Telegram Web Link
#KUE

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1,688 ተማሪዎች አስመረቀ።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በማታ እና በተከታታይ መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው ጥራትና ብቃት ያላቸው መምህራን እና ተማሪዎችን ለማፍራት እየሠራ እንደሚገኝ የተቋሙ ፕሬዝዳንት ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር) ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
#ArsiUniversity

አርሲ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1,535 ተማሪዎች አስመረቀ።

ተመራቂዎቹ በቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጠኝነት እና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርት በፒኤችዲ ሦስት ባለሙያዎችን አስመርቋል።

የጥበብ ከጲላጦስ መፃሕፍት ፀሐፊው ኃይለጊዮርጊስ ማሞ (ዶ/ር) ከሴት ልጃቸው ጋር የዘንድሮ ዓመት ተመራቂ ሆነዋል።

ጋዜጠኛ እና ፀሐፊ ኃይለጊዮርጊስ ማሞ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሚዩኒኬሽን ክፍል ለመጀመሪያ ጊዜ በፒኤችዲ ካስመረቃቸው ሦስት ምሩቃን አንዱ ናቸው።

@tikvahuniversity
#MattuUniversity

መቱ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1,044 ተማሪዎች አስመረቀ።

50 ተመራቂዎቹ በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ሲሆኑ ቀሪዎቹ 994 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ መመረቃቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#ASTU

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 1,100 ተማሪዎችን አስመረቀ።

ከተመራቂዎቹ መካከል 18ቱ በዱዋል ሜጀር (በጥምር ሙያ) የተመረቁ ናቸው።

በቅርቡ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ከወሰዱ
የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ዕጩ ተመራቂዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸው ተገልጿል።

አጠቃላይ ተመራቂዎች - 1,100
በሦስተኛ ዲግሪ - 32
በሁለተኛ ዲግሪ - 397
በቅድመ ምረቃ - 671

@tikvahuniversity
#DambiDolloUniversity

ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ እና በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ያስተማራቸውን 1,596 ተማሪዎችን አስመረቀ።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በሳምንቱ መጨረሻ መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity
#DebreMarkosUniversity

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ እና በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ያስተማራቸውን 1,020 ተማሪዎችን አስመረቀ።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በርቀት እና በተከታታይ መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity
#GambellaUniversity

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ያስተማራቸውን 481 ተማሪዎች አስመረቀ።

156 ተመራቂዎች በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ 325 ደግሞ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የተመረቁ ናቸው።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መረሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#TVTI

የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት 2,100 ሰልጣኞችን አስመርቋል።

ተመራቂዎች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ስልጠናቸውን ተከተታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ኢንስቲትዩቱ ብቁ ሰልጣኞችን በማፍራት ለክህሎት ልማት ዕድገት ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኝ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ገልፀዋል።

በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ አነቃቂ ንግግር ያደረጉት ባለሃብቱና ሥራ ፈጣሪው ቤጃይ ነራሽ፥ ተመራቂዎቹ ከተጠቃሚነት ወደ አምራችነት እንዴት መሸጋገር እንዳለባቸው ልምዳቸውን አካፍለዋል።

@tikvahuniversity
37A+ ያሳካችው ተመራቂ

ሠብለወንጌል መንግስቱ ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የማኔጀመንት ትምህርት ክፍል ተመራቂ ናት።

ሠብለወንጌል በቆይታዋ ከወሰደቻቸው የትምህርት ኮርሶች መካከል 37A+ ውጤት በመደርደር ልዩ የማዕረግ ተመራቂ ሆናለች።

ሠብለወንጌል በሦስት ኮርሶች ብቻ A- ውጤት ስለነበራት ሙሉ አራት ነጥብ ማምጣት ባትችልም፤ 3.99 አጠቃላይ ውጤት (CGPA) በማስመዝገብ የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች።

ሠብለወንጌል እንደምትለው የስኬቷ ምስጢር ለትምህርት ሙሉ ጊዜ እና ትኩረት መስጠቷ ነው። በተለይም በፈጣሪ ዕርዳታ ለዚህ ውጤት በቅቻለሁ ብላለች።

በትምህርቷ ያስመዘገበችው ዕጅግ ከፍተኛ ውጤት ከተመረቀችበት ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪ ነፃ የትምህርት ዕድል እንድታገኝ አስችሏታል። #ENA

@tikvahuniversity
2024/10/06 04:26:38
Back to Top
HTML Embed Code: