Telegram Web Link
Foreign Currency Exchange Rates for 01 March 2024

For more updates please visit our website:
https://www.abaybank.com.et/exchange-rates
#abaybank
እንኳን ለ128ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ።
የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ድል!

#abaybank #Adwavictory
የዓባይ ባንክ የ7ኛ ዙር  የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ
----------------------------------
ዓባይ ባንክ ከነሐሴ 26/2015 ዓ.ም እስከ ጥር 18/2016 ዓ.ም ድረስ ሲያከናውን የቆየው 7ኛው  “ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

በዚሁም መሠረት ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ አሸናፊ ቁጥር 46527286 መሆኑ ታውቋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ለሽልማት የተዘጋጁ የ2ኛ ዕጣ እያንዳንዳቸው አስር ፍሪጆች፣ 3ኛ ዕጣ የአስር ቴሌቪዥኖች፣ 4ኛ ዕጣ አስር ላፕቶፖች እና 5ኛ ዕጣ ሃያ ዘመናዊ የስልክ ቀፎዎች የሚያስገኙ ዕጣዎችም ወጥተዋል፡፡

በዕጣ አወጣጡ ሥነ ሥርዓት ላይ የዓባይ ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራሮችና  የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ባለሙያዎችና ታዛቢዎች ተገኝተዋል።

ዓባይ ባንክ በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የደንበኞችን የቁጠባ ባህል ለማሳደግ እንዲሁም ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ የሆነውን የውጭ ምንዛሬ ደንበኞች ህጋዊ በሆነ መንገድ እንዲጠቀሙ በማበረታታት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡

የባንኩን የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም አሸናፊዎችን በቀጣይ የምናሳውቅ ሲሆን፣ ባንኩ ለዕድለኞቸ ከወዲሁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን ማስተላለፍ ይወዳል፡፡
Foreign Currency Exchange Rates for 04 March 2024

For more updates please visit our website:
https://www.abaybank.com.et/exchange-rates
#abaybank
ዓባይ ባንክ በአዳማ ከተማ 534ኛ ቅርንጫፉን “አዳማ ራስ ቅርንጫፍ” እንዲሁም 535ኛ ቅርንጫፉን “ከረዩ ቅርንጫፍ” በሚሉ ሥያሜዎች ከፈተ፡፡
ከዘርፈ ብዙ የባንክ አገልግሎቶች ጋር እንጠብቅዎታለን፡፡ ይጎብኙን!

ዓባይ - ታማኝ አገልጋይ!
#abaybank
https://abaybank.com.et/branch-locator
የዓባይ ባንክ ካርድዎ 24/7 በየትኛውም ቦታ ያገለግልዎታል፡፡
በካርድዎ ግብይትዎን ያቀላጥፉ፣
ክፍያዎን ይፈጽሙ፣
ድካምዎን ያቅልሉ፣
ኑሮዎን ያዘምኑ!

ዓባይ - ታማኝ አገልጋይ!
#abaybank
https://abaybank.com.et/card-banking/
Abay Bank pinned a video
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Introducing the New Hallmark.
Abay Bank pinned a video
እንኳን ለማርች 8 ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን አደረስዎ!
-----------------------------
የዘንድሮው ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን “ሴቶች ላይ ኢንቨስት በማድረግ፣ እድገትን ማፋጠን” በሚል መሪ ሐሳብ በዓለምአቀፍ ደረጃ ለ113ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል።

ዓባይ ባንክም በተለያዩ ደረጃዎች ሴቶች ወደ አመራርነት እንዲመጡ በትኩረት በመሥራትና ሴቶች ፍሬያማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ሀገራዊ ተግባራትን በመደገፍ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡

ባንካችን ለውድ ደንበኞቹ እንደየፍላጎታቸው ካዘጋጃቸው በርካታ የቁጠባ አማራጮች መካከል ለሴቶች ብቻ የተዘጋጁ “ንግሥት” ልዩ የቁጠባ አገልግሎት እና “ሱመያ” ከወለድ ነጻ የቁጠባ አገልግሎት የተባሉ የቁጠባ አማራጮችን በማቅረብ ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጋብዘንዎታል፡፡

ዓባይ - ታማኝ አገልጋይ!
#abaybank
https://abaybank.com.et/womens-saving-account/
የዓባይ ባንክ አዲሱን የብራንድ መለያ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ
-----------------
ዓባይ ባንክ አዲሱን የብራንድ መለያውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል ሰጥቷል።

መግለጫውን አቶ ወንድይፍራው ታደሰ የባንኩ የስትራቴጂ ዋና መኮንን የሰጡ ሲሆን፣
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ከተለያዩ ሚዲያዎች የተወጣጡ ጋዜጠኞች ላነሷቸው ጥያቄዎች ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አዲሱ የብራንድ መለያ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በይፋ ይመረቃል።
የዓባይ ባንክ የአዲሱ የብራንድ መለያ ምረቃ ሥነሥርዓት ከጥቂት ደቂቃ በኋላ በይፋ ይጀመራል።

ሥነሥርዓቱን ለመታደም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል ተገኝተዋል።
2024/09/29 15:23:29
Back to Top
HTML Embed Code: