Telegram Web Link
#ExitExam

ላለፉት ስድስት ቀናት በመላ አገሪቱ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል።

57 የመንግሥት እና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ማስፈተናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የመውጫ ፈተናው በ244 የቅድመ ምረቃ መርሐግብሮች በ51 የፈተና ማዕከላት ተሰጥቷል።

ለፈተናው ከተመዘገቡት 169,790 ተማሪዎች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈተኑ 117,192 ተማሪዎች እንዲሁም 52,598 ተማሪዎች ደግሞ ፈተናውን በድጋሚ ለመውሰድ የተመዘገቡ መሆናቸውን በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት የጥራትና ብቃት ማሻሻል ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሐመድ ገልፀዋል።

የመውጫ ፈተና ውጤት በቅርቡ እንደሚለቀቅ የሚኒስቴሩ መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity
#Update

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና እና የሪሚዲያል ማጠቃለያ ፈተና ውጤቶች መቼ ይፋ ይደረጋሉ?

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተናቸውን ሰኔ 11/2016 ዓ.ም ማጠናቀቃቸው ይታወቃል፡፡

በተመሳሳይ የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ትናንት ሰኔ 19/2016 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡

የፈተናዎቹ ውጤት መቼ ይፋ እንደሚደረግ አንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራርን ጠይቀናል፡፡

የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ውጤት ከሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ኃላፊው ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል። በጣም ከዘገየ እስከ ሰኞ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይፋ ይሆናል ብለዋል፡፡

የመውጫ ፈተና ውጤት በቀጣይ ቀናት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቅ ከመጀመራቸው በፊት ይፋ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
#BongaUniversity

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች የፊታችን እሑድ ሰኔ 23/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

@tikvahuniversity
በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የገፅ-ለገፅ እና የኦንላይን ትምህርትን ያጣመረ የመማር ማስተማር ስርዓት ለመተግበር የፖሊሲ ዝግጅት እየተደረገ ነው ተባለ፡፡

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከፊንላንድ ሴንትሪያ እና ጃመክ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመቀናጀት በተመረጡ ስድስት ክልሎች በሚገኙ 15 የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የትምህርት አሰጣጡን ማዘመን የሚያስችሉ የሙከራ ተግባራት መከናወናቸው ተገልጿል፡፡

በቀጣይ ሦስት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ የገፅ-ለገፅ እና የኦንላይን ትምህርትን ያጣመረ የመማር ማስተማር ስርዓት ገቢራዊ ለማድረግ የፖሊሲ ዝግጅት እየተከናወነ እንደሚገኝ በተከናወኑ ተግባራት ላይ በተዘጋጀ መድረክ ላይ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታው ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

በመላ አገሪቱ ከ1,500 በላይ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መኖራቸው በመድረኩ ተጠቁሟል። #ኢዜአ

@tikvahuniversity
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሰኔ 25 እና 26/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

የተማሪዎች የምርቃት መርሐግብር ሰኔ 25/2016 ዓ.ም በነቀምቴ ካምፓስ እንዲሁም ሰኔ 26/2016 ዓ.ም በጊምቢ እና በሻምቡ ካምፓሶች እንደሚካሔድ ከዩኒቨርሲቲው የተገኘ መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity
#TVTI_Exit_Exam

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለዕጩ ተመራቂ ተማሪዎቹ የመውጫ ፈተና ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

በኦንላይን ከሚሰጠው ፈተና አስቀድሞ፣ ነገ ሰኔ 21/2016 ዓ.ም ሞዴል የመውጫ ፈተና ለተፈታኞች እንደሚሰጥ ኢኒስቲትዩቱ ገልጿል፡፡

ኢንስቲትዩቱ የመውጫ ፈተና በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም መስጠቱ አይዘነጋም፡፡

@tikvahuniversity
#AksumUniversity
#MaddaWalabuUniversity

አክሱም ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እሑድ ሰኔ 23/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

በተመሳሳይ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እሑድ ሰኔ 23/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ "ስማርት ካምፓስ ፕሮጀክት" ለመተግበር የሚያስችለውን ስምምነት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስማርት መማሪያ ክፍሎች እና የተለያዩ ዘመናዊ አሰራሮችን ለማቅረብ የሚያስችል ነው ተብሏል።

ስምምነቱ የትምህርት መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት፣ የቤተ-ሙከራ ፍተሻዎችን በተሻለ ተሞክሮ ለማከናወን፣ የምዘና ፈተናዎችን ለመስጠት የሚያስችል ስማርት የመማሪያ ክፍሎችን መገንባት እንደሚያካትትም ተገልጿል።

የስድስት ኪሎ ግቢ የመግቢያ በሮች፣ ዋና ዋና የአስተዳደር ህንጻዎችን፣ ሙዚየሙንና ሌሎች ስፍራዎች ላይ የሲሲቲቪ ካሜራ መግጠምና ተዛማጅ የመሰረተ ልማት ግንባታ የሚያካትት መሆኑም ተጠቁሟል።

ስምምነቱ የጥቁር አንበሳ አጠቃላይ ስፔሻላይድ ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት ክፍያዎችን በቴሌብር ለመፈጸም የሚያስችል መሆኑም ተሰምቷል፡፡

@tikvahuniversity
#MoE

ትናንት የተሰጠው የፋርማሲ ትምህርት የመውጫ ፈተና "የቴክኒክ ችግር" አጋጥሞት እንደነበር ትምህርት ሚኒስቴር አረጋገጠ።

ስለሆነም ፈተናውን በድጋሜ እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ፈተናው በድጋሜ ቅዳሜ ሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጠዋት ከ3:00 ሰዓት ጀምሮ እና ከሰአት ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ ይሰጣል ተብሏል።

ለፈተናው ተቀምጣችሁ የነበራችሁ የፋርማሲ ተማሪዎች በየተፈተናችሁበት የፈተና ጣቢያ በሰዓቱ በመገኘት በድጋሜ የሚሰጠውን ፈተና እንድትወስዱ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

@tikvahuniversity
በፀጥታ ችግር ምክንያት በአማራ ክልል በ2016 የትመህርት ዘመን ከ2.6 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው መራቃቸውን መንግሥት ገለፀ፡፡

በክልሉ በተካሔደ የትምህርት ንቅናቄ መድረክ ላይ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) እንደገለፁት፣ እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት ከ3 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶችም ዝግ ሆነው ቆይተዋል፡፡

ትምህርት በጀመሩ ተማሪዎች እና መምህራን ላይም ከፍተኛ ጫናና መዋከብ እንደደረሰ ኃላፊዋ ጠቁመዋል፡፡

በርካታ በክልሉ ገጠራማ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርት በመቆሙ ወደ ትዳር እየገቡ እንደሆነ ከክልሉ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በቅርቡ የተሰጡትን የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተናዎች የፀጥታ ችግር ባለባቸው የክልሉ አካባቢዎች በተለይም በምዕራብ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች አለመሰጠታቸው ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity
#2024_Commencement

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ከሳምንቱ መጨረሻ ጀምሮ ያስመርቃሉ፡፡

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም
አክሱም ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25-26/2016 ዓ.ም
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 26/2016 ዓ.ም
ቦረና ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 26/2016 ዓ.ም
አምቦ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
ደብረ ብርሃን - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 29/2016 ዓ.ም

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#MoE ትናንት የተሰጠው የፋርማሲ ትምህርት የመውጫ ፈተና "የቴክኒክ ችግር" አጋጥሞት እንደነበር ትምህርት ሚኒስቴር አረጋገጠ። ስለሆነም ፈተናውን በድጋሜ እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ አሳውቋል። ፈተናው በድጋሜ ቅዳሜ ሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጠዋት ከ3:00 ሰዓት ጀምሮ እና ከሰአት ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ ይሰጣል ተብሏል። ለፈተናው ተቀምጣችሁ የነበራችሁ የፋርማሲ ተማሪዎች በየተፈተናችሁበት የፈተና ጣቢያ በሰዓቱ…
#Update

ነገ ሰኔ 22/2016 ዓ.ም በድጋሜ የሚሰጠው የ2016 ዓ.ም የፋርማሲ ትምህርት ክፍል ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ለግማሽ ቀን ብቻ ይሰጣል።

ፈተናው ነገ በሁለት ፈረቃ ጠዋት እና ከሰዓት እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ከተፈታኞች ቁጥር አንጻር ፈተናው ጠዋት ከ2:30 ሰዓት ጀምሮ ለግማሽ ቀን ብቻ የሚሰጥ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

በዚህ የመውጫ ፈተና የሚቀመጡት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ እና ፈተናውን በድጋሜ የሚወስዱ ተፈታኞች መሆናቸው ተገልጿል።

የፋርማሲ ትምህርት ክፍል ዕጩ ተመራቂዎች በጤና ሚኒስቴር የሚዘጋጀውን የላይሰንሰር ፈተና በሌላ ጊዜ እንደሚሰጣቸው ተጠቁሟል።

@tikvahuniversity
#Update

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኳል።

የተማሪዎቹ ውጤት ዛሬ ለተቋማቱ መላኩን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከአንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል።

በዚህም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

የዘንድሮው የመውጫ ፈተና ለ57 የመንግሥት እና ለ124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በ244 የቅድመ ምረቃ መርሐግብሮች መሰጠቱ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
Photo
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዋን በመግደል ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በይግባኝ በእድሜ ልክ እስራት መቀጣቱን ፖሊስ ገለፀ።

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ግለሰብ በጩቤ ሦስት ቦታ በጀርባዋ በመውጋት የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱ ይታወሳል።

በውሳኔው ቅር የተሰኘው የአሶሳ ከተማ አስተዳደር አቃቤ ህግ ይግባኝ በመጠየቅ የእስራቱ ውሳኔ እንዲሻሻል በማለት የተከሳሹን የወንጀል ድርጊት ክብደትና ድርጊቱን የሚያስረዱ የሰው ማስረጃና የህክምና ማስረጃ በማስደገፍ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ጠቅላይ ፍ/ቤት ልኳል።

የይግባኝ መዝገቡ የደረሰው የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት መዝገቡን ሲመርምር ከቆየ በኃላ፣ ተከሳሹ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ በመሆኑ በይግባኝ ችሎት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹንም ያርማል ማህበረሰቡንም ያስተምራል በማለት በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ከአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#2024_Commencement የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ከሳምንቱ መጨረሻ ጀምሮ ያስመርቃሉ፡፡ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም አክሱም ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም አሶሳ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም ወለጋ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25…
#2024_Commencement
#የቀጠለ

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ከሳምንቱ መጨረሻ ጀምሮ ያስመርቃሉ፡፡

ዲላ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
ደምቢ ዶሎዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 29/2016 ዓ.ም
መቱ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 29/2016 ዓ.ም

@tikvahuniversity
#RayaUniversity

ራያ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የተቋሙ ተማሪዎች መካከል 97.55 በመቶ ማለፋቸውን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ካስፈተናቸው 286 ተማሪዎች መካከል 279 ተማሪዎች (97.55 በመቶ) ማለፋቸውን አሳውቋል።

@tikvahuniversity
#አሶሳ_ዩኒቨርሲቲ

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የመዉጫ ፈተና (Exit Exam) ካስፈተናቸዉ ተፈታኞች መካከል አብዛኞቹ ተፈታኞች ፈተናዉን እንዳለፉ አሳውቋል።

የውጤቱም ዝርዝር መረጃ በቀጣይ ይፋ እንደሚያደግ ገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/10/01 16:34:09
Back to Top
HTML Embed Code: