Telegram Web Link
Tikvah-University
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 5ኛ አመት ተመራቂ ተማሪዎች " ከሁለት አመት በፊት Add አድርገን መጨረስ የምንችላቸውን ኮርሶች በዩኒቨርሲቲው ምክንያት ባለመውሰዳችን የመውጫ ፈተና ላይም መቀመጥም ሆነ የመመረቂያ አዳራሽ ውስጥ እንዳንገኝ ዩኒቨርሲቲው ወስኖብናል " በማለት ቅሬታቸውን ለቲክቫህ አቅርበዋል። " ከሁለት አመት በፊት ከ በግዜው በኮቪድ ምክንያት በክረምት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ…
" ሰሚና አዳማጭ አቤት የሚለን አጥተን ቁጭ ብለናል " - ተማሪዎች

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 5ኛ አመት ተመራቂ ተማሪዎች " ከሁለት አመት በፊት Add አድርገን መጨረስ የምንችላቸውን ኮርሶች በዩኒቨርሲቲው ምክንያት ባለመውሰዳችን የመውጫ ፈተና ላይም መቀመጥም ሆነ የመመረቂያ አዳራሽ ውስጥ እንዳንገኝ ዩኒቨርሲቲው ወስኖብናል " በማለት ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበው ነበር።

እኛም የተማሪዎቹን ጉዳይ እየተከታተልን የቆየን ሲሆን ተገቢ ምላሽ ሳናገኝ ቀርተናል።

ተማሪዎቹ ባለው ጊዜ መፍትሄ እንዲሰጣቸውና በምርቃቱ ላይ እንዲገኙ ጠይቀዋል።

ዩኒቨርሲቲው በገባው ቃል አለመገኘቱን ተከትሎ የመውጫ ፈተና ላይ እንዳልተቀመጡ ፤ ከዚህ ባለፈ የምረቃ ስነስርዓት ላይ እንዳይገኙ በመወሰኑን ቅሬታ ላይ እንደሚገኙ አመልክተዋል።

ተማሪዎቹ " ቤተሰብ ይመረቃሉ ብሎ ቢጠብቀንም መመረቂያ አዳራሽ ውስጥ እንኳን እንዳንገባ ወስነውብናል " ብለዋል።

" ሰሚ እና ችግራችንን አይቶ የሚመልስልን አካል አጥተናል " ያሉት ተማሪዎቹ " ከዩኒቨርሲቲው ሰዎች ንቀትና ያልተገባ ባህሪ ነው የምናየው " ብለዋል።

በቲክቫህ ላይ የወጣውን ዜና አመራሮቹ ቢደርሳቸውም ከቁብ ሳይቆጥሩት በውሳኔያቸው ቀጥለዋል። ከምንም በላይ ክብር እንኳን አልተሰጠንም ሲሉ ወቅሰዋል።

@tikvahuniversity
#HawassaUniversity

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2016 መውጫ ፈተና ምን ያህል ተማሪ እንዳለፈ ይፋ አደርጓል።

መረጃው ከሀዋሳ የተማሪዎች ህብረት የተገኘ ነው።

@tikvahuniversity
የ2016 ሀገር አቀፉ የሬሜዲያል ፈተና ይፋ ተደርጎ ተማሪዎች በኦንላይን ውጤታቸውን በመመልከት ላይ ይገኛሉ።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ነው እየተመለከቱ ያሉት።

ድረገጹ በተመሳሳይ ጊዜ ብዙ ተማሪዎች እየሞከሩት ስለሆነ ከፍተኛ መጨናነቅ አለ።

ደጋግሞ በመሞከር ውጤት መመልከት ይቻላል።

ውድና የተከበራችሁ ተማሪዎች በኮሜንት መስጫው ውስጥ ሀሳብ መቀያየር እና ጥቆማ ማስቀመጥ ትችላላችሁ።

@tikvahuniversity
#WolloUniversity

አወል ሰይድ (ዶ/ር) የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ተወካይ ሆነው ተመድበዋል፡፡

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት መንገሻ እየነ (ዶ/ር) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው በቅርቡ መመደባቸው ይታወቃል፡፡

ይህንን ተከትሎ አወል ሰይድ (ዶ/ር) በቀጣይ አመራር እስኪመደብ ድረስ ከስኔ 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሥራን በተጨማሪ ደርበው እንዲሰሩ ውክልና በትምህርት ሚኒስቴር ተሰጧቸዋል፡፡

@tikvahuniversity
#2024_Commencement
#የቀጠለ

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ከሳምንቱ መጨረሻ ጀምሮ ያስመርቃሉ፡፡

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
ጅማ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 26 እና 27/2016 ዓ.ም

@tikvahuniversity
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና የወሰዱ የተቋሙ ተማሪዎች ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ያስፈተናቸው ተማሪዎች ውጤት በተቋሙ ሬጅስትራር አማካኝነት ይፋ መደረጉንና ተማሪዎችም ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ አሳውቋል።

@tikvahuniversity
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም ሃገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ግዜ ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል ከ 89 በመቶ በላይ የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን አሳውቋል።

@tikvahuniversity
#WerabeUniversity

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም ሃገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ግዜ ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል ከ 84 በመቶ በላይ የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን አሳውቋል።

@tikvahuniversity
#MizanTepiUniversity

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ.ም ሃገር አቀፍ የመውጫ ፈተና በተቋሙ ከተቀመጡት ተማሪዎች ውስጥ 74.5 በመቶ ተፈታኞች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በስምንት ኮሌጆች ለመውጫ ፈተና ካስቀመጣቸው 1438 ዕጩ ተመራቂዎች መካከል 1071 ተማሪዎች ማለፋቸውን ገልጿል።

@tikvahuniversity
#MattuUniversity

አዲሱ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት አለሙ ዲሳሳ (ዶ/ር) የሥራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ የትምህርት ሚኒስቴር ተወካዮች በተገኙበት ከዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንትና ሴኔት አባላት ጋር የሥራ ርክክብና ትውውቅ አድርገዋል፡፡

በቆይታቸው መልካም የሥራ ባህልን በመፍጠር የዩኒቨርሲቲውን ራዕይ ለማሳካትና ወደ ራስገዝ ዩኒቨርሲቲነት የሚደረገውን ጉዞ ከመላው የተቋሙ ማኅበረሰብ ጋር በመሆን እንደሚያፋጥኑ ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የክረምት መርሐግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ነባር ተማሪዎች ምዝገባ ከሐምሌ 12-14/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

ትምህርት ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም እንደሚጀምር ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

የበጋ ኮርስ ተከታትላችሁ ነገር ግን ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት ያላስላካችሁ እስከ ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ድረስ ማስላክ ይኖርባችኋል፡፡

ይህ የጥሪ ማስታወቂያ የ PGDT ተማሪዎችን ያካትታል ተብሏል፡፡ ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡

@tikvahuniversity
#2024_Commencement
#የቀጠለ

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ከነገ ሰኔ 23/2016 ዓ.ም ጀምሮ ያስመርቃሉ፡፡

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 29/2016 ዓ.ም
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም

@tikvahuniversity
2024/10/01 10:09:13
Back to Top
HTML Embed Code: