Telegram Web Link
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ ለ2017 የትምህርት የዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ማካሔድ ጀምሯል፡፡

ምዝገባው በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ከዛሬ ነሐሴ 20/2016 ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 5/2016 ዓ.ም ይካሔዳል ተብሏል።

እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዲሄዱ ለማድረግ በክልሉ የሚገኙ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ የትምህርት ዘርፍ አመራሮች እና ባለሙያዎች የድርሻቸውን እንዲወጡ ቢሮው ጠይቋል።

@tikvahuniversity
ክቡር ኮሌጅ የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ላጠናቀቁ ከ 600 በላይ ተማሪዎች ልዩ የክህሎት ስልጠና በነፃ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ስልጠናው ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚያደርጉት ሽግግር በመሰረታዊ የህይወትና የቴክኖሎጂ ክህሎት ብቁ እንዲሆኑ ለማድረግ በማሰብ የተዘዘጋጀ ነው፡፡

እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩትን የትምህርት መስክ እንዴት መምረጥ እንዳለባቸው የሚያግዝ ስልጠና መሆኑ ተገልጿል።

በአምስት የክህሎት ዘርፎች ማለትም የአመራር ክህሎት፣ የሥራ ፈጣሪነት አስተሳሰብ፣ ዲጂታል ማርኬቲንግ፣ ግራፊክስ ዲዛይን እና ፕሮግራሚንግ የተዋቀረውን ሰልጠና፣ ከ 65 የግል እና የመንግሥት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ ከ 600 በላይ ተማሪዎች በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡

@tikvahuniversity
በሶማሊ ክልል የ2016 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

በ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 34,073 ተማሪዎች መካከል 19,977 (50.8 በመቶ) ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

በተመሳሳይ በክልሉ የ6ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 28,483 ተማሪዎች መካከል 22,828 (80 በመቶ) ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ጉሌድ አህመድ ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
#MoE

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራር ምደባ ሲያደርጉ ችሎታ እና ብቃት ያላቸውን ሴቶች ወደ ከፍተኛ አመራር ደረጃ በብቃታቸው መሠረት የሚሸጋገሩበት ሁኔታን ታሳቢ እንዲያደርጉ ትምህርት ሚስቴር አሳሰበ፡፡

በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመካከለኛ አመራር ደረጃ ያሉ አመራሮችን ወደ ከፍተኛ አመራር ለማሸጋገር ግብ ያደረገ ስልጠና ለ 150 ሴቶች መሰጠቱን ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡

በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የቦርድ ሰብሳቢዎች የተላከ ሰርኩላር፣ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በከፍተኛ አመራርነት ያሉ የሴት አመራሮች ድርሻ ከ 11 በመቶ ወደ 8 በመቶ ዝቅ ማለቱን ይጠቁማል፡፡

ስለሆነም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ሴቶችን በማብቃት ወደ ከፍተኛ አመራር ደረጃ እንዲሻገሩ ማድረግ ላይ በልዩ ትኩረት እንዲሰሩ ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል፡፡

(ሚኒስትር ዴኤታው ለ 46 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የቦርድ ሰብሳቢዎች የፃፉት ሰርኩላር ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
#WachemoUniversity

ሳራ ሽኩር ሙዘይን (ዶ/ር) የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ፣ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሠሩ በዩኒቨርሲቲው የሥራ አመራር ቦርድ ተወክለዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ብርሃኑ መገርሳ (ዶ/ር) በቀን ነሐሴ 20/2016 ዓ.ም ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤ፣ ሳራ ሽኩር ሙዘይን (ዶ/ር) ከነሐሴ 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ የተወደከሉ መሆናቸውን ያሳያል፡፡

(የውክልና ደብዳቤው ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
#BahirDarUniversity

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኦሪጅናል ዲግሪ እንዲሠራላችሁ በ45ኛ ዙር የጠየቃችሁ 106 አመልካቾች ኦሪጅናል ዲግሪያችሁ የደረሰ በመሆኑ መውሰድ እንደምትችሉ አሳውቋል፡፡

ኦሪጅናል ዲግሪ ለመውሰድ ስትሔዱ ክሊራንስ እና ቴምፖራሪ ኦርጅናሉን መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

(ኦሪጅናል ዲግሪ የደረሰላችሁ አመልካቾች ስም ዝርዝር ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
24 ሺህ ለሚሆኑ የቴክኒክና ሙያ መምህራን የሙያ ልህቀት ስልጠና ሊሰጥ ነው፡፡

12 ተከታታይ ቀናት በሚሰጠው ስልጠና፤ 23,957 የቴክኒክና ሙያ መምህራን እንደሚሳተፉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ተናግረዋል፡፡

ሰልጣኞች በስልጠናው አዲሱን የትምህርትና ስልጠና ፖሊስ በደንብ እንዲረዱ እንደሚደረግ ሚኒስትሯ ገልፀዋል።

ስልጠናው ከነገ ነሐሴ 22/2016 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 3/2016 ዓ.ም ድረስ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 17 ማዕከላት ይሰጣል፡፡

@tikvahuniversity
#MoE

ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲማሩ ሊደረግ ነው፡፡

በ2017 የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የግል እና የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች (የአምስት እና የስድስት ዓመት ህፃናት) የእንግሊዘኛ ትምህርት እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡

በ2015 ዓ.ም ወደ ትግበራ የገባው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ብቻ እንዲማሩ የሚያስገድድ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በመጪው የትምህርት ዘመን የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት መማር እንደሚጀምሩ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) በ31ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ጉባኤ ላይ ተናግረዋል፡፡

"ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቁና ተወዳዳሪ ለማድረግ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ በእንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲማሩ እናደርጋለን" ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡ #ShegerFM

@tikvauniversity
በድሬዳዋ አስተዳደር የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምዝገባ ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም ይጀመራል፡፡

አስተዳደሩ በ2017 የትምህርት ዘመን በአንደኛ ደረጃ፣ በመካከለኛ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ137 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር አቅዷል፡፡

በአስተዳደሩ የሚገኙ በርካታ የግል ትምህርት ቤቶች የተማሪ ምዝገባ አካሒደው ወደማጠናቀቁ መቃረባቸውን የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሱልጣን አሊይ ተናግረዋል፡፡

የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምዝገባ ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም የሚጀመር ሲሆን፤ በአስተዳደሩ ሁሉም አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ ቅስቀሳ መጀመሩን ገልፀል፡፡

@tikvahuniversity
2024/10/03 15:35:17
Back to Top
HTML Embed Code: