Telegram Web Link
💨 ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም! ለ90 ቀን ከሚቆይ ነጻ 100ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር! ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት
  
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether
የኦሮሚያ ክልል በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የክልሉ ተማሪዎች ዕውቅና ሰጥቷል።

በክልሉ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ከ241,000 በላይ ተማሪዎች መካከል 8,520 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

ከእነዚህ ተማሪዎች ውስጥ 305 የሚሆኑ ተማሪዎች ከፍተኛ ነጥብ ማምጣታቸውን ተናግረዋል።

ከፍተኛ ውጤት ካመጡ ተማሪዎች ውስጥ ለ77 ተማሪዎች የላፕቶፕ፣ የገንዘብ እና የሜዳልያ ሽልማት ተበርክቷል።

በክልሉ የሚገኙ ሞዴል እና ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ማሳለፋቸውን ጠቅሰዋል።

@tikvahuniversity
#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን የመግቢያ ጊዜ መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ትምህርት መስከረም 22/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

Note:
ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ እንደሚደረግ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#WoldiaUniversity

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል እና የአዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜን አራዝሟል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተምራችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እና በ2017 ዓ.ም ወልድያ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለምትመደቡ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 27 እና 28/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎ ጥሪ የተላለፈ ቢሆንም፤ ምዝገባው በተለያዩ ምክንያቶች የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

Note:
የሌሎች ነባር ተማሪዎች ምዝገባ ከዚህ ቀደም በተገለፀው መሰረት መስከረም 27 እና 28/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

@tikvahuniversity
#SalaleUniversity

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ፤ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከታወቀ በኋላ የሚገለፅ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

1ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ነባር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ቀናት ከዚህ በፊት በተገለፀው መሰረት መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ራያ ዩኒቨርሲቲ 59 የተቋሙ መምህራንን በከፍተኛ ዲፕሎማ መርሐግብር (HDP) አስመርቋል።

ስልጠናውን ተከታትለው ከተመረቁ መመህራን ውስጥ 11 ሴት መምህራን ይገኙበታል።

ራያ ዩኒቨርሲቲ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የመምህራን አቅም ለማሳደግና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ መምህራኖቹን በከፍተኛ ዲፕሎማ መርሃሐግብር (HDP) እያሰለጠነ እንደሚገኝ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት መለቀቅን ተከትሎ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ የድኅረ ምረቃ አመልካቾችን ለመቀበል ማስታወቂያ እያወጡ ይገኛሉ።

አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን የመግቢያ ፈተና (NGAT) ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

(የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ያወጧቸው የጥሪ ማስታወቂያዎች ከላይ ተያይዘዋል፡፡)

@tikvahuniversity
#AAU

የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የወሰዳቹ ተፈታኞች ውጤታችሁን ኦንላይን ማየት እንደምትችሁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ውጤት ለማየት 👇
https://portal.aau.edu.et/Web/ApplyForAdmission/TestingStatus

በተመሳሳይ በመንግስት ስፖንሰር ተደርጋችሁ የቅድመ ምረቃ ትምህርታችሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመከታተል ፈተና የወሰዳችሁ አመልካቾች፣ ውጤታችሁን https://portal.aau.edu.et/ ላይ ገብታችሁ Username (email) እና Password በማስገባት መመልከት ትችላላችሁ።

ዩኒቨርሲቲው ሦስተኛ ዙር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) በቅርቡ ይሰጣል ማለቱ አይዘነጋም።

@tikvahuniversity
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማሳለፍ የቻሉ ትምህርት ቤቶች ሰባት ብቻ ናቸው።

ከነዚህ ጥቂት ስኬታማ ትምህርት ቤቶች መካከል በጅግጅጋ ከተማ የሚገኘው The Spark Academy አንዱ ነው።

ትምህርት ቤቱ ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ያስፈተናቸውን 35 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማሳለፍ ችሏል። ሁለት ተማሪዎች ደግሞ ከ500 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

የተገኘው ውጤት የት/ቤቱ ማኅበረሰብ የተቀናጀ ጥረት ፍሬ መሆኑን የአካዳሚው ባለቤት ክፍለገብርኤል ወ/ተንሳይ ለ SRTV አማርኛ ተናግረዋል።

አካዳሚው በ2017 ዓ.ም 25 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንደሚያስፈትን የገለፁት ባለቤቱ፤ ሁሉንም ተማሪዎች ለማሳለፍና የሀገሪቱ ከፍተኛ ውጤት በትምህርት ቤቱ እንዲመዘገበ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ መደበኛ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች እንዲሁም ለነባር የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ጥሪ አለማድረጉን አረጋግጧል።

ወደፊት በ EBC እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ማኅበራዊ ሚዲያ ገፆች ጥሪ የሚደረግ መሆኑን የገለፀው ዩኒቨርሲቲው፤ እስከዛ ድረሰ ተማሪዎቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል።

@tikvahuniversity
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ ዙር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) የማመልከቻ ግዜን እስከ መስከረም 25/2017 ዓ.ም አራዝሟል፡፡

ለ GAT ፈተና ለማመልከት 👇
https://portal.aau.edu.et

ለማመልከት፦

https://Portal.aau.edu.et ይክፈቱ።
► Exam Application የሚለውን ይጫኑ።
► Test Taker Registration ቅፅን ይሙሉ።
► ፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶዎን ያስገቡ።
► Submit የሚለውን ይጫኑ።
► ሲስተሙ የሚሰጥዎትን ቁጥር ኮፒ ያድርጉ።
► የGAT ፈተና ክፍያ ብር 1000 በቴሌብር ይክፈሉ።
► የክፍያ ቲኬትዎን አውርደው ፕሪንት ይበሉ። የፈተና ቀን ወደመፈተኛ አዳራሽ ለመግባት ያስፈልግዎታል።

@tikvahuniversity
#EthiopianCivilServiceUniversity

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ነባር ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚካሔደው መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

የተከታታታይ (የማታ እና የቅዳሜና እሑድ) ትምህርት ፕሮግራሞች ነባር ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 22 እና 23/2017 ዓ.ም የሚካሔድ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሁሉም ፕሮግራሞች የዘገዩ ተማሪዎች ምዝገባ በቅጣት መስከረም 24/2017 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን፤ የሁሉም ትምህርት መርሐግብሮች ትምህርት መስከረም 24/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

@tikvahuniversity
2024/10/03 21:28:26
Back to Top
HTML Embed Code: