Telegram Web Link
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በባሌ ዞን ከሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ 70 ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየውን የስቴም ስልጠና አጠናቋል።

ስልጠናው ላለፉት ሁለት ወራት በዩኒቨርሲቲው የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ ማዕከል ተሰጥቷል።

@tikvahuniversity
በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለግብርና መረጃ ናሙና ሰብሳቢዎች እና ተቆጣጣሪዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

ስልጠናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚከናወን የግብርና መረጃ ናሙና የመሰብሰብ ፕሮጀክት፣ ሰብሳቢዎችን እና ተቆጣጣሪዎችን ለሥራው ብቁ ለማድረግ የተሰጠ ነው።

መንግሥት መሰል የግብርና ናሙና ቆጠራ ከ22 ዓመታት በፊት የሠራ ሲሆን፤ ለግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ አስፈላጊ መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ስልጠናው በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት፣ በትምህርት ሚኒስቴር፣ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በዩኒቨርሲቲዎች ትብብር የተዘጋጀ ነበር፡፡

ምስል፦ አርባ ምንጭ፣ ወልቂጤ፣ ወልድያ እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች

@tikvahuniversity
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የዲግሪ ፕሮግራም የኤክስቴንሽን ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም የአንደኛ ሴሚስተር ምዝገባ ከመስከረም 22 እስከ 24/2017 ዓ.ም ይከናወናል።

በቅጣት ምዝገባ ከመስከረም 27/2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

@tikvahuniversity
#Update

የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ይፋ ሆኗል።

በ2017 ዓ.ም የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ለሚማሩ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና ነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።

የተፈታኞች ውጤት ዛሬ ይፉ ሆኗል። ተፈታኞች የምዝገባ ቁጥር / Username በማስገባት ውጤታችሁን በተከታዩ ሊንክ መመልከት ትችላላችሁ 👇

https://result.ethernet.edu.et/ngat_result

@tikvahuniversity
#ይመዝገቡ

ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችልዎትን ስልጠና ይውሰዱ።

አምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ በአራት የስልጠና ዘርፎች የኦንላይን ስልጠና ይሰጣል፦

► በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣
► በአንድሮይድ ማበልፀግ፣
► በዳታ ሳይንስ እና
► በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ።

ስልጠናውን በተሰጠው ጊዜ (ስምንት ሳምንት) ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይበረከትላቸዋል።

ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/

@tikvahuniversity
#DebreBerhanUniversity

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 29 እና 30/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል።

በቅጣት የመመዝገቢያ ጊዜ ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም ሲሆን፤ ትምህርት ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

@tikvahuniversity
#OdaBultumUniversity

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ነባር የመደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 21 እና 22/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል።

የሪሚዲያል ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ላስመዘገባችሁ እና በ2017 ዓ.ም በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለምትመደቡ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቀን በሌላ ማስታወቂያ ወደፊት ጥሪ ይደረጋል ተብሏል።

@tikvahuniversity
👏🏽  ሞራል ለኮከቦቻችን! ቪድዮአቸውን ላይክ እያደረግን ምርጥ 20 ውስጥ እናስገባቸው!  👏🏽 

እስከ መስከረም 20/2017 ዓ.ም ብቻ!

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፦

🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበት ከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳትረሱ
📲 የTikTok ደረገጽ @Safaricomet ታግ እናድርግ

እንዝፈን! እንፖስት! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!

የአዲስ ዓመት ልዩ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ! ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮዎት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማኅበራዊ ገፅዎት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮች እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡

የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገፆችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማኅበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስትዎት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡

Tag ሲያደርጉን
ለ Facebook @TecnoEt https://www.facebook.com/share/KpViroSyJgPe1bML/?mibextid=qi2Omg
ለ Instagram @TecnoMobileEthiopia https://www.instagram.com/tecnomobileethiopia?igsh=cjdwdjQzbGlvaDV1
ለ TikTok @TecnoEt
https://www.tiktok.com/@tecnoet?_t=8pQuOpSYlGP&_r=1 ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።
በተጨማሪም #TecnoEt2017 ኪወርድን መጠቀም እንዳይረሱ!
2024/09/30 13:19:29
Back to Top
HTML Embed Code: