Telegram Web Link
የዓባይ ባንክ አዲሱ የብራንድ መለያ በይፋ ተመረቀ።
እንኳን ለዐብይ ጾም አደረስዎ!

ዓባይ ባንክ ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለዐብይ ጾም አደረስዎ እያለ የጾሙ ጊዜ የፈጣሪን በረከት የሚያገኙበት እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን።
እንኳን ለረመዷን ጾም አደረስዎ!

ዓባይ ባንክ ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለረመዷን ጾም አደረስዎ እያለ የጾሙ ጊዜ የበረካ እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን።

ረመዷን ሙባረክ!
Foreign Currency Exchange Rates for 11 March 2024

For more updates please visit our website:
https://www.abaybank.com.et/exchange-rates
#abaybank
Channel photo updated
የዓባይ ባንክ አዲሱን ብራንድ የማስመረቅ ሥነሥርዓት በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል
ዓባይ ባንክ በቅርቡ ስላስተዋወቀው አዲሱ የብራንድ መገለጫ አጠቃላይ ማብራሪያ ሰጠ
------------------------------------------------
ዓባይ ባንክ ይጠቀምበት የነበረውን የብራንድ መለያ በአዲስ የብራንድ መለያ የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል ማስመረቁ ይታወሳል፡፡

አቶ ወንድይፍራው ታደሰ የዓባይ ባንክ የስትራቴጂ ዋና መኮንን መጋቢት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከአርትስ ቲቪ ጋር ባደረጉት ውይይት የባንኩን አዲስ የብራንድ መለያ እንዲሁም የሪብራንዲንግ ሥራውን አጠቃላይ ይዘት አስመልክቶ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥተዋል፡፡

አዲሱ የብራንድ ማንነት ባንኩ ለፈጠራ ሥራ፣ ደንበኛ ተኮር ለሆነ አገልግሎት እና ዘለቄታዊ እድገት በፍጥነት ወደፊት የሚገሰግስ ባንክ መሆኑን ማሳያ እና ይህንንም ዘርፈ-ሰፊ ጥረት የሚያግዝ እንደሆነ አቶ ወንድይፍራው ገልፀዋል፡፡

ዓባይ ባንክ በብራንድ አማካሪነት ትልቅ ስም ባለው እና ታዋቂ በሆነው ስቱዲዮኔት ኃ/የተ/ድ ባለቤት አቶ ያየህይራድ ታደሰ የሪብራንዲንግ ፕሮጀክቱን በማሰራቱ ትልቅ ክብር እንደተሰማው ገልፀው አማካሪው ላደረጉት ዓይነተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ከዚህም ጋር አያይዘው አዲስ የብራንድ መለያ መቀየር ያስፈለገበትን መነሻ ሐሳቦች የጠቆሙት አቶ ወንድይፍራው የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ የባንኩን አመርቂ ዕድገት በሚመጥን መልኩ ማቅረብ ማስፈለጉ ከዋነኞቹ ምክንያቶች አንዱ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፣ ባንኩ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዘ ሰፊ ሥራዎችን በማከናወን እና ከፍተኛ ወጪ በማውጣት በዓይነቱ ልዩ እና ምቹ የሆነ አዲስ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ እና ድረ-ገጽ በማበልጸግ ወደ ሥራ እንዳስገባም ተናግረዋል፡፡

ለደንበኞች ምቹ አገልግሎት ከመስጠት ጋር በተገናኘ ባንኩ ለአካባቢ ጥበቃ እና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትኩረት በመስጠት ደንበኞች የባንኩን አገልግሎት በዲጂታል ባንኪንግ እንዲጠቀሙ የሚያስችል የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስርዓት በመዘርጋት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ዓባይ ባንክ በሀገሪቱ ዕድገት ውስጥ የጎላ ሚና በመጫወት በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ ለሁሉም የንግድ ተቋማት፣ ለግብረ ሰናይ ድርጅቶች እና ለሁሉም ማህበረሰብ አካላት ዘርፈ ብዙ የባንክ አገልግሎቶችን በማቅረብ ተግቶ እንደሚሠራ አቶ ወንድይፍራው ታደሰ ገልፀዋል፡፡

https://youtu.be/aTKPu-z6MAA?si=dXAJRrH0aG-wrz3N
#ዓባይባንክ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አስደሳች ዜና!
ዓባይ ባንክ አዲስ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ይፋ አደረገ!

ባንካችን በዓይነቱ ልዩ እና ምቹ የሆነ አዲስ የሞባይል መተግበሪያ አቀረበልዎ!
አዲሱን የሞባይል መተግበሪያ ከአፕስቶር እና ፕሌይስቶር በማውረድ አዲሱን የሞባይል ባንኪንግ በምቾት ይጠቀሙ!

#ዓባይባንክ #ሞባይልባንኪንግ
Abay Bank pinned a video
አዲሱን የባንካችንን ድረ-ገጽ እናስተዋውቅዎ!

በአዲስ ይዘት፣ ቅርጽ እና ውበት ተዘጋጅቶ ደንበኞችን ማዕከል ባደረገ መልኩ አስፈላጊውን መረጃ አጠናቅሮ የተዘጋጀው እና ለአጠቃቀም ምቹ፣ ቀላል እና ፈጣን የሆነውን አዲሱን የባንካችን ድረ-ገጽ እንዲጎበኙ ስንጋብዝዎ በታላቅ ደስታ ነው፡፡
ይህን ማስፈንጠሪያ ይከተሉ👇
www.abaybanksc.com

በተጨማሪም ቀጥሎ በተዘረዘሩት የባንካችን የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ቤተሰብ በመሆን የባንክ አግልግሎቶችን፣ ክፍት የሥራ ቦታዎችን እና አጠቃላይ የፋይናንስ መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/abaybanksharecompany
ቴሌግራም፡
https://www.tg-me.com/abaybanksharecompany
ትዊተር፡
https://twitter.com/AbayBank
ሊንክድኢን፡
https://www.linkedin.com/company/abaybank/
ዩትዩብ፡
https://www.youtube.com/@abaybank4665
2024/09/29 13:31:02
Back to Top
HTML Embed Code: