Telegram Web Link
ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በ2016 ዓ.ም ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ያስፈተናቸዉን ሁሉንም ተማሪዎች አሳልፏል።

በ2016 ዓ.ም በክልል እና በሀገር ደረጃ የተሰጡትን የ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ፈተናዎች ሁሉንም ተማሪዎች በከፍተኛ ዉጤት አሳልፏል።

የትምህርት ቤቱ ከፍተኛዉ ዉጤት 544/600 ሲሆን ዝቅተኛዉ 361/600 ሆኖ ተመዝግቧል።

@tikvahuniversity
በአማራ ክልል ደብረብርሃን የሚገኘው የኃይሌ ሚናስ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ያስፈተናቸው ሁሉም ተማሪዎቹ አልፈዋል።

በአዳሪ ትምህርት ቤቱ የመጀመሪያ ዙር የሆኑት 20 ሴት እና 13 ወንድ ተማሪዎች በ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ወስደዋል፡፡

ተማሪ ሳሮን ስዩም 564 ውጤት በማምጣት የአዳሪ ትምህርት ቤቱን ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች፡፡

@tikvahuniversity
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛው ውጤት በትግራይ ክልል የቓላሚኖ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪው ዮናስ ንጉሰ አስመዝግቧል፡፡

በትግራይ ክልል ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ700 መሰጠቱ ይታወሳል።

ተማሪ ዮናስ ንጉሰ 675 ከ700 በማምጣት በሀገር ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ የተባለውን ውጤት አምጥቷል።

ሌላኛዋ የቓላሚኖ ተማሪ ሔለን በርኸ 662 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች። ሌሎች የቓላሚኖ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ማምጣታቸው ተሰምቷል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
የኦሮሚያ ልማት ማህበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ያስፈተናቸውን ሁሉንም ተማሪዎችን አሳልፏል።

በርካታ ተማሪዎችም ከፍተኛው ውጤት አስመዝግበዋል።

@tikvahuniversity
ከ600 ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበችው ተማሪ

በአዲስ አበባ የኦግዝሌየም ካቶሊክ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነችው ሲፈን ተክሉ፤ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ የሆነውን ውጤት አስመዝግባለች፡፡

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዋ ሲፈን ተክሉ 575 ውጤት ከ600 በማምጣት ከፍተኛ የተባለውን ውጤት አሳክታለች።

የስርዓተ ምግብ ባለሙያ የመሆኑ ዝንባሌ እንዳላት የምትናገረው ተማሪ ሲፈን፤ "ጌዜዬን ትምህርት ላይ በማሳለፌ፣ በቡድን በማጥናቴ እንዲሁም የቤተሰብና የመምህራኖቼ ድጋፍ ለዚህ ስኬት አብቅቶኛል" ብላለች። #AMN

@tikvahuniversity
#DireDawaUniversity

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ መደበኛ ነባር ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ መደበኛ ነባር ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው ከመስከረም 8-10/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ልዩ አዳሪ ያልሆነ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ዘንድሮ ያስፈተናቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በሙሉ የዩነቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ተማሪዎቹ ከ500 በላይ ውጤት ማምጣት እንደቻሉም ነው ዩኒቨርሲቲው የገለፀው፡፡

@tikvahuniversity
በሃዲያ ዞን የሚገኘው ሊች ጎጎ የልህቀት አዳሪ ትምህርት ቤት በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ሁሉም ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸው ተገልጿል።

558 ከፍተኛው ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል።

@tikvahuniversity
በሲዳማ ክልል ሀዋሳ የሚገኘው ሀዮሌ ልዩ ትምህርት ቤት ያስፈተናቸው ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት አስመዝግበዋል።

570 ከፍተኛው ውጤት በተማሪ ዳኒ ጃፈር መመዝገቡን ትምህርት ቤቱ ለቲክቫህ ገልጿል።

ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን ሲያደርሰን ይቀርባል።

@tikvahuniversity
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ልዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች መካከል 98 በመቶ የሚሆኑት የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሆሞሻ ወረዳ የሚገኘው 'ፋሮ የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት' ዘንድሮ ያስፈተናቸውን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በመሉ ማሳለፍ መቻሉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity
ቤተሰብ አካዳሚ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች ውስጥ በጅማ ካምፓስ ያስፈተናቸውን ተማሪዎች በሙሉ አሳልፏል።

በአዲስ አበባ ካምፓስ ካስፈተናቸው ተማሪዎች መካከል 97 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን አካዳሚው ለቲክቫህ ገልጿል፡፡

አካዳሚው በአጠቃላይ 197 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተና አስፈትኗል።

@tikvahuniversity
በራያ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ፕሮግራም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 14 ተማሪዎች መካከል 13ቱ የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል በ2016 ዓ.ም ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያስቀመጣቸው ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ አልፈዋል፡፡

በማዕከሉ የተመዘገበው የዓመቱ ከፍተኛ ውጤት 557 ሲሆን፤ ትንሹ ደግሞ 395 መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። ሌሎች ተማሪዎች ከ419 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

ዘንድሮ በማዕከሉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከተፈተኑት ውስጥ 42.55 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስቲም ማዕከል በዚህ ዓመትም ለ3ኛ ጊዜ በተደጋጋሚ ሁሉንም ያስፈተናቸውን ተማሪዎች ማሳለፍ መቻሉን ገልጿል።

@tikvahuniversity
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ሁሉም የጤና ሳይንስ ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 11 እና 12 /2017 ሲሆን ትምህርት መስከረም 13 ይጀምራል።

@tikvahuniversity
2024/10/01 13:31:32
Back to Top
HTML Embed Code: