Telegram Web Link
ህብረተሰቡ መብቱን ከመግዛት እንዲቆጠብ ተጠቆመ
=====||=====
ወንጀል ፈፃሚዎችን ለማስቀጣት ቁርጠኛ አመራርና ዐቃቤያነ ህግ መኖራቸውን አዉቆ ማህበረሰቡ መብቱን ገዝቶ ከመጠቀም ተቆጥቦ በአግባቡ እንዲገለገልና የሙስና ወንጀል መፈጸሙን ያየ ወይም ያወቀ እንደሆነም ጥቆማ በመስጠት የወንጀል ፍትሕ ስርዓቱን እንዲያግዝ ተጠየቀ

ህብረተሰቡ የሙስና ወንጀል ሲፈጸም አይቶ ዝም ከማለት ጥቆማውን ለተቋሙ እንዲያቀርብ የተጠየቀው የሙስና ወንጀሎችን ከመከላከል እና አጥፊዎችን በህግ ከማስጠየቅ አንጻር ተቋሙ በራሱ ሰራተኞች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎችን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው፡፡

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ ከሙስና ወንጀሎች ጋር በተገናኘ ሙስናን ከመከላከል አንፃር የተሰሩ ስራዎችንና በተቋሙ  የተገኙ የወንጀል ግኝቶች የምርመራ ሂደትን አስመልክቶ በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ፍቃዱ ፀጋ አማካኝነት ሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

ሚኒስቴር ዴኤታዉ መግለጫዉን ሲጀምሩም በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ በጊንቢ ቶሌ ቀበሌ በንጹሃን ላይ በተፈጸመው ዘግናኝ የወንጀል ድርጊት ሀዘናቸዉን የገለፁ ሲሆን የተፈፀመዉን የወንጀል ድርጊት መርምሮ ድርጊቱን የፈጸሙ ሁሉ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ለማድረግ የሚያስችል ምርመራ እንዲደረግ ከፌዴራል ፖሊስና ከክልሉ የፍትህ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ስምሪት ተሰጥቶ ምርመራ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ በ2014 በጀት አመት በሙስና ወንጀሎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት እቅድ ይዞ ሲሰራ መቆየቱን የገለፁት ሚኒስቴር ዴኤታዉ  በዋናነት ሙስናን የመመርመርና የመክሰስ ስትራቴጅ ተነድፎ ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት ተደርጎ ወደ ተግባር የተገባ መሆኑንና በተጨማሪም በተቋሙ ሙስናን እንዴት መከላከል እንደሚቻል ጥናት በማድረግ ጭምር በበላይ አመራሩ ታምኖበት ሲሰራበት ቆይቷል፡፡ ለዚህም ተግባር ያግዝ ዘንድ በህግና ፍትህ ኢንስቲቲዩት እንዲሁም በፍትህ ሚኒስቴር ዐቃቢያነ ህግ ዋና ጉባኤ ፅ/ቤት አማካኝነት የተለያዩ ጥናቶች መደረጋቸዉን  ተናግረዋል፡፡

በተቋም ደረጃ ከሙስና ወንጀሎች ጋር በተያያዘ በሶስት የተቋሙ ሰራተኞች ላይ ምርመራን በማጣራት በአንዱ ግለሰብ ላይ ክስ መመስረቱን የተናገሩት አቶ ፍቃዱ እነዚህ ግለሰቦችም በተቋሙ የሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጀነራል ሀብት መርማሪ  ሆኖ ሲሰራ የነበረ ወንደወሰን በቀለ የተባለ ግለሰብ፣ የሙስና ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ህግ የሆነው ስንታየሁ አስማማዉና በኢኮኖሚ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት የመዝገብ ቤት ሰራተኛ የሆነው ቶሎሳ አበራ የሚባሉ ሶስት ግለሰቦች እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡

ወንደወሰን በቀለ የተባለዉ የሀብት መርማሪ ፖሊስ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ የልማት ተነሺ ናችሁ በሚል ከ65 ሚሊዬን ብር በላይ ያላግባብ የመዘበሩ ሰዎችን በማጣራት ሂደት ዉስጥ በተደረገዉ ሀብት ማሳገድ ግለሰቡ እግድ አስነሳላችኋለሁ በማለት 11 ሰዎች ከ200 መቶ ሺ እስከ 400 መቶ ሺህ ጉቦ በመጠየቅ ገንዘብ የተቀበለ መሆኑ  በማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን ሚኒስቴር ዴኤታዉ በመግለጫቸዉ ገልፀዋል፡፡

ዐቃቤ ህግ ስንታየሁ አስማማዉ በበኩሉ በስራ አጋጣሚ  እጁ የገባን ሶስት ተጠርጣሪዎች ያሉበት መዝገብ ተጠቅሞ ከአንዱ ተጠርጣሪ ገንዘብ ሲቀበል እጅ ከፈንጅ የተያዘ መሆኑንና የመዝገብ ቤት ሰራተኛዉ ቶሎሳ አበራ በበኩሉ ከፍተኛ ፍድር ቤት የሚያስከስሰዉን መዝገብ ወደ መጀመሪያ ፍርድ ቤት ዝቅ እንዲል አደርግላችኋለሁ በማለት ከአራት ግለሰቦች ገንዘብ እንደተቀበለ በሰጡት ቃል መረዳት መቻሉን አብራርተዋል፡፡

በተያያዘ ሌሎች ተመሳሳይ ጥቆማዎችና ምርመራዎች ሂደት ላይ መሆናቸዉ የተገለፀ ሲሆን በዋናነት ህብረተሰቡ ከተባበረ ወንጀል ፈፃሚዎችን ለማስቀጣት ቁርጠኛ አመራርና ቁርጠኛ የሆኑ የተቋሙ ዐቃቢያነ ህግ መኖራቸውን አዉቆ ማህበረሰቡ መብቱን ገዝቶ ከመጠቀም ተቆጥቦ በአግባቡ እንዲገለገልና  ጥቆማዎችን ማቅረብ ሲፈልግም ልደታ በሚገኘዉ የሙስና ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት 4ተኛ ፎቅ በመገኘት ጥቆማ ቢሰጥ ዐቃቤ ሀግ ተገቢዉን ምርመራ አድርጎ ክስ በመመስረት ተገቢዉን ዉሳኔ ለማሰጠት ቁርጠኛ መሆኑን ሚኒስቴር ዴኤታዉ አቶ ፍቃዱ ፀጋ አሳስበዋል፡፡

በተያያዘም በቅርቡ ዉሳኔ ያገኙ ሌሎች ትልልቅ አገራዊ መዝገቦችን አስመልክቶ በመግለጫዉ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ በጉራፈርዳ ማንነትን መሰረት አድርጎ በተፈፀመ ጥቃት የተሳተፉ ወንጀለኞች ከ6 አመት ጀምሮ እስከ 23 አመት ድረስ በሚደርስ እስራት የተቀጡ መሆናቸዉ፤ በተመሳሳይ በመተከል በተፈጸመ ጥቃት በወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች  ከ8 አመት እስከ እድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንደተቀጡ ገልፀዋል፡፡

ከሀይማኖት ጋር በተገናኘ በጎንደርና በወራቤ ያሉ ምርመራዎች፣ በጅንካና በደራሼ ያሉ የምርመራ ሂደቶችም በሂደት ያሉ መሆናቸዉን የተናገሩት አቶ ፍቃዱ በቅርቡ በጊንቢ ቶሌ የተፈፀመዉን ግድያ አስመልክቶም የምርመራ ለማከናወን ስምሪት መሰጠቱንም ገልፀዋል፡፡

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid05AKrXXyxa8JbTDY7MFcCGmuX7vwSdNfnbhBGLDnt4G6uzh29QXnkubjoHi3U9RZel&id=100064822533625
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የምዝበራ ወንጀል እንዲፈጸም ባደረገ ግለሰብ ላይ ክስ ተመሰረተ።

====||====

የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፈቃዱ ጸጋ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ የሙስና ተግባር ዝንባሌን ለመረዳት በተቋሙ ውስጥ ጥናት መደረጉን ተናግረው፣የተካሄደው ጥናት ውጤት እያመጣ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ለአብነትም፣ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የልማት ተነሽ ያለሆኑ 29 ግለሰቦች ላይ ከ65 ሚሊየን ብር በላይ ያለአግባብ በመንግስት ገንዘብ ላይ ምዝበራ እንዲፈጸም ባደረገ ግለሰብ ላይ ክስ መመስረቱንም ገልጸዋል።

ለተቋሙ በቀረቡ ጥቆማዎች መሰረት ሶስት የተቋሙ ሰራተኞች የሙስና ወንጀል ሲፈጽሙ ተገኝተው የክስና ምርመራ ተግባር እየተካሄደ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አመላክተዋል።

ትራንስፓረንሲ ኢትዮጵያ በርካታ የህዝብ አቤቱታ በሚቀርብበት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተጀመረውን ክትትል እያደነቀ፣ ይህ ተግባር በዚሁ ክፍለ ከተማ እንዲሁም በሌሎችም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያሳስባል።
Transparency has given training to Journalists and Government Public Relations Officers from Sidama and SNNPRS regions
=====//=====

June 30, 2022:
Transparency Ethiopia has organized a successful training event where a total of 30 high level journalists and government public relations directors received training on how to conduct and give interviews. Fifteen (15) prominent journalists of the regions and fifteen (15) PR Directors of all regional government Bureaus were present.

The purpose of the event was to help create a smooth and amicable working relationship between the two categories of professionals and equip them with important skills of conducting and giving interviews. Transparency Ethiopia believes that a complementary relationship between these two categories of professionals is instrumental to foster transparency and bridge the gap between the public and government offices.

Woyessa Woka, TE regional representative opened the session with brief information about the profile of Transparency Ethiopia and presented the agenda of the day. Dr. Mengistu Dinato, assistant professor at Hawassa University, and Hiwot Yohannes, lecturer and former head of Communication and Journalism Department of Hawassa University, provided theoretical training during the first half of the session to the journalists and to the PR Directors respectively.

The second half of the session focused on practical training in the presence of both groups of professionals together. Ato Philipos Nahom, Sidama Region Public Relations Directorate Director, collaborated with the trainers during the practical session. He noted, during his concluding remark, that his Office understands the existing gaps with regards to public relations and expressed commitment to work towards alleviating the challenges collaboratively with Journalists and other stakeholders. Ato philipos appreciated Transparency Ethiopia for taking such an initiative and called for similar initiatives to continue.

Woyessa, TE’s Hawassa representative, finally expressed gratitude to European Union Civil Society Fund III for financially supporting the event; and also extended appreciation to Ato Philipos Nahom, the trainers of the day and all the participants for their active participation.
 
 
Transparency Ethiopia conducts Successful training and discussion session with Assosa University students.
                   ====//====
Assosa University student leaders from various clubs have received a three day(July 01-03)training on three themes namely: time management, Ethical leadership, and Volunteerism and campaigning in anti corruption movement in Ethiopia. Abraham Hunduma and
Getachew Kebede, regional representatives of Transparency Ethiopia, effectively delivered the trainings.

In parallel to the training event, a discussion session was held with 100 (one hundred) Assosa University graduating class students on the theme 'being responsible, transparent and accountable citizens'.

At the end of the session, the graduating students took an oath where they expressed their commitment to refrain from corruption and immoral acts, and to fight injustice and safeguard humanrights as they join the workforce.

Ato Yayeyirad, Ethics and Anti-Corruption Directorate Director of Assosa University, encouraged students to put the knowledge they have acquired into practice. Students finally received a certifate as a token of their participation in the trainings and discussions.

The training and discussion events are part of the European Union Civil Society Fund III supported project titled "Ensuring Participation of Actors for Transparency and Accountability of Institutions to Support the fight against Corruption and Promote Democratic Governance and Rule of Law in Ethiopia".
በሙስና እና ብልሹ አሰራር ዙርያ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ትራንስፓረንሲ ኢትዮጽያ ያሳስባል።
***//****
ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ከመዋጋት ጋር በተያያዘ በሳምንቱ መካከል በአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር በነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ እንዲሁም የጋራ መኖርያ ቤቶች ዕጣ ውጤት ጋር በተያያዘ የተወሰዱ እርምጃዎች የሚበረታቱ እና ለፀረ ሙስና ትግሉ ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ትራንስፓረንሲ ኢትዮጽያ ይገልፃል።

የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር በቁጥጥር ስር የዋሉት ኤልሻዳይ ከተሰኘ በጎ አድራጎት ማህበር ስራ አስፈፃሚ ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በመጠርጠራቸው ነው። ኤልሻዳይ የተሰኘው ድርጅት በአዋሽ፣ በአዳማ፣ በሐዋሳ፣ በእንጅባራ በመሳሰሉ አካባቢዎች ተፈናቃዮች በሌሉበት ተፈናቃዮች አሉ በማለት በተደጋጋሚ ጊዜ የእርዳታ እህልና አልባሳት በመረከብ ሽጦ ለተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት መግዛቱ በምርምራ መረጋገጡን ፌደራል ፖሊስ አረጋግጧል።

በሌላ ዜና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ/ም የወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ  ውድቅ መደረጉን አስታውቋል።ዕጣው የተሰረዘው የከተማ አስተዳደሩ ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓቱ በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ሲጀመር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነት መኖሩ በመረጋገጡ ነው ተብሏል፡፡

በእጣው የሚካተቱት 79 ሺህ ቆጣቢዎች መሆን ሲገባው ምርመራ ሲደረግ ግን በእጣው ውስጥ የተካተቱት ሰዎች ቁጥር 172 ሺህ መሆኑ ተረጋግጧል ነው ያሉት፡፡

ከ14ኛ ዙር የ20/80 እና ከ40/60 3ኛ ዙር  እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ  ቢሮና የቤቶች ቢሮ  አመራሮችና ባለሙያዎችን ከሀላፊነት የማብሳት እና በህግ በቁጥጥር ስር የማዋል እርምጃ መወሰዱ ተሰምቷል።

ትራንስፓረንሲ ኢትያጽያ ሙስናን ለመዋጋት በሚደረገው ሁሉን አቀፍ ትግል ውጤታማነት ይህን መሰል ህጋዊ እርምጃዎች በሁሉም ዘርፎች መቀጠል አስተዋጾ እንደሚያደርግ ያሳስባል።
2024/11/16 11:45:49
Back to Top
HTML Embed Code: