Telegram Web Link
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ የሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል ተመርቋል።

በማዕከሉ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የኢትዮጵያን ታሪክና ባህል ለውጪው ዓለም ይበልጥ እንዲተዋወቅ የሚጠበቀበትን ሚና እንዲወጣ ጠይቀዋል።

ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ አንጋፋውንና በኢትዮጵያ ቀዳሚ የሆነው የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የመጀመሪያው ዳይሬከተር ሆነው አገልግለዋል።

በኢትዮጵያ የዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ውስጥ ብርሃን ፈንጣቂ በመሆን የተለያዩ ዘመን አይሽሬ የሙዚቃ ሥራዎችን አበርክተዋል።

ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ ለዘመናዊ የሙዚቃ ዕድገት አሻራቸውን ያሳረፉ ዕውቅ ፕሮፌሰር መሆናቸውን የመስኩ ባለሙያዎች ይገልፃሉ። #ኢዜአ

@tikvahuniversity
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ነገ ሰኔ 3/2016 ዓ.ም መሰጠት ይጀምራል።

ፈተናው በተመረጡ የፈተና ማዕከላት በኦንላይን ይሰጣል።

የማጠቃለያ ፈተናው የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በሚፈተኑት የሒሳብ ትምህርት ይጀመራል።

ተፈታኞች ፈተናው መሰጠት ከሚጀምርበት ሰዓት 30 ደቂቃ ቀድመው መገኘት የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ የተከለከሉ ቁሳቁሶችን ወደ ፈተና ማዕከላት ይዘው መምጣት የለባቸውም ተብሏል።

@tikvahuniversity
በሪያድ እና በጂዳ ባሉ የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በኦንላይን ለሚሰጠው ፈተና ልምምድ ማድረግ ጀምረዋል።

ፈተናውን በኦንላይን የሚወስዱ ተፈታኞች ደጋግመው በመለማመድ ለፈተናው ዝግጁ እንዲሆኑ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መክሯል።

@tikvahuniversity
#BahirDarUniversity #FacultyPromotions

ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለሦስት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ዕድገት ሰጠ።

የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ለሦስት የዩኒቨርሲቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ዕድገት አፅድቋል።

የሙሉ ፕሮፌሰርነት ዕድገት ያገኙ ምሁራን፦

1. ዶ/ር አወቀ አንዳርጌ በአፕላይድ ሒሳብ
2. ዶ/ር ገብረእግዚአብሔር ካሕሳይ በ Solid State Physics.
3. ዶ/ር ታደሰ አምሳሉ በ Land Policy and Natural Resource.

ምሁራኑ ባበረከቷቸው የምርምር፣ የማኅበረሰብ አገልግሎት እና የመማር ማስተማር ሥራዎቻቸው ተገምግመው ከተባባሪ ፕሮፌሰርነት ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማደጋቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ፈተና ነገ ሰኔ 4/2016 ዓ.ም መሰጠት ይጀምራል።

በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 12 እስከ 14/2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡

የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 4-5/2016 ዓ.ም እንዲሁም የ6ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 12 እስከ 14/2016 ዓ.ም ድረስ እንሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መግለፁ ይታወቃል።

የ8ኛ ክፍል ፈተና በከተማዋ በሚገኙ 182 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለ86,672 ተማሪዎች የሚሰጥ ሲሆን፣ የ6ኛ ክፍል ፈተና ደግሞ በ183 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለ86,222 ተማሪዎች ይሰጣል ተብሏል።

ሁለቱንም ፈተናዎች የሚያስፈፅሙ ከ2,200 በላይ ፈታኞች፣ ከ700 በላይ ተቆጣጣሪዎች እንዲሁም 183 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች መመደባቸው ታውቋል።

@tikvahuniversity
በፀጥታ ችግር ምክንያት የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚያልፋቸው ተማሪዎች ክልሎች በሚያቀርቡት ጥያቄ መሰረት በልዩነት እንደሚፈተኑ ተገለጸ።

በቀጣይ ወር በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ 701,200 ተማሪዎች መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል፡፡

በቂ የኮምፒውተር አቅርቦት ባለባቸው ትምህርት ቤቶች በኦንላይን ተማሪዎች ከቤታቸው ወደ ተመደቡበት ትምህርት ቤት በመሔድ ፈተናውን እንደሚወስዱ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

የኮምፒውተርና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ክፍተት ባለባቸው ቦታዎች ደግሞ ተማሪዎች ከሰኔ 30/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች በመግባት ፈተናውን በወረቀት ይፈተናሉ ብለዋል፡፡

በዚህም ተማሪዎች ወይም የተማሪ ወላጆች ላፕቶፕ እንዲያሟሉ የሚገደዱበት ምንም አይነት አሰራር አለመኖሩን ዋና ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል።

ነገር ግን የኮምፒውተር እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች በግል ላፕቶፕ የመፈትን አቅምና ፍላጎት ያለው ተማሪ፣ ከፈተናው 10 ቀናት በፊት ላፕቶፑን ለሚመለከተው አካል አስረክቦ አስፈላጊው የቴክኒክ ምርመራና ፍተሻ ከተደረገለት በኋላ ፈተናውን መውሰድ እንደሚችል ገልፀዋል።

በፀጥታ ችግር ምክንያት የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚያልፋቸው ተማሪዎች ክልሎች በሚያቀርቡት ጥያቄ መሰረት በልዩነት ይፈተናሉ ብለዋል።

@tikvahuniversity
የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ዛሬ መሠጠት ጀምሯል።

የማኅበረሰብ ሳይንስ ተማሪዎች የሒሳብ ትምህርት ፈተና ሙሉ ቀን በአራት ክፍለጊዜ ተከፍለው በኦንላይን ሲወስዱ ውለዋል።

የማኀበረሰብ ሳይንስ ተማሪዎች እስከ ሐሙስ ድረስ ለተከታታይ አራት ቀናት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናቸውን የሚወስዱ ይሆናል።

78 ሺህ የሚሆኑ የሪሚዲያል ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከታህሳስ ጀምሮ ሲከታተሉ የቆየ ሲሆን፤ ውጤታቸው 30 በመቶ በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ሒደት እና 70 በመቶ በማዕከል በሚዘጋጅ ፈተና የሚለይ መሆኑ ይታወቃል።

ምስል፦
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
በአማራ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት የሚጠበቀውን ያህል የ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና እንደማይቀመጡ ተገለፀ።

በክልሉ የተፈጠረው ግጭት በተለይ በምስራቅ ጎጃም ዞን በርካታ ትምህርት ቤቶች እንዳያስተምሩ ማድረጉን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ገልጿል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሚገኙ 996 አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል የመማር ማስተማር ሥራቸውን እያከናወኑ የሚገኙት 32 ትምህርት ቤቶች ብቻ ናቸው።

በትምህርት ዘመኑ ከአንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ539,996 በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ እንደሚመጡ ቢታቀድም፣ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት ከ13,000 የሚበልጡ አይደሉም ብሏል መምሪያው።

በዞኑ 791 ት/ቤቶች 41,944 ተማሪዎች የ6ኛ ክፍል ፈተና እንደሚያስፈትኑ ቢጠበቅም፤ 12 ትምህርት ቤቶች በሁለት ዙር 506 ተማሪዎችን ብቻ ያስፈትናሉ ተብሏል።

በተመሳሳይ በዞኑ በ593 ትምህርት ቤቶች 38,203 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደሚወስዱ ቢታቀድም፣ በ10 ትምህርት ቤቶች 431 ተማሪዎች ብቻ በሁለት ዙር ፈተና የሚወስዱ ይሆናል።

በዞኑ በ65 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 19,657 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እንደሚወስዱ ቢታሰብም፤ 5 ትምህርት ቤቶች 577 ተማሪዎችን ብቻ በሁለት ዙር የሚያስፈትኑ ይሆናል።

የሰላም ዕጦት ችግሩ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ያደረገ፣ ተማሪዎችንና ማኅበረሰቡን በስነልቦና ያኮሰሰ እና ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የትምህርት ማኅበረሰብ አባላትን ከመደበኛ ሥራቸው ውጭ ያደረገ መሆኑን መምሪያው ገልጿል።

በአማራ ክልል ዘንድሮ 184,393 የ8ኛ ክፍል እንዲሁም 170,470 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መግለፁ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
ሰላም ሚኒስቴር ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር የክረምት በጎ ፊቃድ ስልጠና ለተማሪዎች መስጠት ጀምሯል።

አምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ መቐለ ዩኒቨርሲቲ እና ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ስልጠናውን ለተማሪዎቻቸው ትናንት መስጠት ጀምረዋል።

ተማሪዎቹ ትምህርታቸውንና ስልጠናውን ካጠናቀቁ በኋላ ለአንድ ወር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ይሰማራሉ።

ምስል፦ አምቦ፣ መቐለ እና ወራቤ ዩኒቨርሲቲዎች

@tikvahuniversity
የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የሁለተኛ ቀን ፈተና ዛሬ ይሰጣል።

የማኅበረሰብ ሳይንስ ተማሪዎች የጂኦግራፊ ትምህርት ፈተና በአራት ክፍለጊዜ ተከፍለው በኦንላይን ይወስዳሉ።

ትናንት በነበረው የመጀመሪያ ቀን ፈተና በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ተማሪዎች በተፈጠረ የቴክኒካል ችግር ምክንያት በቂ የፈተና ሰዓት እኖዳልነበራቸው በርካታ ተማሪዎች አስተያየታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አድርሰዋል።

የማኀበረሰብ ሳይንስ ተማሪዎች እስከ ሐሙስ ድረስ ለተከታታይ አራት ቀናት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናቸውን የሚወስዱ ይሆናል።

ምስል፦ አምቦ፣ ቡሌ ሆራ፣ ዳምቢ ዶሎ እና ዲላ ዩኒቨርሲቲዎች

@tikvahuniversity
2024/09/29 07:21:02
Back to Top
HTML Embed Code: