Telegram Web Link
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የብሩህ ኢትዮጵያ የፈጠራ ሀሳብ ውድድር የመክፈቻ ስነ-ስርዓት አካሒዷል።

በውድድሩ ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ 150 ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ።

በአገር አቀፍ ደረጃ 1,375 የሚሆኑ የንግድ የፈጠራ ኃሳብ ባለቤቶችን በማወዳደር፣ 150 ወጣቶች የተመለመሉ ሲሆን፤ እነዚህ 150 ወጣቶች የሚወስዱት የሁለት ሳምንት ስልጠና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጀምሯል።

ከእነዚህ ወጣቶች መካከል በውድድር የተሻለ አፈጻጸም ለሚያስመዘገቡ 50 የንግድ ፈጠራ ኃሳብ ባለቤቶች ለእያንዳንዳቸው 2,000 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለክረምት መርሐግብር ሠልጣኞች የመውጫ ፈተና ሰጥቷል።

የኢንስቲትዩቱ የክረምት መርሐግብር ሰልጣኞች በተቋሙ ዋና ግቢ፣ በአዲግራት፣ በባህር ዳር፣ በራያ፣ በወልቂጤ እና በወሎ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የመውጫ ፈተና መውሰዳቸውን ኢኒስቲትዩቱ ገልጿል።

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለግብርና መረጃ ናሙና ሰብሳቢዎች እና ተቆጣጣሪዎች ስልጠና መስጠት ጀምረዋል፡፡

ስልጠናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚከናወን የግብርና መረጃ ናሙና የመሰብሰብ ፕሮጀክት፣ ሰብሳቢዎችን እና ተቆጣጣሪዎችን ለሥራው ብቁ ለማድረግ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሰልጣኞቹ በአቅራቢያቸው ወደሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በመሔድ ስልጠናውን መከታተል እንደጀመሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ስልጠናው በትምህርት ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት እና በዩኒቨርሲቲዎቹ ትብብር እየተሰጠ ሲሆን፤ እስከ መስከረም 05/2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል፡፡

ምስል፦ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣ አርሲ ዩኒቨርሲቲ እና ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Tikvah-University
በአማራ ክልል የ2017 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ ዛሬ ነሐሴ 20/2016 ዓ.ም ይጀመራል።

ለ2017 የትምህርት ዘመን 6.9 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመዝገብ መታቀዱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መግለፁ ይታወቃል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ገበታቸው የራቁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ያድርጉ፡፡ ተማሪዎች ምዝገባ እንዲያደርጉ ያበረታቱ፡፡

@tikvahuniversity
በአማራ ክልል መደበኛ የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 20 እስከ 24/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡

በክልሉ ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል ሰባት ሚሊዮን ተማሪዎችን ለማስተማር ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡

መደበኛ የተማሪዎች ምዝገባ እስከ ነሐሴ 24/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን የገለፁት ኃላፊዋ፤ እስከ ጳጉሜን/2016 ባሉት ቀናት ደግሞ ተጨማሪ ማስረጃ የሚያስፈልጋቸውን ተማሪዎቾ የማጥራት ሥራ ይከናወናል ብለዋል፡፡

መስከረም 7/2017 ዓ.ም መደበኛ የመማር ማስተማር ሒደቱ እንደሚጀምር ኃላፊዋ ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ
#MattuUniversity

መቱ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

► የሥራ መደብ፦ በተለያዩ የሙያ መስኮች
► ተፈላጊ መምህራን ብዛት፦ 67
► ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ
► የሥራ ቦታ፦ መቱ እና በደሌ

መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች በመቱ ዩኒቨርሲቲ የብቃትና የሰው ሀብት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ ቁጥር 7 እና 26 እንዲሁም በበደሌ ካምፓስ የሰው ሀብት ቢሮ እና በፖ.ሳ.ቁጥር 318 በመላክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

(መቱ ዩኒቨርሲቲ ያወጣው ሙሉ ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
2024/10/03 13:23:46
Back to Top
HTML Embed Code: