Telegram Web Link
ለ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ፌዴራል ፖሊስ ገለፀ፡፡

ለፈተናው የሚደረገውን ዝግጅት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከባለድረሻ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡

ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከክልል የትምህርት ቢሮዎች እና የፀጥታ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው ተብሏል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከትግራይ ክልል ውጭ ከሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
መንገሻ አየነ (ዶ/ር) የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመደቡ፡፡ መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ከሰኔ 12/2016 ዓ.ም ጀምሮ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መመደባቸውን ሰኔ 10/2016 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ የወጣ የምደባ ደብዳቤ ያሳያል፡፡ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን…
አዲስ የተመደቡት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) የሥራ ርክክብ አድርገዋል።

አዲሱ ፕሬዝዳንት የትምህርት ሚኒስቴር ተወካዮች በተገኙበት ከዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት እና የሴኔት አባላት ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን ራስ ገዝ ማድረግ፣ አዲሱን ተቋማዊ የሰራተኞች የሥራ ምደባ ማስፈጸም እንዲሁም የተቋሙን የምርምር ዩኒቨርሲቲነት እውን ሊያደርጉ የሚችሉ ተግባራትን ማከናወን ቅድሚያ የሚሰጧቸው ጉዳዮች እንደሆኑ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለክረምት ፕሮግራም ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል።

የነባር የክረምት ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 2 እና 3/2016 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

አዲስ የPGDT ኮርስ ተመዝጋቢዎች ምዝገባ ከሰኔ 25-30/2016 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

የክረምት ትምህርት ከሐምሌ 08/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#Update

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ውጤት ከመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ይፋ እንደሚደረግ ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል።

የፈተናው ውጤት መቼ ይፋ እንደሚደረግ በርካታ ተማሪዎች ጥያቄያቸውን አድርሰውናል።

የፈተናው ውጤት መቼ ይገለፃል ስንል የጠየቅናቸው የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር፤ "በቅርቡ፥ ከመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት" ሲሉ መልሰውልናል።

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ከሰኔ 3-11/2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ትናንት የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ የመውጫ ፈተና ለወሰዱ ተፈታኞች ፈተናው በድጋሜ ዛሬ ከሰዓት እንደሚሰጥ አሳውቋል፡፡

በዚህም ፈተናው በድጋሜ ዛሬ ሰኔ 18/2016 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ላይ እንደሚሰጥ ተፈታኞች እና ፈታኞች እንዲያውቁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

በተመሳሳይ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ እና የኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ዛሬ ከሰዓት ፈተናውን እንደሚወስዱ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#MekelleUniversity

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ትናንት የተሰጡት የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ እና የኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ የመውጫ ፈተናዎች ከተዘጋጀው ብሉ ሪንት ውጪ በመሆናቸው ፈተናዎቹ በድጋሜ እንዲሰጡ ተፈታኞቹ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አድርሰዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ኅብረት ተወካይ በጉዳዩ ላይ ከተቋሙ አመራሮች ጋር የተወያየ ሲሆን፤ ፈተናዎቹ ከብሉ ፕሪንት ውጪ እንደተዘጋጁ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል፡፡ ይሁን እንጂ ፈተናው በድጋሜ ዛሬ ከሰዓት እንደሚሰጥ ለማረጋገጥ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

በተመሳሳይ ሰኔ 14/2016 ዓ.ም የተሰጠው የ Management የመውጫ ፈተና በተዘጋጀው ብሉ ፕሪንት መሰረት የተዘጋጀ እንዳልነበር በርካታ ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረባቸው አይዘነጋም፡፡

@tikvahuniversity
#AddisAbabaUniversity

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ ምረቃ እና በድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 29/2016 ዓ.ም በሚሌኒየም አዳራሽ ያስመርቃል።

@tikvahuniversity
#EducationDiplomacy

መንግሥት የትምህርት ዲፕሎማሲን በማጠናከር
በ2016 ዓ.ም ለ865 የጎረቤት አገራት ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጥቷል።

እነዚህ ተማሪዎች በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ።

ነጻ የትምህርት ዕድል ካገኙት መካከል የደቡብ ሱዳን፣ የሶማሊላንድ እና የጅቡቲ ተማሪዎች ይገኙበታል።

@tikvahuniversity
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

@tikvahuniversity
አምቦ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

በዕለቱ የህክምና ዶክተሮች፣ የመጀመሪያ፣ የሁለተኛ እንዲሁም የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች እንደሚመረቁ ዩኒቨርሲቲው ለቲክቫህ ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር እስከ ነሐሴ ወር ድረስ 18.8 ሚሊዮን የመማሪያ መጻሕፍት ወደ አገር ውስጥ በማስገባት፣ ለመጪው የትምህርት ዘመን ለክልሎች ለማሠራጨት ዕቅድ መያዙን አስታወቀ፡፡

እስካሁን 20.7 ሚሊዮን የሁለተኛ ደረጃ የመማሪያ መጻሕፍት ታትመው አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ለክልሎች መሠራጨታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር የመማር ማስተማር ቁጥጥርና ሥርጭት ባለሙያ ዘሪሁን አሰግድ ለሪፖርተር ገልፀዋል፡፡

ባለፈው ዓመት የተከሰተውን የመማሪያ መጻሕፍት አቅርቦት ችግር ለመፍታት ወጥቶ የነበረውን ጨረታ ባሸነፈው የጃፓን ኩባንያ አማካይነት ኅትመቱ እየተከናወነ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በገጠመው የበጀት ችግር ምክንያት የመማሪያ መጻሕፍት ኅትመት በሁለት ዙሮች መደረጉንና እስከ መጪው ነሐሴ ወር ድረስ ቀሪ 18.8 ሚሊዮን የመማሪያ መጻሕፍት እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከዚህ በፊት ለሦስት ተማሪ አንድ መጻሕፍት ይዳረስ የነበረውን አሠራር፣ ለአንድ ተማሪ አንድ መጽሐፍ እንዲዳረስ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity
ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት በሀረሪ ክልል ሲሰጥ የነበረው የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ተጠናቋል።

5 ሺህ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ተገልጿል።

ክልል አቀፍ ፈተናው በ29 የመፈተኛ ጣቢያዎች ተሰጥቶ በሰላም መጠናቀቁን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የሙያ ፍቃድና ምዘና ዳይሬክተር ዙኸራ ሙክታር ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 26/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

በዕለቱ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎች እንደሚመረቁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/10/01 14:23:06
Back to Top
HTML Embed Code: