Telegram Web Link
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ከቅዳሜ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደሚፈተኑበት ተቋማት ገብተዋል።

ዛሬ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኞች ገለፃ ሲሰጡ የዋሉ ሲሆን ሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነገ ኦረንቴሽን እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

የመጀመሪያው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

@tikvahuniversity
ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የ2ዐ16 ዓ.ም የክረምት ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ሐምሌ 18 እና 19/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

ትምህርት ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

@tikvahuniversity
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም ነባር የክረምት ትምህርት ምዝገባ የሚካሄደው ነሐሴ 2 እና 3/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

የምዝገባ ጥሪው ነባር የክረምት የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን የሚመለከት መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#Tigray_National_Exam

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ይጀምራል፡፡

ፈተናው በክልሉ በሁለት ዙር ከሐምሌ 2-12/2016 ዓ.ም በመቐለ፣ ራያ፣ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከሐምሌ 2-5/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን፤ ከ31 ሺህ በላይ የማኅበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዚህ ዙር ለፈተና እንደሚቀመጡ ይጠበቃል፡፡ ተፈታኞች በአጠቃላይ የፈተና ዲሲፕሊን ዙሪያ ገለፃ በተቋማቱ ተደርጎላቸዋል፡፡

በዛሬው የመጀመሪያ ቀን ፈተና በጠዋቱ መርሐግብር እንግሊዝኛ፤ በከሰዓት መርሐግብር ሒሳብ ፈተና የሚሰጥ ይሆናል፡፡፡

@tikvahuniversity
#Tigray_National_Exam

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በትግራይ ክልል እየተሰጠ ነው፡፡

ፈተናው በኦንላይን እና በወረቀት እየተሰጠ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በኦንላይን መሠጠት ጀምሯል፡፡

ፈተናው በትግራይ ክልል በሁለት ዙር ከሐምሌ 2-12/2016 ዓ.ም በመቐለ፣ ራያ፣ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከሐምሌ 2-5/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን፤ ከ31 ሺህ በላይ የማኅበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዚህ ዙር ለፈተና እንደሚቀመጡ ይጠበቃል፡፡

ምስል፦ መቐለ ዩኒቨርሲቲ፣ @ProfKindeya

@tikvahuniversity
#Safaricom Ethiopia

የ 400,000 ብር ሽልማት አሸናፊ ይሁኑ!

#1Wedefit የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፦
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
📲 የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ገጽ ታግ እናድርግ
🏷 #የምትኖሩበትን ከተማ አድራሻ እና #1Wedefit የሚለውን ማስገባት እንዳትረሱ

እንዝፈን፣ እንወዳደር፣ እንሸለም!

#SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether #DigitalMusicChallenge
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የክረምት ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ሐምሌ 15 እና 16/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

አመልካቾች በተገለፁት ቀናት ብቻ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ሬጂስትራር ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

@tikvahuniversity
የወሰዳቸውን 52 ኮርሶች በሙሉ A+ ያመጣው ተመራቂ

ተማሪ መርቲኑ ቶሌራ በ2016 ዓ.ም ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ በአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት መስክ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቋል፡፡

ባለብሩህ አዕምሮው ተማሪ መርቲኑ 4.00 አጠቃላይ ውጤት (CGPA) በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ተማሪ መርቲኑ በዩኒቨሲቲ ቆይታው የወሰዳቸውን 52 ኮርሶች በሙሉ A+ በማምጣት ድንቅ ውጤት አስመስግቧል።

@tikvahuniversity
የ12ኛ ክፍል ተፈታኙ የኃይማኖት አባት

ነገ ሐምሌ 3/2016 ዓ.ም መሠጠት የሚጀምረውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ከተገኙ ተፈታኞች መካከል የኃይማኖት አባት የሆኑት አባ ተ/ወልድ ወ/ጻዲቅ ይገኙበታል።

አባ ተ/ወልድ በ1962 ዓ.ም ነበር ትምህርታቸውን ከ8ኛ ክፍል ያቋረጡት። "ሞራልና ፍላጎት ካለ ከትምህርት ምንም ሊገድበኝ የሚችል ነገር የለም" በማለት ያቋረጡትን ትምህርት በመቀጠል፥ ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ይወስዳሉ።

"ጊዜው የቴክኖሎጂ ነው፥ የትኛውም የሥራ መስክ በትምህርት ካልተደገፈ ሙሉና የተሳካ ሊሆን አይችልም" ይላሉ አባ ተ/ወልድ።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናውን በማለፍ ወደፊት አቅማቸው እስከፈቀደ ድረስ ትምህርታቸውን ለመቀጠል ቁርጠኝነት እንዳለቸው አባ ተ/ወልድ ይገልፃሉ። #SalaleUniversity

@tikvahuniversity
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በአማራ ክልል

በአማራ ክልል 96,408 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ነገ ሐምሌ 3/2016 ዓ.ም መሠጠት የሚጀምረውን አገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና፤ 96,408 ተማሪዎች በአማራ ክልል እንደሚወስዱ ቢሮው ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

51,900 የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እና 44,508 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናውን በ 375 የፈተና ጣቢያዎች እንደሚወስዱ ተገልጿል። ይህ አሀዝ ቢሮው ፈተናውን ይወስዳሉ ብሎ ይጠብቅ ከነበረው በግማሽ ያነሰ ነው።

ተፈታኞችን ለማዘጋጀት የማጠናከሪያ ትምህርት መሰጠቱን፣ የክለሳ ሥራዎች መደረጋቸውን እንዲሁም ሞዴል ፈተናዎች መሠጠታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለት ዙር ከሐምሌ 3-11/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች በተለይም በአማራ ክልል የሚገኙና ምዝገባቸውን ማድረግ ላልቻሉ ተማሪዎች በመስከረም 2017 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር ፈተና እንደሚዘጋጅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ አይዘነጋም።

@tikvahuniversity
#University_of_Gondar

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ነባር የክረምት ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም የምዝገባ ጊዜ ሐምሌ 15 እና 16/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በመሆኑም ነባር የክረምት ተማሪዎች በኮሌጅ፣ በኢንስቲቱዩት ወይም በትምህርት ቤት ረዳት ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች በመገኘት ምዝገባችሁን እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

ትምህርት ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/10/05 22:45:30
Back to Top
HTML Embed Code: