Telegram Web Link
#EAES

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

"በወረቀት እና በበይነ መረብ እየተሰጠ ያለው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና፥ በሰላምና እጅግ በጣም በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል" ብሏል አገልግሎቱ።

በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ ክልል እየተሰጠ ያለው የመልቀቂያ ፈተና ነገ ከሰዓት በፊት እንደሚጠናቀቅ አገልግሎቱ ገልጿል።

አገልግሎቱ በፈተና የመስጠት ሒደቱ ለተሳተፉ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ትምህርት ቢሮዎች፣ የፀጥታና ደህንነት ተቋማት፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮጵያ መብራት ኃይል፣ የፈተና አስፈጻሚዎች፣ አመራሮች እና ተማሪዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ የተፈታኞች አሸኛኘት በፎቶ

የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች አሸኛኘት በኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት

@tikvahuniversity
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለማታ እና ቅዳሜና እሁድ ነባር ተማሪዎች አውጥቶት የነበረውን የምዝገባ ጥሪ በቀናት አራዝሟል።

ኢንስቲትዩቱ የ1ኛ፣ 2ኛ፣ 4ኛ እና 5ኛ ዓመት የማታ እንዲሁም የቅዳሜና እሁድ ተማሪዎች ምዝገባ ከሐምሌ 13-15/2016 ዓ.ም ይካሔዳል ብሎ የነበረ ሲሆን፤ ምዝገባው ከሐምሌ 19-22/2016 ዓ.ም ይካሔዳል ተብሏል።

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና በአስር የፈተና ማዕከላት በወረቀት እና በኦንላይን መሰጠቱ ይታወቃል።

ከማዕከላቱ መካከል ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ አንዱ ነው።

በሁለተኛው ዙር ፈተና፥ 184 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በኮሌጁ በኦንላይን ፈተናቸውን ወስደዋል።

@tikvahuniversity
በትግራይ ክልል እየተሰጠ የሚገኘው ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

በ2013/14 ዓ.ም በቀድሞ ስርዓተ ትምህርት ተምረው ፈተናውን ሳይወስዱ የቆዩ ተማሪዎች ፈተናቸውን ከሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲወስዱ ቆይተዋል፡፡

ዛሬ በጠዋቱ መርሐግብር እየተሰጠ ከሚገኘው የኬሚስትሪ ትምህርት ፈተና በኋላ፥ በክልሉ በሁለት ዙር የተሰጠው መልቀቂያ ፈተና ይጠናቀቃል።

23 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች፤ ለአራት ተከታታይ ቀናት በመቐለ፣ ራያ፣ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች የተሰጠውን ሁለተኛ ዙር ፈተና እንደወስዱ ይገመታል።

በተያያዘ መረጃ በራያ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ መልቀቂያ ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/10/05 09:25:54
Back to Top
HTML Embed Code: