Telegram Web Link
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሐኪሞች በመድኃኒት እጥረት ምክንያት ሕክምና መስጠት መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡

በሆስፒታሉ የመድኃኒት አቅርቦትና የሕክምና መስጫ መሣሪያዎች እጥረት ምክንያት ተገቢውን ሕክምና መስጠት መቸገራቸውን በሆስፒታሉ የሚሠሩ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሕክምና ባለሙያዎች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በተለይ ዝቅተኛ የገቢ ምንጭ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ሕክምና ማግኘት አለመቻላቸውን የገለፁት ባለሙያዎቹ፤ "በአሁኑ ወቅት የመድኃኒት ዋጋ መወደድና ዩኒቨርሲቲው የተመደበለት በጀት አነስተኛ መሆን" ዋነኛ የችግሩ መንስዔ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም በጣም በቅናሽ ዋጋ ማግኘት የሚቻሉ እንደ አልኮል፣ መርፌና ምላጭ የመሳሰሉ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ታካሚዎች ከሆስፒታሉ ውጭ ከሚገኙ ፋርማሲዎች እንዲገዙ በማድረግ ለከፍተኛ ወጪ እየተዳረጉ መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎቹ ጠቁመዋል፡፡

የመድኃኒት ዋጋ በእጥፍ መጨመሩ፣ እንዲሁም የሁሉም የዩኒቨርሲቲዎች በጀት 50 በመቶ እንዲቀነስ መደረጉ ለመድኃኒት ግዥ የሚሆን በጀት እጥረት እንዲከሰት ማድረጉን የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጀማል አባፊጣ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ ሪፖርተር የጤና ሚኒስቴርን ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካለትም፡፡ #ሪፖርተር

@tikvahuniversity
#MoH

በውጤታችሁ ላይ ጥያቄ ያላችሁ የጤና መስክ ተመዛኞች ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ።

ባለፈው ወር በትምህርት ሚኒስቴር እና በጤና ሚኒስቴር በጋራ የተሰጠውን የመውጫ እና የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ #የጤና_መስክ ተመዛኞች ውጤት ከመጋቢት 04/2016 ዓ.ም ጀምሮ ኦንላይን እየተመለከቱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በውጤታችሁ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች ያላችሁ ተመዛኞች ከመጋቢት 04/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0118275936 በመደወል ወይም በኢሜይል አድራሻ [email protected] ብቻ ሙሉ ስም፣ ሙያ እና የፈተና መለያ ቁጥር (Username) በማስገባት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ ተመዛኞች ስም ዝርዝር ለክልል የጤና ተቆጣጣሪ አካላት የሚላክ በመሆኑ በየክልላችሁ በመሔድ የሙያ ሥራ ፍቃድ ማውጣት እንደምትችሉም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ተመዝግበዋል፡፡ - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ የተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ ከየካቲት 3-30/2016 ዓ.ም መከናወኑ ይታወቃል፡፡

በዚህም ፈተናውን ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ መካሔዱን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው የአገሪቱ አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ ተካሒዶ መጠናቀቁን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ በዚህ ሳምንት እንደሚከናወን ጠቁመዋል፡፡

የፈተና ዝግጅት ሥራው ተማሪዎቹን በአግባቡ ለመመዘን በሚያስችል መልኩ ጠቀሱት ኃላፊው፤ በቀጣይ የፈተናው ሕትመት ይጀመራል ብለዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ ወደፊት ይፋ ይሆናል ተብሏል። #ኢዜአ

@tikvahuniversity
#AksumUniversity

በ2016 ዓ.ም ለስፔሻሊቲ ስልጠና አክሱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ መጋቢት 16 እና 17/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ (ሪፈራል ካምፓስ)

@tikvahuniversity
ተግባር ተኮር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ የተለየው ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም. ወደ ትግበራ ይገባል፡፡

ተቋሙ ተግባር ተኮር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ መሆን የሚያስችለውን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ማጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፋሪስ ደሊል (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

ግብርና፣ ኢንጅነሪንግና ቴክኖሎጂ፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ እንዲሁም የጤና ዘርፍ የዩኒቨርሲቲው የትኩረት መስኮች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በአራቱም የዩኒቨርሲቲው ኮሌጆች የተግባር ትምህርት ለመስጠት የሚያስችሉ ቤተ-ሙከራዎች የመገንባትና የማጠናከር ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የመምህራን አቅም መገንባት፣ የተጨማሪ የዳታ ማዕከል ግንባታ፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅም ማጎልበት እንዲሁም የሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶች ማሟላት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ፕሬዝዳንቱ ጠቅሰዋል፡፡ #ኢፕድ

@tikvahuniversity
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ባለ ስምንት ወለል ህንጻ ሊያስገነባ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው ያወጣውን የፕሮጀክት ጨረታ ያሸናፈው ጉተማ ፈሬሳ ኮንስትራክሽን የግንባታ ማስጀመርያ ስምምነት ውል ከዩኒቨርሲቲው ጋር ተፈራርሟል፡፡

ህንጻው ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ዘመናዊ የመማሪያ ክፍሎች፣ አገልግሎት የሚሰጡ ዘመናዊ ክፍሎች በዘመናዊ ግብዓቶች ይደራጃል ተብሏል፡፡

ህንጻው ተቋሙ የጀመረውን ራስ-ገዝ የመሆን ሒደት የሚያፋጥን እንደሚሆን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ፍቅሬ ደሳለኝ ገልፀዋል፡፡

2.3 ቢሊየን ብር ወጪ የሚገነባው ህንጻው 19 ቢሮዎች፣ 24 የመማሪያ ክፍሎች፣ 18 ስማርት ክፍሎች፣ ሁለት አዳራሾች፣ 11 ሶቆች፣ አንድ ቤተመጻህፍት፣ ስድስት የተማሪዎች ኮርነስ እና የመኪና ማቆሚያ እንደሚይዝ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
በቱኒዚያ በተካሔደው የሁዋዌ አይ.ሲ.ቲ. ውድድር ሦስተኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና በሚካሔደው የፍፃሜ ውድድር ይሳተፋሉ፡፡

ባለፈው ሳምንት በቱኒዚያ በተካሔደው ክፍለ አኅጉራዊ የፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው ከተወዳደሩት ዘጠኝ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል በኮምፒውቲንግ ትራክ የተወዳደሩት የሦስት ተማሪዎች ቡድን በሦስተኛ ደረጃ ማጠናቀቁ ይታወቃል፡፡ ሁለቱ ተማሪዎች የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፤ አንዱ ደግሞ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው።

ሞሮኮ እና ቱኒዚያን ተከትለው ሦስተኛ ደረጃን ያገኙት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች፤ ዘመናዊ የሁዋዌን ስልክ የተሸለሙ ሲሆን የተቀሩት ስድስት ተማሪዎች ለተሳትፏቸው የሁዋዌ ታብሌቶችን ተሸልመዋል።

አሸናፊዎቹ ተማሪዎች በ2024 በቻይና በሚካሔደውና ከ500 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ከ20 ሺህ በላይ ተማሪዎች በሚሳተፉበት የመጨረሻው ምዕራፍ ውድድር እንደሚሳተፉ የሁዋዌ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሊሚንግ ዬ ገልፀዋል። #ሪፖርተር

@tikvahuniversity
#AddisAbabaUniversity

በ2016 ዓ.ም ለስፔሻሊቲ ስልጠና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) ማክሰኞ መጋቢት 17/2016 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ምዝገባ እስከ ሰኞ መጋቢት 16/2016 ዓ.ም ቀን 6፡00 ሰዓት በኦንላይን https://portal.aau.edu.et. እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

➤ የሥራ መደብ፦ በተለያዩ ሙያ መስኮች
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 23
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ 2ኛ ዲግሪ
➤ የሥራ ቦታ፦ ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ
➤ የማመልከቻ ጊዜ፦ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት

አመልካቾች ስትመዘገቡ የትምህርት እና የሥራ ልምድ ማስረጃ ዋናውና የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

በኢሜይል ለመመዝገብ፦ 𝘒𝘥𝘶𝘩𝘳𝘥@𝘬𝘥𝘶.𝘦𝘥𝘶.𝘦𝘵

ለተጨማሪ መረጃ፦ +251252401076

@tikvahuniversity
#HawassaUniversity

በ2016 ዓ.ም ለስፔሻሊቲ ስልጠና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ መጋቢት 18 እና 19/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ምዝገባ ለማድረግ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት በኢሜይል [email protected] ወይም በፖ.ሳ.ቁ. 05 አስቀድሞ ማስላክ ይጠበቅባችኋል።

የምዝገባ ቦታ፦
በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሬጅስትራር ቢሮ

ተመዝጋቢዎች ከዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ሬጅስትራር እና ድኅረ ምረቃ ትምህርት ቤት “Admission” እና “Acceptance” ደብዳቤ መያዝ ይኖርባችሀኋል።

ማንኛውም ተመዝጋቢ አስቀድሞ ይሠራበት ከነበረ ተቋም ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

ኦረንቴሽን መጋቢት 20/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tilvahuniversity
#Update

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ ማድረጋቸውን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በቅርቡ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው የአገሪቱ አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ መጠናቀቁም ተገልጿል።

የፈተናው ሕትመት በቀጣይ ቀናት እንደሚጀመር ለኢሳት የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥም አረጋግጠዋል፡፡

ለ3ኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው፤ ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡

@tikvahuniversity
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አዳዲስ የአጭር ጊዜ ስልጠናዎች ለመስጠት ስርዓተ ትምህርት አዘጋጅቷል።

ኢንስቲትዩተ የሁለት መደበኛ ስልጠና ስርዓተ ትምህርት ክለሳም አድርጓል።

12 ሙያዎች ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የአጭር ጊዜ ስልጠናዎች ለመስጠት አዲስ ስርዓተ ትምህርት መዘጋጀቱን የኢንስቲትዩቱ ስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ዋ/ዳይሬክተር ሀብታሙ ክብረት ገልጸዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ በዓለም ባንክ EASTRIP ፕሮጀክት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ያካሔደውን የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት መሰረት በማድረግ የስርዓተ ትምህርት እና የመማሪያ ሰነድ ማዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

ስርዓተ ትምህርት ከተዘጋጀላቸው ሙያዎች መካከል፦

- የውጭ ቋንቋዎች ስልጠና (እንግሊዘኛ፣ አረብኛ እና ፈረንሳይኛ)
- የትኩስ መጠጥ አገልግሎት (Bartender Service)፣
- የመጠጥ አግልግሎት (Barista Service)፣
- የሥጋ ቤት አገልግሎት (Butchery)፣
- ጤናና ውበት (Wellness and Spa Service) ይገኙበታል፡፡

@tikvahuniversity
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከፍትህ እና ሕግ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር 8ኛውን ሀገር ዓቀፍ የአምሳለ ችሎት ውድድር ያካሒዳል።

በሀገሪቱ የሚገኙ የሕግ ትምህርት ቤቶችን በመወከል ያለፉ ተማሪዎች ከመጋቢት 20 እስከ 22/2016 ዓ.ም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በሚካሔደው ውድድር ይሳተፋሉ።

@tikvahuniversity
#BahirDarUniversity

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ለተከታተሉ ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ Freshman ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸሁን በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት በማምጣት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ከመጋቢት 26 እስከ 28/2016 ዓ.ም መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
➤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሰላም ግቢ
➤ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በግሽ አባይ ግቢ

በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለአንደኛ ዓመት የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላችሁና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ምዝገባ መጋቢት 30/2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#BahirDarUniversity

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለዘጠኝ ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል።

የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ ምሁራኑ በየመስኳቸው የነበራቸውን ልዩ አበርክቶ በመገምገም የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷቸዋል።

የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው ምሁራን፦

1. ሙሉጌታ አድማሱ ደለለ (Bio Systems Engineering)
2. ታምራት ተስፋዬ ይመር (Biorefinery Engineering)
3. አስማማው ጣሰው ወልዴ (Animal Production)
4. መላኩ አለማየሁ ወርቄ (Horticulture)
5. የሻምበል መኩሪያው ቸከኮል (Animal Nutrition)
6. አቻምየለህ ጋሹ አዳም (Land Governance)
7. ምርኩዝ አበራ አድማሱ (Plant Pathology)
8. ታደሠ መለሠ መራዊ (Curriculum and Instruction)
9. አስራት ዳኘው ከልካይ (Curriculum and Instruction)

ቦርዱ የምሁራኑን የማስተማር ሥራ፣ የምርምር ተሳትፎ፣ የማህበረሰብ አገልግሎት እና በተቋማዊ ጉዳይ ያላቸውን አስተዋፆ በመገምገም የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ማፅደቁን ከተቋሙ የተገኘ መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity
#AdigratUniversity

በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁና በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በ2014 ዓ.ም ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድባችሁ መማራችሁ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ በ2013 ዓ.ም ከዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ስትወጡ ያልጨረሳችሁት የተወሰኑ የትምህርት ዓይነቶች መኖራቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በመሆኑም ከዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ስትወጡ ያላጠናቀቃችሁት ትምህርት ያላችሁ ተማሪዎች በዚህ ሴሚስተር እንድታጠናቅቁ ከመጋቢት 28 እስከ 30/2016 ዓ.ም ባለው ግዜ መመዘገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

@tikvahuniversity
2024/09/30 19:23:50
Back to Top
HTML Embed Code: