Telegram Web Link
ራያ ዩኒቨርሲቲ የነባር መደበኛ የቅድመ ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።

ዩኒቨርሲቲው ለነባር ተማሪዎች መስከረም 13 እና 14/2017 ዓ.ም ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የፎረንሲክ ምርመራ ማዕከል ሥራ አስጀምሯል።

የማዕከሉ ሥራ መጀመር አገልግሎቱን በአካባቢው ለሚገኙ ማኅበረሰብ ለመስጠት ያስችላል ተብሏል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቻይንኛ ቋንቋ አጭር ስልጠና ምዝገባ ላይ ነው።

ስልጠናው ቅዳሜ ጠዋት ከ3:00-5:00 ለአስር ተከታታይ ሳምንት የሚሰጥ ሲሆን፤ ስልጠናውን ለሚያጠናቅቁ ሰርተፊኬት ይሰጣል።

የምዝገባ ቦታ፦
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮንፊሽየስ ኢንስቲትዩት፥ 6 ኪሎ ዋና ግቢ፣ 8ኛ ፍሉር ፎረም ህንጻ

ምዝገባ የሚያበቃው፦
መስከረም 21/2017 ዓ.ም

ስልጠናው የሚጀምረው፦
መስከረም 25/2017 ዓ.ም

የስልጠናው ቦታ፦
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ

@tikvahuniversity
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል ለአስር ተከታታይ ሳምንታት ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና አጠናቋል።

ማዕከሉ Brighter Generation ከተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር ከአምስት የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ተመርጠው ለመጡ 18 ተማሪዎች ስልጠናውን ሰጥቷል።

@tikvahuniversity
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ለመሆን ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው።

ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ራስገዝ ሲሆን ትኩረት የሚያደርግባቸው አምስት ዘርፎች ተለይተው የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጀመሩን የተቋሙ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ፍስሀ ጌታቸው (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

ግብርናና ላይፍ ሳይንስ፣ የጤና ሳይንስና ህክምና፣ ፊዚካል ሳይንስ፣ ማኅበራዊ ሳይንስና ሂዩማኒቲስ እንዲሁም የመምህራን ስልጠና የተለዩ አምስቱ ዘርፎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

የእነዚህ ዘርፎች ልየታና የስርዓተ ትምህርት ክለሳ እንደሚደረግም ጠቁመዋል።

@tikvahuniversity
#AAU #GAT

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) ሁለተኛ ዙር ፈተና ነገ መሰጠት ይጀምራል።

ፈተናው ከነገ መስከረም 15/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይሰጣል።

በጠዋት እና ከሰዓት ክፍለ ጊዜ ለሚሰጠው ፈተና የተፈታኞች ኮድና ስም ዝርዝር እንዲሁም የመፈተኛ ክፍል ከላይ ከተያያዙት ኤክሴሎች ይመልከቱ፡፡

ሦስተኛ ዙር ፈተና የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) የሚሰጥበትን ቀን በቅርቡ እንደሚያሳውቅ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#DebreMarkosUniversity

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በተቋሙ 1ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የነበራችሁ ነባር መደበኛ የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 29 እና 30/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪ ለነበራችሁ ወደፊት የምዝገባ ጥሪ እንደሚደረግ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

በ2017 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ የመግቢያ ፈተና ተፈትናችሁ የማለፊያ ውጤት ያገኛችሁ የምዝገባ ጊዜ መስከረም 29 እስከ 30/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

በተለያዩ ምክንያት ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ የመልሶ ቅበላ ፎርም ሞልታችሁ የወጣችሁ ተማሪዎች ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
Tikvah-University
Photo
በአዲስ አበባ እና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በ2017 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ ለመማር ላመለከቱ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ዛሬ ተሰጥቷል።

የመግቢያ ፈተናውን ለመውሰድ በሁለቱም ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን የተመዘገቡ 7,717 ተማሪዎች፣ በተመረጡ 42 የመፈተኛ ጣቢያዎች (ዩኒቨርሲቲዎች) መሰጠቱ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች መግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት መለቀቅን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ የድኅረ ምረቃ አመልካቾችን ለመቀበል ማስታወቂያ እያወጡ ይገኛሉ።

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲም በ2017 ዓ.ም በሁለተኛ ዲግሪ እና በሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ለአዲስ አመልካቾች አውጥቶት የነበረውን ማስታወቂያ እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም አራዝሟል።

በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉና መማር የምትፈልጉ አዲስ አመልካቾች በኦንላይን https://studentportal.bdu.edu.et ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።

አመልካቾች ለምዝገባ ሊያሟሏቸው የሚገቡ፦

✍️ የማመልከቻ ፎረም፥
✍️ የማመልከቻ ክፍያ ብር 300፥
✍️ በመንግስት ስፖንሰር ለሚማሩ የስፖንሰርሺፕ ፎርም፥
✍️ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን የመግቢያ ፈተና (NGAT) ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
✍️ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት ከምዝገባ በፊት ለባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማስላክ ይኖርባቸዋል፡፡
✍️ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሚያዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና ወስደው ማለፍ ይኖርባቸዋል፡፡

@tikvahuniversity
#WallagaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለነባር እና አዲስ ገቢ መደበኛ የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም፦

► ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች፥
► በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም
► በ2017 ዓ.ም ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ መደበኛ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
በ2017 ዓ.ም ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ መደበኛ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ብቻ በዋናው ግቢ ነቀምት ሲሆን፤ ሌሎቻችሁ በየነበራችሁበት ካምፓስ።

@tikvahuniversity
#DebreTaborUniversity

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም አንደኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የነበራችሁ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ምዝገባ ከመስከረም 28 እስከ 30/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች በ2016 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲው መሔድ ያልቻለችሁ እንዲሁም ዊዝድሮዋል መሙላት ሳትችሉ የቀራችሁ ተማሪዎች በዚህ ዓመት ትምህርታችሁን እንድትቀጥሉ ዩኒቨርስቲው ስለፈቀደ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት ማመልከት ትችላላችሁ።

Note:
በ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ዓመት የምትቀላቀሉ (በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪ የነበራችሁና የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በትምህርት ሚኒስቴር አዲስ የምትመደቡ) ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ ይደረግላችኋል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
2024/09/30 11:33:25
Back to Top
HTML Embed Code: