Telegram Web Link
🔥 ትኩስ የስፖርት ዜናዎችን በቀላሉ በSMS እናግኝ! 💬

ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30001 SMS በመላክ አሁኑኑ Elite ስፖርትን እንቀላቀል ! በቀን 2 ብር ብቻ!

በ Elite ስፖርት በሽ ዜናዎች

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለሦስት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት የማዕረግ ዕድገት ሰጥቷል።

የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ የዶ/ር ቢንያም ጫቅሉ፣ ዶ/ር ቡሻ ታአ እና ዶ/ር ሰፊነው ዓለሙን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ዕድገት አፅድቋል።

ሙሉ ፕሮፌሰር የሆኑ ምሁራን፦

1. ፕ/ር ቢንያም ጫቅሉ - በዲጂታል ሔልዝ እና ኢምፕሊመንቴሽን ሳይንስ
2. ፕ/ር ቡሻ ታአ - በሶሲዮሎጂ
3. ፕ/ር ሰፊነው ዓለሙ - በቬተሪናሪ ኢፒዲሞሎጂ እና ኢኮኖሚክስ

@tikvahuniversity
የጤና ሙያተኞች የሙያ ብቃት ምዘና ውጤት በቀጣይ ሳምንት ይፋ ይደረጋል፡፡

ጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር በጋራ በመሆን ከመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለያዩ የጤና ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ የጤና ተማሪዎች የሙያ ብቃት ምዘና ሰኔ 19/2016 ዓ.ም መስጠታቸው ይታወቃል፡፡

በ17 የጤና ሙያዎች የተሰጠውን ፈተና 15 ሺህ የሚጠጉ ተመዛኞች መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡

ከምዘናው እርማት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በዚህ ሳምንት ተጠናቀው፤ ውጤቱ በቀጣይ ሳምንት ይፋ እንደሚደረግ በጤና ሚኒስቴር የጤናና ጤና-ነክ ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ እንዳልካቸው ፀዳል ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity
የክረምት ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና በ28 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተሰጠ ነው፡፡

ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮችና መምህራኖች እየተሠጠ የሚገኘው ልዩ የአቅም ማሻሻያ ስልጠናው ዛሬ አራተኛ ቀኑ ላይ ደርሷል፡፡

ስልጠናው ለትምህርት ቤት አመራሮች ለአስር ቀናት እንዲሁም ለመምህራን ለሃያ ቀናት እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

ምስል፦ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
በ12 ብር ብቻ 400 MB የእለታዊ ኢንተርኔት ፓኬጅ በM-PESA ስንገዛ፣  እስከ 50% ነፃ ተጨማሪ ዳታ እንፈስ!

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom  #FurtherAheadTogether
Tikvah-University
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ አድርጓል። በአስተዳደሩ የ8ኛ ክፍል ፈተና የማለፊያ ነጥብ ለወንድ ተማሪዎች 50%፣ ለሴት ተማሪዎች 47% እንዲሁም ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች 45% እንደሆነ ቢሮው አሳውቋል። በዚህም በአስተዳደሩ በ2016 ዓ.ም ለፈተና ከቀመጡ 9,085 ተማሪዎች መካከል 5,673 ተማሪዎች ወይም 62.43 በመቶዎቹ ማለፋቸውን…
የድሬዳዋ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን ይፋ አድርጓል፡፡

ተማሪዎች ከታች ባለው ሊንክ አማካኝነት መለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤት መመልከት ይችላሉ ተብሏል፡፡

ውጤት ለመመልከት 👇
https://www.gsix.diresrms.org/View_Result/get_result

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ8,500 በላይ ተማሪዎችን ነገ ያስመርቃል፡፡

ተመራቂዎቹ በፒኤችዲ፣ በማስተርስ እና በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም በመደበኛው፣ በክረምት፣ በተከታታይ እና በርቀት መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 58 በስፔሻሊቲ እና 4 በሰብ-ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን ሐኪሞችም ያስመርቃል፡፡ በተጨማሪም በህክምና አመራርነት 6 ምሩቃንን በሰርትፍኬት ያስመርቃል፡፡

@tikvahuniversity
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የ 'PGDT' የክረምት መርሐግብር አመልካቾች ምዝገባ ከሐምሌ 26 እስከ 28/2016 ዓ.ም እንደሚካሔድ ገልጿል።

ትምህርት ሰኞ ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ያደርጋል። የኢንስቲትዩቱ የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች እንዲሁም ዳግም ተፈታኞች የዛሬ ወር የመውጫ ፈተና መውሰዳቸው ይታወቃል። "ኢንስቲትዩቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመውጫ ፈተናው ላይ እየተወያየ መሆኑንና ውይይቱ ሲጠናቀቅ የተፈታኞች ውጤት እንደሚገለፅ" ነግረናችሁ ነበር። ተቋሙ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የነበረው…
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል።

የኢንስቲትዩቱ የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች እንዲሁም ዳግም ተፈታኞች የዛሬ ወር የመውጫ ፈተና መውሰዳቸው ይታወቃል።

ኢንስቲትዩቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመውጫ ፈተናው ላይ ውይይት ሲያደርግ መቆየቱ ለውጤቱ መዘግየት ምክንያት ሆኗል።

አሁን ላይ "ውጤቱ የተለቀቀ ስለሆነ፣ የተቋሙ ሬጅስትራር በመሔድ ማየት እንደሚችሉ" ኢንስቲትዩቱ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግሯል።

@tikvahuniversity
#BahirDarUniversity

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።

ተመራቂዎቹ በመደበኛው፣ በክረምት፣ በተከታታይ እና በርቀት መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው፡፡

አጠቃላይ ተመራቂዎች - 8,524
በፒኤችዲ - 82
በማስተርስ ዲግሪ - 1,119
በመጀመሪያ ዲግሪ - 2,589
በስፔሻሊቲ እና ሰብ-ስፔሻሊቲ - 62
በፒጂዲቲ - 4,334
በኤችዲፒ - 96
በአመራር ሰርተፊኬት - 6
በማሪታይም- 234

@tikvahuniversity
#ነፃ_የፌሎውሺፕ_ዕድል

ከዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ተመርቀዋል? የማኅበረሰብ ለውጥ ለማምጣት ፍላጎት አለዎት?

እንግዲያውስ ለዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ምላሽ የአመራር ፌሎውሺፕ ፕሮግራም ያመልክቱ።

ለሁለት ዓመት የሚቆየው ፌሎውሺፕ ፕሮግራሙ የአደጋ ተጋላጭነት አስተዳደር ክህሎትና ልምድ እንዲያጎለብቱ ያስችልዎታል።

በዘርፉ ባለሙያዎች ስልጠና የሚያገኙ ሲሆን፤ በፕሮጀክቶች ላይ በመስራት ከዘርፉ ሙያተኞች ጋር ትስስር እንዲፈጥሩ ይደረጋል።

ስለፌሎውሺፕ ፕሮግራሙ መረጃ ለማግኘት 👇
https://drive.google.com/file/d/12fK_rTrR37tfEasG7tPd4Sm--4L2jkeu/view?usp=drive_link

ኦንላይን ለማመልከት 👇
https://docs.google.com/forms/d/1QJflHITYBmP_dxSQRTWhUsGZoHRQashTNqMsIOd2zZI/edit

የማመልከቻ ጊዜው የሚያበቃው 👇
ነሐሴ 5/2016 ዓ.ም

@tikvahuniversity
#Infinix_Note40_Pro_Plus

ነሐሴ 4 ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በቃና ስቱዲዮ የተደገሰው ልዩ የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G የሙዚቃ እና የጌም ድግስ የትም ይሁኑ የት ማይቀርበት ነው፡፡ በተለያዩ የጌም ቶርናመንቶች አዲሱን የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልክን ጨምሮ በሽልማቶች የሚንበሸበሹበት፤ እነ ዲጄ ሚላ፣ ዮን ዜማ፣ ፍላሽ ኪዶ፣ ዲጄ ፔርዱ፣ ሳጂ እና አብሌር በመድረኩ የሚነግሱበት ደማቅ ምሽት ተዘጋጅቷል፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሰቲ 544 ተማሪዎችን አስመረቀ።

ተመራቂዎቹ በድኅረ ምረቃ እና በቅድመ ምረቃ መርሐግብር በተለያዩ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

በዚህም 388 የድኅረ ምረቃ እና አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ያለፉ 156 የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በድምሩ 544 ተማሪዎች ተመርቀዋል።

በዚህ ዓመት በጥር እና በሰኔ ወር የተሰጡ የመውጫ ፈተናዎች ያለፉ ተፈታኞች ቁጥር ከ60% በላይ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/10/04 09:29:03
Back to Top
HTML Embed Code: