Telegram Web Link
#KabridaharUniversity

ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 848 በተማሪዎች አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው 726 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 73 በሁለተኛ ዲግሪ እና 49 በከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም (HDP) ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል። #SMMA

@tikvahuniversity
#ArbaMinchUniversity

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተመረቀ።

ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በግንባታና ግብዓት በማሟላት ሒደት ላይ የቆየው ሆስፒታሉ፤ ዛሬ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም ተመርቆ አገልግሎት መሥጠት ጀምሯል፡፡

ሆስፒታሉ 600 የህሙማን አልጋዎች እና የተለያዩ ዘመናዊ የህክምና ግብዓቶች የተሟላለት መሆኑ ተገልጿል።

ሆስፒታሉ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የአርባ ምንጭና አካባቢዋ ነዋሪዎች አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION🚨

" የበይነ መረብ (ኦንላይን) ተፈታኞች በተመደባችሁበት የፈተና ጣቢያ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳስባለን " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ፈተና በበይነ መረብ (ኦንላይ) እንዲሁም በወረቀት እንደሚሰጥ በዛሬው ዕለት በድጋሚ አሳወቀ።

በሁለቱም መንገድ ለሚሰጠው ፈተና ዝግጅት ተደርጓል ብሏል።

ትላንት እና ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ያሉ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች " የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተና ቀርቷል " እያሉ ለተማሪዎች መናገራቸውን እና የጽሁፍ መልዕክት በቴሌግራም ላይ መለጠፋቸውን የተማሪ ወላጆች እንዲሁም ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

እንዲህ ያለው ውሳኔ የሚተላለፈው ከማዕከል ከትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ ሳለ ፥ ትምህርት ቤቶቹ ውሳኔውን ማን እንዳሳለፈ በይፋ ያሉት ነገር ሳይኖር በደፈናው " ቀርቷል " የሚል ነገር ብቻ ነው የነገሯቸው።

በኋላም እራሳቸው ት/ቤቶቹ ቀድሞ ያሰራጩትን ያልተረጋገጠ መረጃ በማጥፋት የኦላንይን ፈተናው እንዳልቀረ መልሰው ገልጸዋል።

ዛሬ እሁድ ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው በፍጹም እንዳልቀረ በድጋሜ አረጋግጧል።

ብሔራዊ ፈተናውን በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቅቆ የተማሪዎችን የመፈተኛ ቀን እየተጠባበቀ እንደሚገኝም አሳውቋል።

" ፈተናውን አስመልክቶ የተሳሳቱ መልዕክቶች በየጊዜው ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር ባልሆኑ ገጾች እየተለቀቁ ይገኛሉ " ሲልም ገልጿል።

ለተማሪዎች፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች ባስተላለፈው መልዕክት ፈተናው ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት እንደተማሪዎች የቀደመ ምርጫ መሰረት ይሰጣል ብሏል።

አስቀድመው በወረቀት የመረጡ ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲ፣ በበይነ መረብ (ኦንላይን) የመረጡም በተመደቡበት የፈተና ጣቢያ ተገኝተው ፈተናውን እንዲወስዱ በጥብቅ አሳስቧል።

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ተማሪዎች ከላይ በምስሉ እንደተያያዘው አይነት ከሃሰተኛ ወሬ ራሳቸውን በመከላከል ለፈተናው የሚያደርጉትን ዝግጅት እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

ለማንኛውም መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር ብቻ እንዲከታተሉም አደራ ብሏል።

#TikvahEthiopia
#NationalExam
#MoE

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች መግባት ጀምረዋል።

ፈተናው በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ያረጋገጠ ሲሆን፤ በወረቀት ተፈታኞች ወደሚፈተኑበት ዩኒቨርሲቲዎች ከትናንት ሰኔ 29/2016 ዓ.ም መግባት ጀምረዋል።

ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3-11/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

በትግራይ ክልል ፈተናው በሁለት ዙር ከሐምሌ 2-12/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

በዚህም በመጀመሪያው ዙር በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፈተናውን የሚወስዱ 6,000 ተማሪዎች ከትናንት ጀምሮ መግባት መጀመራቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

እነዚህ ተፈታኞች ከክልሉ ምስራቅ ዞን እና በከፊል ከማዕከላዊ ዞን የተውጣጡ መሆናቸው ተገልጿል።

ምስል፦ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያ ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን መቀበል ጀምረዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን ወደሚወስዱበት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየገቡ ነው።

የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ደግሞ ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ዘንድሮ ከ 700,000 በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን እና በወረቀት እንደሚወስዱ መገለፁ ይታወሳል።

ምስል፦ ወራቤ፣ ወሎ፣ ደምቢ ዶሎ እና መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች

@tikvahuniversity
በግል የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተፈታኞች ጉዳይ

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ውጤት ሰኔ 21/2016 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

የመውጫ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውጤትም ከቀናት በፊት መለቀቁንና ተፈታኞቹም ውጤታቸውን እየተመለከቱ እንደሆነ ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል።

ይሁን እንጂ ፈተናውን በድጋሜ የወሰዱ የግል ተፈታኞች ውጤትን በተመለከተ አሁንም ያልተጠናቀቁ ነገሮች መኖራቸውን የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ገበየሁ ለቲክቫህ ተናግረዋል።

በግል ፈተናውን በድጋሜ የወሰዱ ተፈታኞች ጉዳይ፣ የያጋጠሙ ችግሮች እና ውጤታቸው እንዴት ይገለፃል በሚለው ላይ በቀጣይ ቀናት ተጨማሪ መረጃ እንደሚኖር ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል።

ዘንድሮ 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ማስፈተናቸው ይታወቃል።

@tikvahuniversity
#AddisAbaba ወላጆች እና ተማሪዎች በ12ኛ ክፍል የኦንላይን ፈተና ጉዳይ ግልጽ የሆነ ማብራሪያ እንድንጠይቅ ባዘዛችሁን መሰረት የከተማውን ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አነጋግረናል።

ሙሉ ቃላቸውን በደቂቃዎች ውስጥ እንልካለን።

@tikvahuniversity
2024/10/06 10:21:10
Back to Top
HTML Embed Code: