Telegram Web Link
የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት መለቀቅን ተከትሎ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ የድኅረ ምረቃ አመልካቾችን ለመቀበል ማስታወቂያ እያወጡ ይገኛሉ።

አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን የመግቢያ ፈተና (NGAT) ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

(የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ያወጧቸው የጥሪ ማስታወቂያዎች ከላይ ተያይዘዋል፡፡)

@tikvahuniversity
#AAU #GAT #UAT

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዙር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) ዛሬ መስጠት ጀምሯል። ፈተናው እስከ ነገ መስከረም 16/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

ፈተናውን ለመውሰድ አመልክታችሁ ስማችሁ ያልወጣ እንዲሁም ፈተናው ላለፋችሁ አመልካቾች ቀጣይ የፈተና ቀን ወደፊት እንደሚያሳውቅ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ሦስተኛ ዙር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) በቅርቡ ይሰጣል ማለቱ አይዘነጋም።

በሌላ በኩል ለቅድመ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራም በማታ መርሐግብር ለመከታተል የመግቢያ ፈተና (UAT) ለምትወስዱ የፈተና ቀን ወደፊት ይገለፃል ተብሏል።

@tikvahuniversity
#DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል።

በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም በዲላ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 19 እና 20/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፤ በተለያዩ ምክንያቶች የምዝገባው ቀን የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣች ተማሪዎች ምዝገባ፣ በ2017 ዓ.ም አዲስ ከሚመደቡ ተማሪዎች ጋር የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል።

Note:
የሌሎች ነባር የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ከዚህ ቀደም በተገለጸው መሰረት መስከረም 19 እና 20/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

@tikvahuniversity
እንኳን ለደመራ በዓል አደረሳችሁ!

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የደመራ በዓል ይመኛል!

@tikvahuniversity
#ETA

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የሁለተኛ ሳምንት የዳግም ምዝገባ ሥራ ከመስከረም 13/2017 ዓ.ም ጀምሮ እያከናወነ ይገኛል።

በደመራ እና መስቀል በዓላት ምክንያት ዛሬ ሐሙስ መስከረም 16 እና ዓርብ መስከረም 17/2017 ዓ.ም የዳግም ምዝገባ ሥራ የማይኖር መሆኑን ባለሥልጣኑ ገልጿል።

የዳግም ምዝገባ ሥራው ቅዳሜ መስከረም 18/2017 ዓ.ም የሚቀጥል መሆኑ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርሲቲ የነባር የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜን አራዝሟል።

ዩኒቨርሲቲው የነባር የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም ይካሄዳል ብሎ የነበረ ቢሆንም፤ ባልተገለፀ ምክንያት የምዝገባ ጊዜው ተራዝሟል።

Note:
ነባር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች እንዲሁም የሕክምናና ጥርስ ሕክምና ተማሪዎች ምዝገባ በቀድሞው ጥሪ ማለትም መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑ ተገለጿል።

@tikvahuniversity
#DebreBerhanUniversity

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የርቀት እና ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም ማስተባበሪያ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለነባር የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከመስከረም 27 እስከ 29/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የነባር የሁለተኛ ዲግሪ የርቀት እና ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ከጥቅምት 4 እስከ 6/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
💨 ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም! ለ90 ቀን ከሚቆይ ነጻ 100ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር! ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት
  
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether
የኦሮሚያ ክልል በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የክልሉ ተማሪዎች ዕውቅና ሰጥቷል።

በክልሉ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ከ241,000 በላይ ተማሪዎች መካከል 8,520 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

ከእነዚህ ተማሪዎች ውስጥ 305 የሚሆኑ ተማሪዎች ከፍተኛ ነጥብ ማምጣታቸውን ተናግረዋል።

ከፍተኛ ውጤት ካመጡ ተማሪዎች ውስጥ ለ77 ተማሪዎች የላፕቶፕ፣ የገንዘብ እና የሜዳልያ ሽልማት ተበርክቷል።

በክልሉ የሚገኙ ሞዴል እና ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ማሳለፋቸውን ጠቅሰዋል።

@tikvahuniversity
#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን የመግቢያ ጊዜ መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ትምህርት መስከረም 22/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

Note:
ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ እንደሚደረግ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#WoldiaUniversity

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል እና የአዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜን አራዝሟል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተምራችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እና በ2017 ዓ.ም ወልድያ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለምትመደቡ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 27 እና 28/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎ ጥሪ የተላለፈ ቢሆንም፤ ምዝገባው በተለያዩ ምክንያቶች የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

Note:
የሌሎች ነባር ተማሪዎች ምዝገባ ከዚህ ቀደም በተገለፀው መሰረት መስከረም 27 እና 28/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

@tikvahuniversity
2024/09/30 09:25:59
Back to Top
HTML Embed Code: