Telegram Web Link
የ8ኛ ክፍል ክልል/ከተማ አቀፍ ፈተና በመላ ሀገሪቱ በመሰጠት ላይ ይገኛል።

ፈተናው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 182 የመፈተኛ ጣቢያዎችም መሰጠት ጀምሯል።

በከተማዋ 86,672 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች እንደሚሰጥ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ መግለፁ ይታወቃል።

ተማሪዎች በጠዋቱ የፈተና ክፍለጊዜ የአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ፈተናዎችን የሚወስዱ ይሆናል፡፡

የፈተናውን አሰጣጥ የሚያስፈፅሙ ፈታኞች፣ ተቆጣጣሪዎች እና የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች መመደባቸው ተገልጿል።

ምስል፦ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

@tikvahuniversity
ዛሬ በመላ ሀገሪቱ መሠጠት የጀመረው የ8ኛ ክፍል ክልላዊና ከተማ አቀፍ ፈተና በአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ እየተሠጠ አይደለም።

በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት በምዕራብ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች ፈተናው እየተሰጠ አለመሆኑን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል።

"ወቅታዊ የፀጥታ ችግር በተፈጠረባቸው የምዕራብ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች አንድም ተማሪ እንደማይፈተን" የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሃን መናገራቸው ይታወሳል።

በተመሳሳይ 32 ትምህርት ቤቶች ብቻ የመማር ማስተማር ሥራቸውን እያከናወኑ በሚገኝበት ምስራቅ ጎጃም ዞን፣ በርካታ ተማሪዎች ለፈተናው አለመቀመጣቸው ታውቋል፡፡

“ምንም ዓይነት ተማሪ የማያስፈትኑ ሁለት ዞኖች አሉ፡፡ ሰሜን ጎጃም እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ምንም ተማሪ አያስፈትኑም፡፡ 6ኛም፣ 8ኛም፣ 12ኛም አያስፈትኑም፡፡ ምስራቅ ጎጃም የተወሰነ ያስፈትናል" ነበር ያሉት ኃላፊዋ፡፡

ፈተናው በሚሰጥባቸው ሌሎች ዞኖች ደግሞ ከ350 ሺህ በላይ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል፡፡ ለዓመታት ተቋርጦ የነበረው የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰኔ 13 እና 14/2016 ዓ.ም በአማራ ክልል ይሰጣል፡፡

ምስል፦ ደሴ፣ ባህርዳር እና ሰቆጣ

@tikvahuniversity
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በመጪው ክረምት ለሚሰጠው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠውን የአሰልጣኞች ስልጠና 224 አሰልጣኞች እየወሰዱ ነው ተብሏል፡፡

28 የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አማካይነት ለ60 ሺህ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሒሳብ፣ ሳይንስ እና እንግሊዝኛ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና እንደሚሰጥ ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ተናግረዋል።

በሐምሌ እና ነሐሴ ወራት የሚሰጠው ስልጠናው፤ የቅድመ አንደኛ፣ የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን የማስተማር ስነ-ዘዴ አቅም ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
#Update

በፀጥታ ችግር ምክንያት ምዝገባ ማድረግ ላልቻሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሁለተኛ ዙር ፈተና እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከትግራይ ክልል ውጭ ባሉ አካባቢዎች ከሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል።

በዚህም የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ደግሞ ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ተናግረዋል።

በትግራይ ክልል ከሐምሌ 2-12/2016 ዓ.ም በሁለት ዙር ፈተናው ይሰጣል ብለዋል።

ዘንድሮ 701,489 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን እና በወረቀት እንደሚወስዱ ተናግረዋል።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች በተለይም በአማራ ክልል የሚገኙና ምዝገባቸውን ማድረግ ላልቻሉ በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር ፈተና እንደሚዘጋጅ ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
የ8ኛ ክፍል ክልላዊ/ከተማ አቀፍ ፈተና ዛሬ ሰኔ 5/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

ፈተናው በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች በመሠጠት ላይ ነው።

የፀጥታ ችግር ያለባቸው አካባቢዎች በተለይም በምዕራብ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች ፈተናው እየተሠጠ አይደለም። በምስራቅ ጎጃም ዞን ደግሞ በከፊል እየተሰጠ ነው።

ከዓመታት በኋላ ባለፈው ዓመት በድጋሜ መሠጠት የጀመረው የ6ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 12 እስከ 14/2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡

@tikvahuniversity
የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የሦስተኛ ቀን ፈተና ዛሬ ይሰጣል።

የማኅበረሰብ ሳይንስ ተማሪዎች የታሪክ ትምህርት ፈተና በአራት ክፍለጊዜ ተከፍለው በኦንላይን ይወስዳሉ።

የሪሚዲያል ፕሮግራም የማኀበረሰብ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ነገ ከሚሰጠው የእንግሊዝኛ ትምህርት ፈተና በኋላ ይጠናቀቃል።

የተፈጥሮ ሳይንስ የሪሚዲያል ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናቸውን ነገ በሚሰጠው የእንግሊዝኛ ትምህርት ፈተና መውሰድ ይጀምራሉ።

ምስል፦ ሠመራ፣ ወለጋ እና ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲዎች

@tikvahuniversity
በአማራ ክልል በቀጠለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከ180 ሺህ በላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና አለመቀመጣቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለፀ፡፡

ዛሬ የሚጠናቀቀውን የ8ኛ ክፍል ክልል/ከተማ አቀፍ ፈተና ክልል አቀፍ ፈተና በክልሉ ፈተናውን መውሰድ ከነበረባቸው 369,827 ግማሽ ያህሉ ወይም ከከ180 ሺህ በላይ የሚሆኑት ፈተናውን እንዳልወሰዱ የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጌታቸው ቢያዝን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ 99 ሺህ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና እንደማይቀመጡ ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

ግጭቱ ባለባቸው የምዕራብ፣ ምስራቅ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች ያሉ ተማሪዎች ዓመቱን በሙሉ ያልተማሩና ጀምረው ያቋረጡ በመሆናቸው ለፈተናው መቀመጥ እንዳልቻሉ ነው ኃላፊው የገለፁት፡፡

ነሐሴ መጨረሻ ወይም በቀጣዩ ዓመት መስከረም ወር ላይ የይዘት ክለሳ ተደርጎና የማካካሻ ትምህርት ተሰጥቷቸው ተማሪዎቹ ለፈተና ሊቀመጡ እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡

ምስል፦ እንጅባራ

@tikvahuniversity
የፈተና ጥሪ

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በተለያዩ የህክምና ሙያ ባለሙያዎች አወዳድሮ ለመቅጠር ላወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ለተመዘገባችሁና ለተመረጣችሁ አመልካቾች የፈተና ጥሪ አድርጓል፡፡

በዚህም ስማችሁ ከላይ የተጠቀሰው ተወዳዳሪዎች ሰኔ 10/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ግቢ ለፈተና የተጠራችሁ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለፈተና ስትሔዱ ራሳችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡ በሰዓቱ መገኘት ይኖርባችኋል የተባለ ሲሆን፤ የሞባይል ስልክ ይዞ መግባት የተከለከለ ነው፡፡

@tikvahuniversity
ወንድ ልጅ የወለደለችው የ8ኛ ክፍል ተፈታኝ

ሐና ደሳለኝ በመሪ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በማታው መርሐግብር ተማሪ ናት፡፡

ባለትዳር የሆነችው ተማሪ ሐና፤ የመጀመሪያ ቀን የ8ኛ ክፍል ፈተናዋን ከተፈተነች በኋላ ትላንትና ማታ በድንገት ምጧ መምጣቱን ተከትሎ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ በመሔድ ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላለች፡፡

ፈተናዬን ሳልጨርስ አላቋርጥም በማለት የምጥ ድካሟ ገና በአግባቡ ሳይሽር የሁለተኛ ቀን ፈተናዋን በፈተና ጣቢያ አሰተባባሪዎች እገዛ ወስዳለች፡፡ #አአትቢ

@tikvahuniversity
2024/09/29 09:30:10
Back to Top
HTML Embed Code: