Telegram Web Link
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2ዐ16 ዓ.ም የክረምት ትምህርት ፕሮግራም ምዝገባ ሐምሌ 15 እና 16/2016 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን አሳውቋል።

ይህ ጥሪ ለቅደመ እና ድኅረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች የተደረገ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
ረቡዕ ሐምሌ 3/2016 ዓ.ም መሰጠት ከሚጀምረው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አስቀድመው ተማሪዎች ወደሚፈተኑበት ተቋማት በመግባት ላይ ይገኛሉ።

በመጀመሪያ ዙር ፈተና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለፈተና የሚቀመጡ ይሆናል።

ምስል፦ አምቦ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ “የዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ተሳትፎ” በተሰኘ ጭብጥ ላይ የፓናል ውይይት መድረክ አዘጋጅቷል።

አካዳሚው በኢትዮጵያ ከሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ክፍል ጋር በመተባበር መድረኩን አዘጋጅቷል።

መቼ፦ ሐምሌ 4/2016 ዓ.ም ቀን 10፡00 ሰዓት
የት፦ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አዳራሽ
(የአዳራሹ መግቢያ በኋላ በር በኖኅ ሬስቶራንት በኩል ነው)

በዙም አማካኝነት በቀጥታ መሳተፍ ይችላሉ።
Join Zoom Meeting፡
https://us06web.zoom.us/j/86599822304...
Meeting ID: 865 9982 2304
Passcode: 880397

@tikvahuniversity
35A+ ያሳካው ባለወርቅ ሚዳሊያ ተመራቂ

ነስረዲን ሙሐመድዘይን ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል፣ ኬሚካል እና ማቴሪያል ሳይንስ ኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍል የዘንድሮ የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂ ነው፡፡

ነስረዲን በዩኒቨርሲቲው በነበረው ቆይታ እጅግ ታታሪ ተማሪ የነበረ ሲሆን፤ ከወሰዳቸው ኮርሶች 35A+ በማሳካትና 3.99 አጠቃላይ ውጤት (CGPA) በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

@tikvahuniversity
መቱ ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት መርሐግብር #የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ምዝገባ ሐምሌ 14 እና 15/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

ትምህርት ሐምሌ 16/2016 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

@tikvahuniversity
ጅማ ዩኒቨርሲቲ የአቪዬሺን ሳይንስና ኤሮስፔስ ምህንድስና ትምህርት በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም መስጠት ለመጀመር እየሰራ መሆኑን ገለፀ።

ፕሮግራሙን በጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለመክፈት የሚያስችሉ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በኢትዮጵያ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ታሪክ "የመጀመሪያ" የተባለውን ፕሮግራሙን ለመክፈት የሚያስችል ሀገር አቀፍ የካሪኩለም ግምገማ ተካሒዷል።

ፕሮግራሙ ሲከፈት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚሆኑ የአቪዬሺን ሳይንስና ኤሮስፔስ ምህንድስና ባለሙያዎችን ለማፍራት እንደሚሰራ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም ነባር የክረምት ትምህርት መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 12 እና 13/2016 ዓ.ም የሚካሔድ መሆኑን አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ጥሪው ለነባር የክረምት ትምህርት መርሐግብር የቅድመ ምረቃ እንዲሁም የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የተደረገ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ትምህርት ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡ (ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም ነባር የክረምት ትምህርት መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ሐምሌ 15 እና 16/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ጥሪው የመጀመሪያ ዲግሪ፣ የሁለተኛ ዲግሪ እና የፒጂዲቲ ፕሮግራሞች የክረምት መርሐግብር ነባር ተማሪዎችን እንደሚመለከት ተገልጿል፡፡

የነባር ተማሪዎች ቲቶሪያል ከሐምሌ 17-19/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል፡፡ (ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል ለሰባት ወራት ያሰለጠናቸውን 17 ተማሪዎች አስመርቋል።

ሰልጣኞቹ ለሳይንስና ፈጠራ ሥራዎች ዝንባሌ ያላቸው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሲሆኑ፤ በበጋ መርሐግብር በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ለ 224 ሰዓት ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ስልጠናው በመሰረታዊ ሳይንስ፣ በኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ፣ በPCB እና 3D ፕሪንቲንግ፣ በመሰረታዊ ኤሌክትሮኒክስ፣ በመሰረታዊና አድቫንስድ ኮምፒውቲንግ ላይ ትኩረት በማድረግ የተሰጠ መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡

@tikvahuniversity
40A+ ያሳካው የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በሳምንቱ መጨረሻ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል ሀሰን መሀመድ አንዱ ነው፡፡

ሀሰን ከኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል 4.00 አጠቃላይ አማካይ ውጤት (CGPA) በማስመዝገብ በማዕረግ ተመርቋል፡፡ ሀሰን ከወሰዳቸው ኮርሶች ውስጥ 40 የትምህርት አይነቶችን A+ ውጤት በማሰመዝገብ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡

በተጨማሪም በቅርቡ የተሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና 81 ነጥብ ውጤት በማምጣትም አጠናቋል፡፡ ሀሰን ዩኒቨርሲቲ ከገባ በኋላ ሙሉ ትኩረቱን ትምህርት ላይ በማድረግ ተምሮ ለውጤት መብቃቱን ይናገራል፡፡
(https://www.facebook.com/yibeltal.gizaw)

@tikvahuniversity
2024/10/06 00:32:03
Back to Top
HTML Embed Code: