲ ኮ አለፍከዉ
እእ አለፍኩት እንዴ አመሰግናለሁ ብዬ ተሰናብቼአት ተመለስኩ
ታክሲ ዉስጥ እስክወርድ ድረስ ስለ እሷ ነበር የማስበዉ ወይ ጉድ ምን ነካኝ ምን ሆኜ ነዉ ሰዉ እንዴት በ አንድ ቀን በአንድ ቅፅበት ልብ ዉስጥ ገብቶ ሀሳብ ይሆናል ግራ ገባኝ ...
ወደ ሱቅ ደረስኩ እዛ ስዉል ቀኑን መሉ ስለሷ ነበር ማስበዉ ምንም ልረሳት አልቻልኩም አመሻሽ ላይ ሱቅ ዘግቼ ወደ ቤት አመራሁ ቤተሰቡን ዘይሬ እራት ቀማምሼ ወደ ክላሴ ገባሁ አሁንም ግን ከሀሳቤ ልጠፋ አልቻለችም እስከ እኩለ ለሊት እያሰብኩ በዛዉ ተኛሁ.......

አገኛት ይሆን



................... 2 ይቀጥል............

https://www.tg-me.com/abdu43211
አላህ ሆይ!..

ማንነቴን አስታውሰኝና ወዳንተ አዙረኝ።  ከኔነቴ ነቅለህ ወዳንተነትህ አቅርበኝ። ድክመቴን አሳውቀኝና በልቅናህ ባዶነቴን ሙላው!!!

:¨·.·¨: ❀
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
https://www.tg-me.com/abuki4321

┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
#ሀቢቢ! - #ሀቢብቲ

የማለዳዋ ፀሀይ ከመውጣቷ በፊት ቀንህን በአዝካር ክፈተው፡፡ በዱዓ የተከፈተ ቀን ስኬትና ድል አለው፡፡ የአላህን ቁርዓን ማንበብ ባትችል እንኳ ከፍተህ እየው፡፡ ትርጉሙን ባታውቀውም የሆነ መልእክት ያስተላልፍልሃልና፡፡

#ሰናይ_ምሽት! 🌞

@abdu4321
👉 ልብ አንጠልጠይ እዉነተኛ ታሪክ 👈


።።።።።።።። ሲሀም።።።።።።።።።።።።


ክፍል ሁለት



#በ ሀላሌ ቻናል የቀረበ




አዛን ይሰማል ነግቶ ነዉ ማለት ነዉ ወንድሜ ይጣራል ሱብሂ ደርሷል እያለኝ ነዉ ነገር ግን ዝናብ ነበር መስጂድም ለመሄድ አይመችም ተሰባስበን ከሰገድን ቡሀላ ቁርሳችንን እንደበላን አባቴ ዛሬም እንዳልተሻለዉና እኔ ሱቁን እንድከፍት ነግሮኝ ተመልሶ ገብቶ ተኛ
ያዉ በ አባቴ ህመም ብከፋም ብቻዬን በመሄዴ በጣም ነዉ ደስ ያለኝ ምክንያቱ ደግሞ የትናንትናዋ ልጅ ነበረች ከአባቴ ጋ ብሄድ በመኪና ስለምንሄድ አላገኛትም ብዬ ስላሰብኩ ነዉ


በጣሞ ደስ እያለኝ ከቤት በፍጥነት ወጥቼ የትናንትናዉ ቦታ ሄድኩ ግን አልነበረችም የቀጠርኩት ሰዉ ያለ ይመስል አይኔ ይንከራተት ነበር ወይ ጉድ ቆይ አሁን አንዴ መንገድ ላይ ያየሀዉ ሰዉ እንዴት ተመልሰህ ታየዋለህ እያልኩ ማሰብ ጀመርኩኝ በቃ ልቤን ይዛዉ ጠፋች ማለት ነዉ ቢሆንም ተስፋ አልቆረጥኩም አንድ ቀን አያት ይሆናል ብዬ መጠበቄን ቀጥያለሁ...


ጊዜ ጊዜን ሲወልድ ይሀዉ ዛሬ ማትሪክ መለቀቁን ሰማሁ .
ሁሉም የኔን ዉጤት ለማየት ጓግቶል እኔ ግን የሚያሳስበኝ ስለሷ ነበር ካየሁአት ድፍን 2 ሳምንት ሆነኝ ምን ይሻለኛል ሌላ ምንም አላስብም ነበር

ቢሆንም አልሀምዱሊላህ ማትሪክን በጥሩ ዉጤት አለፍኩኝ ግን ሁለቱ ወንድሞቼ ደስ አላላቸዉም እንደነሱ ስትሬት እንዳመጣ ነበር የሚፈልጉት በጣም ነበር የሚቆጣጠሩኝ አሁን ግን አንዱ በስራ አንዱ ደግሞ ለትምህርት ስለሄደ ቁጥጥሩ ቀንሶልኛል



ማይደርስ የለምና ትምህርት ቤት ተከፈተ እነ ሪና ትምህርት ቤት ነበር የገባሁት 11ኛ ክፍል ት/ቤቱ በጣም ትልቅ ነዉ በዛላይ የዱርዬ መሰብሰቢያም ነዉ አብዛኛዉ ደግሞ የሀብታም ልጆች ናቸዉ አንዳንዱ ደግሞ መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸዉ ናቸዉ በ ባህሪያቸዉ ቢሆን ሱሰኛ ና ፋሽን ተከታይ ናቸዉ በ አጠቃላል ት/ቤቱን አልወደድኩትም ነበር ...


ትምህርት ከጀርመን 2 ሳምንት ሆነን እንደተለመደዉ ከተማርን ቡሀላ እረፍት ሰአት እህቴ መጣ ዛሬ ልጋብዝህ አለችኝ
ምን😳 በሂወቶ አንድ ቀን ብላኝ የማታቀዉ ልጅ ምን ሆና ነዉ በዛላይ ማታ የሌለ ተጣልተን ነበር ...
እሺ ብያት በምሳ ወደ ካፍቴሪያ ስሄድ እጇን ከፍ አርጋ ና እዚ ጋ አለችኝ ከጓደኞቹአ ጋ ነበረች ከዛ ገና ሳልቀመጥ ሁሉም ወይኔ ወንድምሽ በጣም ያምራል

ደግሞ ወንድሞ መሆኔን በም አወቁ መቼስ ነግራቸዉ መሆን አለበት
ሁሉም እጃቸዉን ዘረጉ ሰላም አልልም ብል እህቴ የሆነ ነገር ትላለች ብዬ ሁሉንም ሰላም አልኩኝ
ለእህቴ ስል አሏህ የከለከለዉን ሰራሁ ወይ ሪና የማታመጣብኝ ጉድ የለም አንዷማ ይባስ ብላ ሀያት እባላለሁ ብላ ተጠመጠመችብኝ ይሄኔ ነዉ መሮጥ 🏃ሁሉም ስማቸዉን ነግረዉኝ ነበር እኔ ግን የ አንዳቸዉንም አልሰማሁም የ ሀያትንም የሰማሁት ጆሮዬ ላይ መጥታ ስለነገረችኝ ይሆናል ሁሉም በ አንድ ድምፅ ቁጭ በል አሉኝ እህቴ ኧረ ቀስ እንክብካቤ በሉ ከወንድሜ እራስ ዉረዱ አለች
ሀያት ምነዉ ወንድምሽ መኪና ነዉ እንዴ ስትል ሁሉም ሳቁ ..

ከተቀመጥኩ ቡሀላ ምግብ አዘዝን መብላት ስንጀምር እህቴ ማዉራት ጀመረች ለካ ማታ ስለተጣላን እኔን በጓደኞቹዋ ፊት ለማዋረድ ነበር አንድም ሳይቀራት እኔን የሚያሸማቅቅ ነገር ማዉራቱዋን ቀጠለች ሁሉም ይስቃሉ ወላሂ የሌለ ተናደድኩ አሁን በሰዉ ነዉር ይሳቃል እንደዛ ቀን ታግሼ አላቅም ነበር ያዉ በመታገሴ ጥሩ ነገር ላገኝ እችላለሁ አሏህም ቢሆን የታገሱትን ጥሩ ምንዳ እንዳላቸዉ ተናግሮ የለ ....


ሪና ሲሀም መጣች አለች ሀያት

እሰይ ቆይ አሷ ደግሞ ስትመጣ ታጥረገርግህ የለ አለችኝ

ደሜ ፈላ ምን አይነት ነገር ነዉ ለነገሩ ይበለኝ አሏህን የሚያስቀይም ነገር ሰርቼ ብደሰት ነበር የሚገርመኝ በጣም ተናደድኩ ቤት ዉስጥ ቀና ብላ የማታየኝ ኧረ ተዉኝ እስቲ ደግሞ ብመታት እህቱን ደበደበ ቢሉስ ብዬ እየተቃጠልኩ ዝም አልኩ ..


እናንተ ጥላችሁኝ መጣችሁ አይደል እያለች ስመጣ ሲሀም መጣች አሉ ሲሀሜ ይቅርታ እርቦን እኮ ነዉ አሉዋት ሀያት ለ ሲሀም ጠርታ አየሽዉ የ ሪና ወንድም አለቻት
እንዴ ይሄ ነዉ እያለች መሳቅ ጀመረች ሁሉም አዎ ምነዉ ሲሉዋት ዉይይ አቀዋለሁ እያለች መሳቋን ቀጠለች ..
ወይ ገድ ደሞ የት አዉቃኝ ነዉ ዉሸቶን ነዉ እንጂ እያሾፈችብኝ መስሎኝ ቀና ብዬ የት አባሽ ነዉ ደግሞ የምታቂኝ ልላት ስል የማየዉን ማመን አቃተኝ አይኔ የሚያየዉን ላምን አልቻልኩም የምናገረዉም የምሰራወም ጠፋብኝ ህልም መሰለኝ ደንዝዤ ፈዝዤ ቀረሁ..........






..................... ይቀጥላል...................
🍃ለፈገግታ🍃
ሸይኹ በሚያስተምርበት መስጂድ ውስጥ ሰዎች የሚሰጡትን ክብር እንድትመለከት ሚስቱን አስከትሎ ሄደ። በምላሷ ትወጋው ስለነበር አዛዋን ለማስቆም መሆኑ ነው።…
:
መስጂድ ውስጥ ሚንበር ላይ ቆሞ ሲያስተምር ዋለ። እቤት ሲመለሱ ሃሳቧን ጠየቃት።
«ሁሉም ሰው ዝም ብሎ በዒባዳ ተመስጦ ነበር። አንተ ብቻ ስትለፈልፍና ስትንቀለቀል ነበር።
ሰዎች በተዋዱዕ መሬት ላይ ሲቀመጡ ጉረኛው አንተ ግን ከፍታ ቦታ ላይ ራስህን ቆልለህ ቆመሀል!»…
ልክ ልኩን ነገረችዋ!😃
ሰውረነ!🙏
✍abdi
👉 ልብ አንጠልጣይ እዉነተኛ ታሪክ👈


#በ ሀላሌ ቻናል የቀረበ




።።።።።።።።።። ሲሀም።።።።።።።።።







ክፍል ሶስት








ይገርማል😳 መቼም አላያትም ብዬ ያሰብኳት ልጅ ፊትለፊቴ ናት በጣም ከመደንገጤ የተነሳ ልቤ ሲመታ ለራሴ አይደለም ለሰዉ ይሰማ ነበር በ አንድ ቀን ያፈቀርኳት ልቤን የሰጠዋት ልጅ ነበር አዉ እሷ ነበረች በጣም ደስ አለኝ .....



የት ነዉ ደግሞ የምታቂዉ ሲሏት
እእእእ ክረምት ላይ ዝናቡን አልቻልኩትም ብሎ ያስጠለልኩት ከዛ መንገዱን ስቶ የተደናበረዉ ነዋ ስትል ሁሉም ሳቁ 😡 ሙድ መያዛቸዉን አላቆሙም እንደዉም
ጭራሽ የምግቡን ሂሳብ አስከፈሉኝ አይይ ልጋበዝ ሄጄ ልጋብዝ


ከዛ አንድ ሀሳብ መጣልኝ ከ ሲሀም ጋ ለመቀራረብ ግዴታ ሪናን መለማመጥ አለብኝ
ከስሯ አልወጣም ነበር ቤት ስራ አግዛታለሁ ት/ቤት ደግሞ ከነ ጓደኞቹዋ እጋብዛታለሁ እነሱ ግን ለ ሂሳብ ጊዜ ብቻ ነበር ትዝ የምላቸዉ እንጂ ትዝም አልላቸዉም


እራሴን ዝቅ አርጌ ከሚንቁኝ ና ቦታ ከማይሰጡኝ ሰዎች ጋር እየሆንኩ ነዉ ብታዩ የምሆነዉ ነዉ የጠፋኝ
ግን ምን አይነት ነገር ነዉ ፍቅር ለካ እንደዚ ያረጋል 'የቃጥበሬ መንዙማ ላይ ራሱ እንደዚ አይደል የሚለዉ' " ፍቅር የሚሉት አደናጋሪ ለዝምተኛ አነጋጋሪ ሀይለኛ ነዉ አስቸጋሪ ጤና የለዉ " ጀማሉል አለም ሰለሏአ አለይ ወሰለም ጀማሉል አለም👏👏👏👏👏👏👏👏



እንደዛም እንደዚም እያልኩ 3 ወር አለፈን ግን እንኳን ፍቅሯ ሊበርድልኝ ጭራሽ እየባሰብኝ መጣ ግን የሚያሳዝነዉ ሲሀም እንኳን ልትወደኝ እንደኔ የምትንቀዉ ሰዉ አልነበረም ለነገሩ ማንን አይታ ታክብረኝ አንድ ቀን እህቴ ክብር ሰታኝ አታዉቅ አይይይ ተዉት ብቻ


እስካሁን ስለ ሲሀም ፀባይ የማቀዉ በጣም ቀበጥ ናት ከብዙ ወንዶች ጋ ትግባባለች በዲኖም ቢሆን በጣም ደካማ ናት ...

እህቴ የቀራች ናት ግን ምን ያረጋል ሸይጧንም ቀርቶ ነበር አልጠቀመዉም እንጂ ጓደኞቹዋን እንደመምከር ከነሱ የባሰች ናት አጀብ ለካ እዉቀት ያለ ስራ ምንም አይደለም አሏህም ቢሆን አውቀዉ የሚያጠፉትን ቅጣቱ ከበድ ያለ ነዉ
ብቻ አሏህ የሚጠቅም ና የምንሰራበት እዉቀት ይስጠን🙌



አሁን ግን በዉስጤ ለብዙ ጊዜ የደበቁትን ስሜቴን ለመናገር ወሰንኩ እስከመቼ እኔ ደግሞ ለሀራም አልፈልጋትም ሀላሌ እንድትሆን ነዉ የምፈልገዉ ያለንበት ሁኔታ ለ ትዳር ይቀረናል ቢሆንም ዚና ላይ ላለመዉደቅ ግዴታ ኒካህ ያስፈልጋል
እንደ ዝሙት ከባድ ወንጀል የለም ክብርንም ዝቅ ያረጋል የ አሏህንም ቁጣ ያወርዳል ብቻ
አሏህ ይጠብቀን ማለት ነዉ


ለሪና ለመንገር ወደ ክፍሏ ሄድኩ ቀስ ብዬ አንኳኳሁ


👦 ኳኳኳኳ

👩 ማነዉ

👦 ፋሪስ ነኝ

👩 ደግሞ ምን ፈለክ

👦 እእ እእ እእ አንዴ ላናግርሽ ፈልጌ ነዉ

👩 ምን ምንድነዉ ደግሞ

👦 እኮ ክፈችዉ እና እናዉራ

👩 እሺ ቶሎ ንገረኝ ምንድነዉ


👦 ምን መሰለሽ ሪና እእ እእ ሲሀምን ማሰብ ከጀመርኩ በጣም ቆየሁ ማለቴ እወዳታለሁ ሀላሌም እንድትሆን እፈልጋለሁ

👩 ሀሀሀሀ ኧረ ጭራሽ ሀላልህ ሌላ የለህም እሷ እንዳንተ አይነት ድሀ ጋ መኖር የምፈልግ ይመስልሀል ሀብታም ና የምፈልገዉን የሚያረግላት ሰዉ ነዉ የምፈልገዉ ....


👦 እኔም ኮ ጠንክሬ ከሰራሁ መለወጥ እችላለሁ አሏህ ሪዝቅ ይሰጠኛል

👩 ስማ አንተ መጀመሪያ ወንድ ሁን ደግሞ ሀብት ለምትለዉ አንተ እስክትሰራ ና እስትቀብር የ ልጆች እናት እንደምትሆን አትርሳ


👦 እኔ ኮ ግን አፍቅራታለሁ በሀላል መንገድ ነዉ የምፈልጋት

👩 ኧረ ስታየኝ ደላላ መስላለሁ እንዴ ከ ራሴ ላይ ዉረድ ሰዉዬ


👦 ኧረ እህቴ ስለሆንሽ ላማክርሽ ነዉ

👩 አይ ተወኝ በቃ ለ አባዬ ሳልነግረዉ ዉጣልኝ

👦 እሺ ግን ምን አለበት

👩 ዉጣልኝ!!


እሺ ብዬ ሆድ እየባሰኝ ወደ ክፍሌ ገብቼ ማሰብ ጀመርኩ በጣም ተናደድኩ እራስህን አጥፋ አጥፋ አለኝ እህቴ ያልተረዳችኝ እሷማ አይታሰብም ሸይጧን መጎትጎት አላቆመም አሁንም ራስህን አጥፋ አጥፋ አለኝ አኡዙቢሏህ ብዬ ኡዱ አረኩና 2 ረከአ ሰገድኩ ስጨርስ ተረጋጋሁ በቃ የኔ ከሆነች እሺ ትላለች ካልሆነም ይቀራል አሏህ ለ እኔ ኸይሬን እንዲመርጥልኝ ለ አሏህ ተዉኩት ከዛ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ


ነጋ ና ሱብሂዬን ሰግጄ ቁርስ በልቼ ሀሳን ጋ ሄድኩ
ሀሳን ማለት አብሮ አደጌ ነዉ
ከጠራሁት ቡሀላ ት/ቤት ሄድን

ግን ት/ቤት ወይ ጉድ ምን ይሄ ት/ቤት ነዉ የዱርዬ መሰብሰቢያ ነዉ ተዉኝ እስቲ ብዙ ጉድ ያለዉ ት/ቤት ነዉ በተለይ እዛ ያሉት ሙስሊሞች በጣም ነዉ የሚገርሙት እነሱ የባሰባቸዉ ናቸዉ

በቅርብ ካነበብኩት school life ከሚለዉ እዉነተኛ ና አስተማሪ ታሪክ በዘቢባ ሲልጣን የግል ታሪክ የፃፈችዉ የኛዉ ት/ቤት ጉድ ነበር....


በጣም ነዉ የጨነቀኝ እህቴ ነግራት ይሁን ብነግራትስ ምንም አላጠፋሁም ካልፈለገች ይቀራል ምንም ለኔ ቢከብደኝም ካፍቴሪያ ሂድ ሂድ አለኝ ግን ቆይ እህቴ ብታዋርደኝስ ለሚስትነት ይፈልግሻል ብላ ግን ምን አሳፈረኝ እኔ ለሀራም አልፈለኳት ብዬ ወደ ካፍቴሪያዉ ሄድኩ ስገባ ሁሉም ተሰብስበዉ ተቀምጠዋል........




........................ 4 ይቀጥላል...............
👉 ልብ አንጠልጣይ እዉነተኛ ታሪክ 👈



።።።።።።።።።።። ሲሀም።።።።።።።።።።


ክፍል አራት
#በ ሀላሌን ቻናል የቀረበ

ሁሉም ተሰብስበዋል እየፈራሁ ወደ ዉስጥ ገባሁ አሰላሙ አለይኩም ብዬ ቁጭ አልኩ አንዳቸዉም ግን አልመለሱልኝም ነበር ሪና ቶሎ ብላ እእ ማታ ለ እኔ ስትቀበጣጥር የነበረዉን ንገራታ አለችኝ ሁሉም ተነሱ ና ሄዱ እኔንና ሲሀምን ትተዉን ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር አብሪያት ስቀመጥ ...
እሺ ምን ነበር ንገረኝ ስትል
እእ እእ እእ ምን መሰለሽ ብዬ ማታ ለ ሪና የነገርኳትን በመሉ አንድም ሳይቀረኝ ነገርኳት
ምን ሀሀሀሀሀ ሀሀሀሀሀሀ ሀሀሀ አንተ ስማ እኔ የ ሪና ወንድም ነህ ብዬ ነዉ እንጂ አስጨመድድህ ነበር እኔ ሲሀም ለ እንደ አንተ አይነቱ የምሰጥ እቃ መሰልኩህ እንዴ ሲጀመር መጀመሪያ ወንድ ሁን እሺ ምን አይነቱ ነዉ አለቺኝ ብቻ በጣም ብዙ ነበር ያለቺኝ ስለደነገጥኩ እንዳንዱን አልሰማሁም ነበር ... በ ሰዉ መሀል አዋርዳኝ ጥላኝ ሄደች


እኔ ግን ደንዝዜ ፈዝዤ ቀረሁ ካፍቴሪያ ዉስጥ ያለዉ ተማሪ እኔን ነበር የሚያየዉ እኔ ግን አንገቴን አቀርቅሪ ነበር...
እንዴ ምን አይነቱ ነዉ በሴት ሊያዉም በፍቅር ይሰደባል አይኮራባትም ምን አይነቱ የወንድ አልጫ ነዉ ይባባሉ ነበር እኔን እንኳን አይዞህ ሊሉኝ ጥለዉኝ ሄዱ
እኔ ግን ምን አጠፋሁ መዉደድ ወንጀል ነዉ እንዴ ቆይ ፍቅር መዋረድ ማለት ነዉ እሺ እኔ ምን አጠፋሁ .....
በዚ ሀሳብ ዉስጥ እያለሁ አንድ የሴት ድምፅ ሰማሁ ፋሪስ የሚል ነበር ቀና ብዬ ሳይ ሀያት ነበረች ወንበሩን ጠጋ አድርጋ ፋሪስ እእ ፋሪሴ አይዞህ ተስፋ አትቁረጥ አሏህ ለ አንተ ካላት ትመጣለች ወሞ ያለ እሷ ሴት የለም እንዴ አለቺኝ ...

እኔ በመገረም እያየሁዋት ደግሞ ከመቼ ጀምሮ ነዉ ለኔ ማዘን የጀመረችዉ ..
እእ ሲሀም ልካሽ ነዉ እንዴ ስላት
ኧረ ወላሂ አይደለም ከ አንተ ስትመለስ ምን እንዳለችህ ጠይቂያት ነበር እንደሰደበችህና አንዳዋረደችህ ስነግረኝ ተቆጣሁዋት በዛም ም/ክ ተጣላን እና አንተ ጋ መጣሁ
እሺ አመሰግናለሁ ስለመጣሽ ምን ያህል ከፍቶኝ እንደነበር አታቂም ...
ይገርማል የገዛ እህቴ ስትርቀኝ ባዳ የሆነች ሊያወም የሷ ጓደኛን አገራት ለነገሩ አሏህ ጥቀም ካላለዉ ምንም ማንም አይጠቅምም ....

ወደ ክላስ ልሄድ ነዉ አብረን እንሂድ አለቺኝ
እሺ ብያት አብረን እየሄድን ስለ ትምህር አዉራን ስደርስ ቻዉ ብያት ገባሁ ...

ምሳ ሰአት ነበር ከ ሀሳን ጋ አየወጣን በር ላይ ሀያት ቆሞ እየጠበቀችኝ ነበር አስጠበቃችሁኝ እኮ አለች
👱እእ ኧረ አንቺ ሂጂ እኔ ከ ሀሳን ጋር እበላለሁ
👱‍♀የሌለ ሳቀች
👱ምን ያስቅሻል የምሬን ነዉ
👱‍♀እኔ እኮ ከነሱ ጋ እንብላ አላልኩህም እኛ ብቻ ነን የምንበለዉ
👱 እንዴ እነ ሪናስ
👱‍♀ ተጣላን
👱 ለምን
👱‍♀ለምን ለፋሪስ ደግፈሽ ሲሀምን ሰደብሻት ብለዉ ነዋ
👱ግን እኮ ጓደኞችሽ ናቸዉ
👱‍♀እና ይሁኑ ሲሳሳቱ እያየሁ ዝም አልልም
እሺ ካልሽ ብዬ ሶስታችንም ወደ ካፍቴሪያ አመራን አዘን ቁጭ አልን እያወራን እየሳቅን ነበር በተለይ ደግሞ ሀያት በጣም ነበር የምተትስቀዉ
ለነገሩ ከ እኔና ሀሳን ጋ ተቀምጦ የማይስቅ የለም
በልተን ስንጨርስ ሀያት ከፈለች አይገርምም ዛሬ ገና ተጊበዝኩ...

በየቀኑ አብረን ነዉ የምንበላዉ ልምድ አደረግነዉ የሌለ ፒስ ፈጠርን
እንደለመድነዉ አንድ ቀን ካፍቴሪያ እየሄድን ሲሀምን ከአንድ ወንድ ጋ ቆማ አየሁዋት እኔን ስታየኝ ልጁን አቅፋዉ ይዛዉ ሄደች በርግጥ እኔን ለማናደድ ነበር ተሳክቶላታል በጣም ነበር የተናደድኩት አንድ ወንበር ላይ ቁጭ ብዬ እያለቀስኩ ሀሳንን ያባብለኛል ሀያት ግን ዝም ብላ ታየኝ ነበር በዚ መሀል እንደዚ አለች ቆይ ምን ነክቶሀል ያነ ሷ ሴት የለም ለምን አተዋትም እሷ እንደሆነች ከ ሌላ ወንድ ጋ ፍቅር ጀምራለች ቁርጥህን አዉቀህ ተቀመጥ
👱 እእ እንዴት እእ ምን ማለት ነዉ ፍቅር ጀምራለች
👱‍♀ ምን አማረኛ መሰለኝ የ አንተ አይደለችም የሌለ ሰዉ ናት የማይሆን ቅዠትህን አቁም !!
👱 ህልም በሆነ አልኩኝ በጣም ደነገጥኩ ይሄ ማለት እኮ ያ ህልሜ በ ከንቱ ቀረ ሚስቴ የልጆቼ እናት ያልኳት ሌትም ቀንም ስለሷ የማስባት ልጅ ለካ......
ለምን እስካሁን አልነገርሽኝም ብዬ አፈጠጥኩባት
👱‍♀ ምን ብዬ ልንገርህ የገዛ እህትህ እንዳጣበሰቻት እእ
👱 ማለት ሪና የኔ እህት እእእ ናት ያጣበሰቻህ እእእ
👱‍♀ አዎ

የምሰማዉን ማመን አቃተኝ እበድ ጩህ አለኝ በጣም አዘንኩ
ሸይጧንም ይህንን አጋጣሚ ተጠቀመ ንዴቴን መቆጣጠር አልቻልኩም ሪናን ፍለጋ አየሮጥኩ ወደ ካፍቴሪያ ስሄድ የለችም ወደ ክላሷ ስሄድ ነበረች እያፈጠጥኩባት አጠገቦ ደረስኩ ዝም ብላ ታየኛለች ...
አንቺ ግን እህቴ ነሽ ጠላቴ ነሽ እንዴት እንደዚ ታረጊኛለሽ እኔ በሀላል ነዉ የምፈልጋት ስልሽ አሻፈረኝ ብለሽ ለብር ለብር ብለሽ ጓደኛሽን ሸጥሻት ቆይ ከ ምንድነዉ የተፈጠርሽዉ ከዚ ቡሀላ ወንድሜ ብለሽ እንዳጠሪኝ አይንሽን ማየት አልፈልግም ጠላት እንኮን ትጠነቀቂዋለሽ አንቺ ግን ወዳጅ መስሎ ጥላት ነሽ ትንሽ አላሳዝንሽም ብዬ የሷንም መልስ ሳልሰማ ጥዬአት ወጣሁ....

ወደ ክላስ ስመለስ ሀያት አይዞህ እንደዚ መዋል ስለማችል አስፈቅደህ ሂድ አለቺኝ
ሀሳን እኔ አደርሰዋለሁ ሲል አይ አልፈልግም ራሴ እሄዳለሁ ቻዉ ብያቸዉ
ስም ጠሪዬ ጋ ሂጄ እንዳመመኝ ነገርኩት እሱም ፈቀደልኝ
ዉሸቴን አልነበረም በጣም ነበር ያመመኝ ልቤን በ ጩቤ እንደተወጋ ሰዉ አሞኛል ይባስ ብላ ደሞ እህቴ ከዳችኝ የገዛ እህቴ
እንደ ክህደት ደሞ የሚያም ነገር የለም ሸህ ሁሴን ገታ እንኳን እንደዚ ብለዉ የለ '' መዳኒት የሌለዉ በሽታ ነዉ ክዳት''
ፍቅርም ቢሆን ህመም ነዉ በሚወዱት ሰዉ መጠላት ህመም ነዉ በሚቀርቡት ሰዉ መገለል ህመም ነዉ ....

መንገድ ላይ እንደ እብድ ብቻዬኔ እያወራሁ ምስጥ ያለ ሀሳብ ዉስጥ ገባሁ የምራመደዉንም አላወቁትም ነበር ግን እራሴን አልጋ ላይ ነበር ያገኘሁት ግራ ገባኝ አሁን ስራመድ አልነበር እንዴ .........

።።።።።። ይቀጥላል።።።።

ታሪኩን ካነበቡቡሀላ ሼር ያድርጉ
https://www.tg-me.com/abdu43211
ለሚያገኙሽና ለምታገኛቸው ሰዎች ሁሉ
በእነሱ እይታ የጥሩ ነገር አርአያ ላትሆኝ
ትችያለሽ ቢሆንም አትጨነቂ
በትክክል የሚያውቅሽ የንጉስ ዘውድ ያክል ከፍ ያለ ቦታ ላይ ያስቀምጥሻልና


#አላማችን ከዝሙት የፀዳ መሀበረሰብ ማፍራት ነዉ
👉 ልብ አንጠልጣይ እዉነተኛ ታሪክ 👈



።።።።።።።።። ሲሀም።።።።።።።።።።


ክፍል አምስት

አይኔን መክፈት እያቃተኝ እንደምንም ከፈትኩት ግን ብዝ ብዝ ይልብኛል በደንብ እየታየኝ ሲመጣ አልጋ ላይ ነኝ ዞር ዞር ብዬ ስመለከት ያየሁትን ማመን አቃተኝ ሆስፒታል ነበርኩ እንዴ ምን ሆኜ ነዉ ደሞ የገባሁት ግራ ገባኝ ለመነሳት ስሞክር በጣም ከበደኝ አልቻልኩም በቃ የሆነ አደጋ ገጥሞኝ ነዉ ብዬ አሰብኩ ግን እኮ ምንም አላስታዉስም የማስታዉሰዉ ነገር ቢኖር ከ ት/ቤት ወጥቼ ወደ ቤት ስሄድ ነዉ ሰዉነቴን ግን ምንም የህመም ስሜት አይሰማኝም ነበር
እሺ ቆይ ምን ሆኜ ነዉ ራሴን ስቼ ሰዉ አምጥቶኝ ነዉ በ ጭንቅላቴ ብዙ ጥያቄዎች ይመላለሳሉ በቃ ዶክተሮቹ ሲመጡ ለቤተሰቦቼ እንዲደዉሉ እነግራቸዋለሁ በዛዉ ምን እንደሆንኩኝ እጠይቃቸዋለሁ
ግን ቆይ ቤተሰቦቼ ሲሰሙ ምን ይላሉ እንዴትስ ይሆናሉ በተለይ እናቴ ግን እኮ ሰዉነቴን ምንም ህመም አይሰማኝም ለዛ ብዙም ጉዳት አልደረሰብኝም ግራ ገብቶኝ ሀሳብ ዉስጥ እንዳለሁ በሩ ይከፈታል ዞር ብዬ ስመለከት ወንድሜ ዩሱፍ ነበር በእጁ እቃ ይዟል መንቃቴን ልብ አላለዉም መሰለኝ እቃዉን አስቀምጦ ወደ ኔ ጠጋ አለ ስመለከተዉ እንባዬ መጣ ለምን እንደሆነ ባላቅም
እሱ ሲያየኝ በጣም ደነገጠ ምንም ሳይናገር እየሮጠ ሄዶ ሱጁድ ወረደ ና እዛዉ ማልቀስ ጀመረ ከዛ ተነሳና ወደ እኔ መጥቶ ተጠመጠመብኝ ለ ጀሊሉ ምን ይሳነዋል አልሃምዱሊላህ ይላል ደጋግሞም ግንባሬን ይስመኛል እኔም አኳሃኑ ይበልጥ አስለቀሰኝ ,...
ፋ ፋ ፋ ፋሪሴ አወቀኝ አለኝ እንባ በተሞል ድምፀ ግን አጠያየቁ ግራ ገባኝ
አዎ አዉቄሀለሁ ዩሱፍ ነህ ስለዉ በድጋሜ ሱጁድ ወረደ
እኔም እናቴ ሰምታለች አልኩት በመሀል ቃላቶች አያጠሩኝ
አዎ ሰምታለች ዉጪ ሁሉም አሉ ብሎ እንባዉን ጠረገ ና እየሮጠ ወጣ ከትንሽ ደቂቃዎች ቡሃላ የክፍሉ በር ተከፈተ ግን የተከፈተ ሳይሆን የተገነጠለ ነዉ የሚመስለዉ እናቴ ና አባቴ ነበሩ እናቴን ሳያት እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም እናቴ ወደ እኔ እየሮጠች መጥታ ፋሪሴ ብላ ጥምጥም አለችብኝ ከዛ ፋሪሴ እኔ ማነኝ ብላ እሷም ጠየቀቺኝ አዎ እናቴ ነሽ የኔ እናት አልኳት
አባቴም በግራ በኩል መጥቶ ተጠመጠመብኝ አባቴ ሲያለቅስ አይቼዉ አላቅም ዛሬ ግን እንደዚ ሲሆን የምሆነዉ ጠፋኝ እኔም አብሬዉ አለቀስኩ አሁንም እሱ እንደ እናቴ ና ዩሱፍ አወቀኝ ብሎ ጠየቀኝ አዎ አልኩት ..
በጣም ግራ ገባኝ ለምንድነዉ እንደዚ የሚጠይቁኝ ምን ብሆን ነዉ ቆይ ግራ ገባኝ ግን ለምን እንደሚጠይቁኝ አልጠየኳቸዉም በዚ መሀል ዩሱፍ ዶክተሮች ጠራ ሲገቡ እናቴ ና አባቴ እጄን ይዘዉ በጣም እያለቀሱ ነበር ዶክተሩ ተቆጣቸዉ እናንተ ምን ነክቶቹ ነዉ ልጁ ወደ ነበረበት ሁኔታ ልመልሱት ነዉ !! አላቸዉ

አንዱ ዶክተር ወደ ኔ ዞር ብሎ ፋሪስ
👨‍⚕ እንዴት ነህ
🤕አልሃምዱሊላህ ደህና ነኝ
👨‍⚕ አኔ ዶክተር አብረሀም እባላለሁ
🤕እኔ ፋሪስ
👨‍⚕እሺ ፋሪስ ሀመም የሚሰማህ ቦታ አለ
🤕የለም
👨‍⚕እሺ እዚ እንዴት እንደመጣህ ታስታዉሳለህ
🤕ኧረ በጭራሽ ምንም ትዝ አይለኝም
👨‍⚕ እሺ አሁን የምነግርህን ተረጋግተህ ስማኝ አዚ የመጣሀዉ ትንሽ የመኪና አደጋ አጋጥሞህ ነዉ ብዙ ሰርጀሪ (ቀዶ ህክምና) ከተሰራልህ ቡሀላ ነዉ ደህና የሆንከዉ አሁን የምጠይቅህን ጥያቄ በእርጋታ መልስልኝ
🤕 እንዴ መቼ ነዉ አደጋ የደረሰብኝ የቱ ጋ ነዉ ሰርጀሪ የተሰራሁት ስል
ሌላኛዉ ዶክተር ፋሪስ እዚ ከመጣህ ቆይተሀል አለ
ፈጠን ብዬ ስንት ቀን ቆየሁ አልኩት

ዶክተሩም ...






.................. 6 ይቀጥላል💁 ...........
2024/09/24 11:14:11
Back to Top
HTML Embed Code: