Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#Urgent🚨

ኢትዮጵያዊው ተማሪ ጣሊያን ሀገር ለትምህርት በሄደበት ህይወቱ አልፎ ተገኘ።

የ22 ዓመቱ አቤኔዘር ተሰማ አበበ በትምህርት ጉዳይ በስኮላርሺፕ ነው ወደ ጣሊያን ሀገር፣ ሲሲሊ ግዛት ያቀናው።

በመሲና ዩኒቨርስቲ የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ ነበር።

ከትላንትና በስቲያ ማታ እንደተኛ ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል።

የህልፈቱን ምክንያት ፖሊስ እየመረመረ እንደሚገኝ ጉዳዩን ከሚያውቁ የቅርብ ቤተሰቦቹ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

የተማሪ አቤነዘር አስክሬንን ወደ ሀገር ቤት ለመምጣት ወጪው ከፍተኛ እንደሆነ ከቤተሰቦቹ ለመረዳት ተችሏል።

ቤተሰብ በታላቅ የልብ ስብራት ውስጥ ስለሚገኝ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ የምትገኙ ኢትዮጵያን እንድትረባረቡ ጥሪ ቀርቧል።

ጎፈንድሚ https://gofund.me/01490b2f

አቶ ተሰማ አበበ 1000020084913 (ንግድ ባንክ)

አቶ ተሰማን በስልክ ማግኘት የምትፈልጉ በ 0911817718 ላይ መደወል ይችላል።

ነፍስ ይማር !

@tikvahethiopia
🤩🎧 ማነው አሪፍ ድምፅ አለኝ የሚለው? እስቲ ቲክቶክ ላይ ፖስት አድርጉና ችሎታችሁ ይታይ! በብዛት የሚታዩት ቪዲዮዎች የገንዘብ ሽልማት እና በታዋቂ አርቲስቶች የመሰልጠን ዕድል ያስገኛሉ!

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፦
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትን ከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳትረሱ
📲 የTikTok ደረ-ገፅ @Safaricomet ታግ እናድርግ! እንዝፈን! እንላክ! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
#BahirDarUniversity

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ለመሆን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች የሚያከናውን ጽ/ቤት ከፍቷል፡፡

የዩኒቨርሲቲውን የራስ ገዝነት ጉዞን ዕውን ለማድረግ ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱን የተቋሙ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ከዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ክፍል ዲኖች እና ኃላፊዎች ጋር በ2017 የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ዘርፍ የትኩረት መስኮች ላይ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው ይህን የገለፁት፡፡

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመቀጠል ራስ ገዝ ከሚሆኑ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች መካካል ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity
#AddisAbabaUniversity

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ የመሆን ጉዞውን የመጀመሪያ ምዕራፍ በመስከረም 2017 ዓ.ም ያጠናቅቃል፡፡

በተቋሙ የራስ ገዝነት የእስካሁን ጉዞ ላይ የዩኒቨርሲቲው ቻንስለር፣ ፕሬዝዳንት፣ የቦርድ አመራሮች፣ የሴኔት አባላት እና የኮሌጅ ዲኖች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ባከናወናቸው አበይት ተግባራት እና በገጠሙ ፈተናዎች እንዲሁም በቀጣይ በሚሠሩ ተግባራት ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የራስ ገዝነት የመጀመሪያ ምዕራፍ በመስከረም 2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል የተባለ ሲሆን፤ ቀሪ ተግባራት በሁለት ምዕራፎች እስከ ሐምሌ 2017 ዓ.ም ይፈፀማል ተብሏል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን የፈቀደው ማቋቋሚያ ደንብ ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት መተላለፉ ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity
የመንግሥት ትምህርት ቤቶችን ከግል ትምህርት ቤቶች ጋር በጥራት ደረጃ እኩል ለማድረግ እንዲሠራ የትምህርት ሚኒስትሩ ጥሪ አደረጉ፡፡

የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከግል ትምህርት ቤቶች በጥራት ደረጃ የተሻሉ የሚሆኑበት አሠራር መፈጠር አለበት ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ትናንት በተጠናቀቀው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ 31ኛ ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ላይ ተናግረዋል፡፡

የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ያላቸውን ሰፊ መሠረተ ልማት ተጠቅመው የትምህርት ጥራቱን ለማስጠበቅ መስራት አለባቸው ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ የሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከግል ትምህርት ቤቶች ጋር እኩል ለማድረግ በቀጣይ ዓመታት በትኩረት እንደሚሠራ ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል የመምህራን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማስጠበቅ የመምህራን ባንክ የማቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩን ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

@tikvahuniversity
#Update

በ2017 የትምህርት ዘመን የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ያላቸሁና በተለያዩ ምክንያቶች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ያመለጣችሁ አመልካቾች እስከ ነሐሴ 26/2016 ዓ.ም ድረሰ በ https://ngat.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

አመልካቾች በየተመደባችሁበት የፈተና ማዕከላት እና የመፈተኛ ፕሮግራም መሰረት ከነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም ድረስ ፈተናው የሚሰጥ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ለፈተና ወደ ማዕከላት ስትሔዱ የተሰጣችሁን User Name and Password እንዲሁም ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ መያዝ ይጠበቃባችኋል።

@tikvahuniversity
የቴክኒክና ሙያ መምህራን የአሰልጣኝ መምህራኖች ስልጠና ዛሬ ተጀምሯል፡፡

"ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት" በሚል መሪ ሃሳብ የሚሰጠው ስልጠና፤ በዘርፉ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂዎችና አዳዲስ እሳቤዎች ላይ የአሰልጣኞችን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በ 17 የስልጠና ማዕከላት በሚሰጠው ስልጠና፣ 24 ሺህ የሚጠጉ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች እንደሚሳተፋ ይጠበቃል፡፡

ስልጠናው ከዛሬ ነሐሴ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 3/2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡

@tikvahuniversity
33ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ መድረክ በአዲስ አበባ መካሔድ ጀምራል።

"ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም" በሚል መሪ ሀሳብ ላይ የሚመክረው መድረኩ፤ በትምህርት ሚኒስቴር እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡

@tikvahuniversity
በሲዳማ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2017 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ተጀምሯል፡፡

በሲዳማ ክልል 1.3 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለማስተማር ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በየነ በራሳ ተናግረዋል፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 1.1 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመቀበል መታቀዱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደስታ ገነሜ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መፃሕፍት ለተማሪዎች ተደራሽ የተደረገ ሲሆን፤ የአካባቢ ቋንቋ ትምህርት መፃሕፍት ህትመት እየተከናወነ እንደሚገኝ ኃላፊዎቹ ጠቁመዋል። #FBC

@tikvahuniversity
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017 የትምህርት ዘመን 362 ሺህ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዕቅድ ተይዟል፡፡

በክልሉ በ2016 ዓ.ም በፀጥታ ችግር ምክንያት 52 ትምህርት ቤቶች ዝግ እንደነበሩ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ተመስገን ዲሳሳ (ዶ/ር) ፣ በአሶሳ ከተማ መካሔድ በጀመረው 26ኛ ክልል አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ ተናግረዋል፡፡

በ2017 የትምህርት ዘመን ሁሉንም ትምህርት ቤቶች ሥራ በማስጀመር ከትምህርት ርቀው የነበሩ ተማሪዎችን የመመለስ ሥራ ይሠራል ብለዋል።

በግጭት ምክንያት የወደሙ እስከ 200 የሚጠጉ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
ለቻርጀር መሯሯጥ ድሮ ቀረ! ገና ቀኑ ሳይጋመስ የሚያልቅ ባትሪ አላማረራችሁም? እንግዲያውስ ቅመም Itel Pro ለእናንተ ነው! ባለ የ4000mAh የባትሪ አቅም ያለው ቅመም Itel በአንድ ጊዜ ቻርጅ ብቻ ለሁለት ቀናት እንደልባችሁ ስልካችሁን መጠቀም ያስችላችኋል! ቅመም Itel Pro በሔዳችሁበት ሁሉ አብሯችሁ ነው!
በሀረሪ ክልል ለ2017 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 27/2016 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 5/2016 ዓ.ም ይከናወናል፡፡

የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የተማሪዎች ምዝገባ ቅስቀሳን በዛሬው ዕለት በኤረር ወረዳ አስጀምሯል።

የቅስቀሳ ሥራው በክልሉ በሚገኙ በሁሉም ወረዳዎች በቀጣይ ቀናት እንደሚከናወን ቢሮው ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
በአገር አቀፍ ደረጃ ለቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች እየተሰጠ የሚገኘው የአቅም ግንባታ ስልጠና በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ውስጥ በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

ስልጠናው ከሚሰጥባቸው 18 የስልጠና ማዕከላት መካከል አንዱ በሆነው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት 1,200 አሰልጣኞች እየሰለጠኑ ይገኛሉ፡፡

ስልጠናው ''ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት'' በሚል መሪ ሃሳብ እስከ ጳጉሜን 3/2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡

@tikvahuniversity
ችሮታው አየለ (ዶ/ር) የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሁነው ተሹመዋል፡፡

በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን ነሐሴ 21/2016 ዓ.ም ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤ እንደሚያሳየው፣ ችሮታው አየለ (ዶ/ር) ከነሐሴ 22/2026 ዓ.ም ጀምሮ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሠሩ ተመድበዋል።

ችሮታው አየለ (ዶ/ር) ላለፉት ስድስት ዓመታት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ችሮታው አየለ (ዶ/ር) ዲላ ዩኒቨርሲቲን በመሩበት ወቅት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስርዓት እንዲሰፍን፣ የማኅበረሰብ አቀፍ ሥራዎች እንዲስፋፉ እና በርካታ የውስጥ አሰራር ስርዓቶች እንዲዘረጉ በማድረግ ከፍተኛ አበርክቶ እንደነበራቸው ከዲላ ዩኒቨርሲቲ የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡ ከነቀፌታ የፀዳ የኦዲት አስተያየት ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ተቋሙ እንዲያሳካ ያስቻሉ መሪ መሆናቸውም ተገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/10/03 17:22:15
Back to Top
HTML Embed Code: