Telegram Web Link
የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

በፖርታል 👉 https://result.eaes.et

በአጭር የፅሑፍ መልዕክት 👉 6284

በቴሌግራም ቦት 👉 https://www.tg-me.com/EAESbot ላይ ውጤት መመልከት ይቻላል።

ብዙ ሰው ስለሚሞክር መጨናነቅ አለ። ተረጋጉና ሞክሩ።

ተማሪዎች እራሳችሁን አታስጨንቁ። ወላጆችም ልጆቻችሁን አበረታቱ።

ውጤት ከመጣ እሰየው ፤ ባይመጣም ቀጣይ አላማን ለማሳካት መስራት ይገባል። ምንም የሚፈጠር ነገር አይኖርም። በርትቶ አላማን ለማሳካት መጣር ነው።

@tikvahuniversity
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያስፈተናቸው ሁሉም ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ተማሪ ናታን ግርማ 551 (ከ600) ውጤት በማምጣት የትምህርት ቤቱን ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል፡፡

@tikvahuniversity
በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የነጋሶ ጊዳዳ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያስፈተናቸው ሁሉም ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ተማሪ ኢብሳ ተስፋ 563 (ከ600) ውጤት በማምጣት የትምህርት ቤቱን ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል፡፡

ተማሪ ኢብሳ ምትኩ 551 (ከ600)፣ ተማሪ እዮብ ፍቃዱ 539 (ከ600)፣ ተማሪ ለማ መገርሳ 517 (ከ600)፣ ተማሪ አርጁማ ጥላሁን 514 (ከ600) እና ተማሪ የሩማን ድሪባ 503 (ከ600) ከ500 በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያስፈተናቸው ሁሉም ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በትምህርት ቤቱ የተመዘገበ ከፍተኛው ውጤት 563 (ከ600) ሲሆን፤ ዝቅተኛው ደግሞ 375 (ከ600) መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያስፈተናቸው ተማሪዎች በሙሉ በላቀ ውጤት ማለፍ መቻላቸውን አሳውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ለተከታታይ አምስት ዓመታት ያስፈተናቸውን ተማሪዎች 100% ማሳለፍ መቻሉ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#BongaUniversity

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለነባር ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

የ2017 ትምህርት ዘመን የነባር ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት መስከረም 7 እና 8/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

@tikvahuniversity
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያስፈተናቸው ሁሉም ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ተማሪ ሶሪያ ተስፋዬ በትምህርት ቤቱ የተመዘገበውን ከፍተኛ ውጤት 528 (ከ600) ማምጣቷን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያስፈተናቸው ሁሉም ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ልዩ አዳሪ ያልሆነ ትምህርት ቤት በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያስፈተናቸው ሁሉም ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት ቤቱ 25 የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስፈተነ ሲሆን፤ ሁሉም ተማሪዎች ከ367 እስከ 509 ከ600 በማምጣት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣታቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
በአገር አቀፍ ደረጃ ለቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች ለ12 ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቋል፡፡

በስልጠናው 24 ሺህ የሚሆኑ የዘርፉ አሰልጣኝ መምህራን ተሳትፈዋል፡፡

ስልጠናው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩትን ጨምሮ በ18 የስልጠና ማዕከላት ተሰጥቷል፡፡

@tikvahuniversity
የ $2,000 ተሸላሚው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሳውላ ካምፓስ ተማሪ የሆነው ዮሐንስ ይኑር የ2016 ዓ.ም የብሩህ ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር አሸናፊ ሆኗል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የአውቶሞቲቭ ተማሪ የሆነው ዮሐንስ ይኑር፣ በሀገር አቀፍ ውድድሩ አሸናፊ ከሆኑት መካከል አንዱ በመሆኑ 2,000 የአሜሪካን ዶላር ተሸላሚ ሆኗል፡፡

@tikvahuniversity
🌻 በእንቁጣጣሽ ልብሳችን ፏ ብለን ወደ TikTok ሄደን ተሰጥዖአችንን እናሳይ!
እስከ መስከረም 18/2017 ዓ.ም ብቻ!

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፦

🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትን ከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳትረሱ
📲የTikTok ደረ-ገጽ @Safaricomet ላይ ታግ እናድርግ! እንዝፈን! እንላክ! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit #FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
#MizanTepiUniversity

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው መስከረም 06 እና 07/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
የእቴጌ መነን የሴት ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤት እና ገላን የወንድ ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤት በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 100 ፕርሰንት ተማሪዎችን ማሳለፍ ከቻሉት ውስጥ ናቸው።

@tikvahuniversity
በስልጤ ዞን ሀይራንዚ ልዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ፈተና ያስፈተናቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማሳለፍ ችሏል።

ከሀይርአንዚ ልዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ2016 12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱት 104 ሲሆኑ 5 ተማሪዎች 500 እና በላይ አምጥተዋል።

ከ450 እስከ 499 ደግሞ 36 ተማሪዎች ናቸው።

ከ400 እስከ 449 ያመጡ 40 ተማሪዎች ናቸው።

ከ350 እስከ 399 ያመጡ 19 ተማሪዎች ናቸው።

ከ312 እስከ 349 ያመጡት 04 ተማሪዎች ናቸው።

በት/ት ቤቱ ከ600 የተመዘገበ ከፍተኛ ውጤት 511 ሲሆን ዝቅተኛው ውጤት ደግሞ 312 ነው።

የዘንድሮ ከፍተኛ ወጤት የተመዘገበው በሴት ተማሪ ነው።

ስልጤ ኤፍኤም

@tikvahuniversity
2024/10/01 11:25:46
Back to Top
HTML Embed Code: