Telegram Web Link
ዓባይ ባንክ አ.ማ እና ሳፋሪኮም ኤምፔሳ የሥራ ስምምነት ውል ተፈራረሙ
----------------------------------------
ዓባይ ባንክ አ.ማ ከሳፋሪኮም ኤምፔሳ ጋር ስትራቲጂክ የሥራ አጋር በመሆን አብረው ለመሥራት  የሥራ  ስምምነት ውል ተፈራረሙ፡፡

በስምምነቱም መሰረት ዓባይ ባንክ የሳፋሪኮም ኤምፔሳ ሱፐር ኤጀንት በመሆን የሞባይል ባንኪንግ እና የኤጀንት ባንኪንግ ሥራዎችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ማሳለጥ እንዲሁም ደንበኞች ከዓባይ ባንክ ሒሳባቸው ወደ ኤምፔሳ ሒሳባቸው ወይም ከኤምፔሳ ሒሳባቸው ወደ ከዓባይ ባንክ ሒሳባቸው ገንዘብ ማስተላለፍ እንዲችሉ፣ የአገልግሎት ክፍያዎችን እንዲከፍሉ፣ የሒሳብ መረጃዎችን እንዲያዩ፣ የአየር ሰዓት እንዲገዙ እና ሌሎችንም የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶች እንዲያገኙ የሚያግዝ ነው፡፡

በፊርማ ሥነሥርዓቱ ላይ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠና የሳፋሪኮም ኤምፔሳ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፖል ካቫቩ በሰጡት አስተያየት የተጀመረውን የሥራ አጋርነት ስምምነት በማጠናከር ደንበኞችን የዘመናዊ የባንክ አገልግሎት እና የክፍያ ሥርዓት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስቻል የደንበኞችን እርካታ ለመጨመር እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል፡፡
የዓባይ ባንክ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባላት ከቅርንጫፍ ሥራ አሥኪያጆች ጋር የሥልጠና እና ምክክር መድረክ አካሄዱ
------------------------------------------------
የዓባይ ባንክ አ.ማ. የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባላት ከቅርንጫፍ ሥራ አሥኪያጆች ጋር የሁለት ቀናት የሥልጠና እና የምክክር መድረክ በአምባሳደር ሆቴል አካሂደዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የዓባይ ባንክ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ ኡስታዝ አብዱልመናን ከበደ፣ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባል ኡስታዝ ባህሩ ዑመር እና የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባል ሼህ ሰዒድ ኪያር ተገኝተው ከታሳታፊዎች ለተሰነዘሩ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

አቶ መሐመድ አሕመድ የዓባይ ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የሐብት ማሰባሰብ ሥራ አሥኪያጅ የሸሪዓ ስታንዳርድ እና ኮምፕሊያንስ እንዲሁም ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት በተመለከተ ለውይይት የሚሆን መነሻ ሐሳብ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ የውይይት መድረኩ እና ሥልጠናው መዘጋጀቱ የሸሪዓ እና ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎትን በተመለከተ ሰፊ ግንዛቤ ማስጨበጥ ያስቻለ መሆኑን ጠቅሰው፣ ተመሳሳይ መርሃግብሮች መዘጋጀታቸው አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ዓባይ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ 7 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በርካታ ደንበኞች በአገልግሎቱ እየተጠቀሙ መሆኑ ታውቋል፡፡
ዓባይ ባንክ ተደራሽነቱን እና አገልግሎቱን ይበልጥ በማስፋፋት ከደጅዎ ደርሷል!

ባንካችን 496ኛ ቅርንጫፉን በጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ “ቡኢ ቅርንጫፍ” በሚል ሥያሜ ከፍቶ ከዘርፈ ብዙ የባንክ አገልግሎቶች ጋር ይጠብቅዎታል፡፡

ዓባይ - ታማኝ አገልጋይ!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዓባይ ባንክ እና ሳፋሪኮም የሞባይል የገንዘብ ዝውውር ኤምፔሳ አገልግሎት በጋራ መስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ (የኢቲቪ ዘገባ)
ሙዳራባህ - የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎት

ባንካችን የሸሪዓ የፋይናንስ መርሆችንና አሠራሮችን መሰረት በማድረግ በሙዳራባህ ከወለድ ነጻ የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎቶቹ “ሙዳራባህ ትርፍ አጋሪ የቁጠባ ሒሳብ” እና “ሙዳራባህ ትርፍ አጋሪ በጊዜ ገደብ የሚቀመጥ ሒሳብ” አገልግሎቶችን በማቅረብ በርካቶችን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን በደስታ ይገልጻል፡፡

ዓባይ - ታማኝ አገልጋይ!

#abaybank #mudarabah
https://abaybank.com.et/wadia-and-mudarabah-deposits/
Foreign Currency Exchange Rates for 01 September 2023
For more updates please visit our website:
https://www.abaybank.com.et/exchange-rates

#abaybank #exchangerates
ዓባይ ባንክ ለ2016 የአዲስ ዓመት ዋዜማ “መርካቶን በሚሊኒየም ባዛርና ትርዒት” በመሳተፍ ደንበኞችን በማገልገል ላይ ይገኛል
--------------------------------------------
ዓባይ ባንክ አ.ማ. ለ2016 አዲስ ዓመት ዋዜማ በተዘጋጀው “መርካቶን በሚሊኒየም ባዛርና ትርዒት” ላይ በመሳተፍ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

በባሮክ ኢቨንት ኦርጋናይዘር አዘጋጅነት በደማቅ ሁኔታ የተከፈተው ባዛር እስከ ጳጉሜን 06/2015 ዓ.ም ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

በባዛር ጉብኝትዎ ለሚያስፈልግዎ ማንኛውም የባንክ አገልግሎት በዓባይ ባንክ እንዲገለገሉ ጋብዘንዎታል፡፡

ዓባይ - ታማኝ አገልጋይ!
#abaybank #newyearexhibition
በዓባይ ባንክ ይሸለማሉ!
---------------------------
ከወዳጅ ዘመዶችዎ ለፍቅራቸው መግለጫ ለመጪዎቹ የአዲስ ዓመት፣ የመስቀልና የመውሊድ በዓላት ከውጭ አገር በዓባይ ባንክ ገንዘብ ሲላክልዎ፣ በባንካችን ሲመነዝሩ እና ከብር 250 ጀምሮ በባንካችን ሲቆጥቡ ከዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል ጀምሮ በርካታ ፍሪጆች፣ ቴሌቪዥኖች፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች እና ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎች ዕጣ አሸናፊ ሊሆኑ ይችላሉ!

ይቆጥቡ፤ ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ፤ ይሸለሙ!
ዓባይ - ታማኝ አገልጋይ!
Abay Bank pinned a photo
2024/09/30 21:34:43
Back to Top
HTML Embed Code: