Telegram Web Link
#MoH

ባለፈው ወር በትምህርት ሚኒስቴር እና በጤና ሚኒስቴር በጋራ የተሰጠውን የመውጫ እና የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ የጤና መስክ ተመዛኞች ውጤታችሁን ኦንላይን መመልከት ትችላላችሁ፡፡

http://hple.moh.gov.et/hple/candidates/index4 ላይ በመግባት፣ ሙሉ ስም እና በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Username) በማስገባት የብቃት ምዘና ፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በውጤታችሁ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች ያላችሁ ተመዛኞች ከመጋቢት 04/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0118275936 በመደወል ወይም በኢሜይል አድራሻ [email protected] ብቻ ሙሉ ስም፣ ሙያ እና የፈተና መለያ ቁጥር (Username) በማስገባት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ ተመዛኞች ስም ዝርዝር ለክልል የጤና ተቆጣጣሪ አካላት የሚላክ በመሆኑ በየክልላችሁ በመሔድ የሙያ ሥራ ፍቃድ ማውጣት የምትችሉ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#BuleHoraUniversity

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ያሰለጥናቸውን 618 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ 182 ተማሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ ኮሌጆች ለሁለተኛ ጊዜ የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ 181 ተማሪዎች በድምሩ 363 ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን በማለፍ ለምረቃ የበቁ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በይርጋ ጨፌ ከተማ የቡና ምርምርና ሥልጠና ማዕከል ሊያስገነባ ነው፡፡

በሁለት ቢሊዮን ብር ወጪ በጌዴኦ ዞን በይርጋ ጨፌ ከተማ የሚገነባው ማዕከሉ፤ በኢትዮጵያ ቡናን ከታች ጀምሮ በአግባቡ ለመጠቀምና በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡

ማዕከሉን ለመገንባት 15 ሔክታር መሬት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት መረከቡን የዲላ ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ ከመመደቡም ባሻገር በቡና የልህቀት ማዕከል ሆኖ እንዲሠራ አቅጣጫ መቀመጡን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ችሮታው አየለ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የቡና ምርምር ማዕከል አቋቁሞ ላለፉት ስድስት ዓመታት የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናወን መቆየቱን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፣ አጫጭር ሥልጠናዎች እንዲሁም ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የቡና ሳይንስና ኢኮኖሚክስ በሁለተኛ ዲግሪ ሥልጠና በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

የማዕከሉ የምሥረታ ሰነድ በትምህርት ሚኒስቴር ዕውቅና ለፕላንና ልማት ሚኒስቴር ተልኮ የፕሮጀክቱ ፈቃድ በመጠባበቅ ላይ እንደሆነ ጠቁመው፤ ባለድርሻ አካላትን ያማከለ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል፡፡ #ሪፖርተር

@tikvahuniversity
በቱኒዚያ በተካሔደው የሁዋዌ አይ.ሲ.ቲ. የክፍለ አህጉራዊ ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሦስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡

ከየካቲት 28 እስከ መጋቢት 1/2016 ዓ.ም በቱኒዚያ በተካሔደው የሁዋዌ አይ.ሲ.ቲ. ውድድር ክፍለ አህጉራዊ የፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው ከተወዳደሩት መካከል በኮምፒውቲንግ ትራክ (Computing Truck) የተወዳደሩት የሦስት ተማሪዎች ቡድን ሞሮኮ እና ቱኒዚያን ተከትለው ሦስተኛ ደረጃን አግኝቷል።

በውድድሩ ከኢትዮጵያ፣ ማሊ፣ ካሜሩን፣ ሴኔጋል፣ አልጄሪያ፣ ቱኒዝያ፣ ሊቢያ፣ ግብፅ እና ሞሮኮ የተውጣጡ 90 ተማሪዎች በተለያየ የውድድር ዘርፍ ተሳታፊ ሆነዋል። #Capital

@tikvahuniversity
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በዶክትሬት ዲግሪ የኅብተረተሰብ ጤና ትምህርት (DrPH) ማስጀመሪያ መርሐግብር አካሒዷል።

የሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከያዝነው ዓመት ጀምሮ እንደሚሰጥ ይፋ ተደርጓል፡፡

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሮግራሙን ለመጀመር ባለፉት አምስት ዓመታት ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የተቋሙ የጤናና ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ መሐመድ ተናግረዋል፡፡

ፕሮግራሙ በሀገሪቱ ጤና ተቋማት ውስጥ ያለውን የአመራር ክፍተት ለመሙላት የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡

የፕሮግራሙ ስርዓተ ትምህርት በመፅደቁ ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ተማሪዎችን መቀበል እንደሚጀምር የተገለፀ ሲሆን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ ይህንኑ መርሀሐግብር ለማስጀመር ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#WachemoUniversity

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ መጋቢት 9 እና 10/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ተመዝጋቢዎች በንግስት እሌኒ መታሰቢያ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት የሥራ ቅጥር መፈፀም እንዳለባችሁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ለምዝገባ እና ለሥራ ቅጥር የሚያስፈልጉ አስፈላጊ ሰነዶችን ከላይ ከተያያዘው የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ይመልከቱ።

@tikvahuniversity
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታችሁን በእንግሊዝኛ ቋንቋ መማራችሁን የሚገልጽ ደብዳቤ (Letter of Proficiency) እንዲፃፍላችሁ የምትፈልጉ አገልግሎቱን ከትምህርት ሚኒስቴር ማግኘት ትችላላችሁ።

ተገልጋዮች ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ስትሔዱ ማሟላት የሚጠበቅባችሁ፦

➧ 12ኛ ክፍል ማጠናቀቃችሁን የሚገልፅ ሰርተፊኬት (አንድ የማይመለስ ኮፒ)፣

➧ በቀድሞው የትምህርት ፖሊሲ 10ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ከሆነ፥ 10ኛ ክፍል ማጠናቀቃችሁን የሚገልፅ ሰርተፊኬት (አንድ የማይመለስ ኮፒ)፣

➧ ማንነታችሁን የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት/መንጃ ፈቃድ ከማይመለስ አንድ ኮፒ ጋር ማቅረብ።

አገልግሎቱ የሚሰጠው ሰኞ እና ሐሙስ በሥራ ሰዓት ብቻ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 202 ተማሪዎች አስመረቀ።

ኮሌጁ 65 የሕክምና ዶክተሮች፣ 49 የስፔሻሊቲ ሐኪሞች እና 88 በኅብረተሰብ ጤና ሳይንስ የሰለጠኑ ተማሪዎችን አስመርቋል።

ኮሌጁ ከ13 ዓመታት በፊት የሕክምና ሙያ ትምህርትን መስጠት የጀመረ ሲሆን በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ወደ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለማደግ እየሠራ ይገኛል።

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
ትናንት መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ከኢትዮጰያ ንግድ ባንከ ኤ.ቲ.ኤም ማሽን የሌላቸውን ገንዘብ ወጪ ያደረጉ የተቋሙ ተማሪዎች በፍጥነት በቅሊንጦ ቅርንጫፍ በመቅረብ እንዲመልሱ አሳስቧል።

ወጪ ያደረገውን ገንዘብ የማደመልስ ተማሪ ላይ ዩኒቨርሲቲው አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድና ተማሪዎቹ በሕግ እንደሚጠየቁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በተመሳሳይ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከትክክለኛ ሒሳባቸው ውጪ ገንዘብ ወጪ ያደረጉ ተማሪዎች የራሳቸው ያለሆነውን ገንዘብ በአስቸኳይ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የትኛውም ቅርንጫፍ በመሔድ ተመላሽ እንዲያደርጉ በጥብቅ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ችግር ምክንያት ዛሬ የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞት እንደነበር መግለፁ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#Update

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውና ሌሎችም የተቋሙ አካላት በካሽ የወሰዱትን እና ለሌላ ሶስተኛ ወገን ያስተላለፉትን ገንዘብ እንዲመልሱ አስጠነቀቁ።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲስተም ላይ ካጋጠመው ችግር ጋር በተያያዘ በርካቶች ገንዘብ ያለገደብ ሲያወጡና ሲያስተላልፉ ነበር።

በተለይም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አካላት ትላንት ካጋጠመው ችግር ጋር በተያያዘ ገንዘብ ወጭ ሲያደርጉና ወደ ሌላም ሲያስተላልፉ እንደነበር ተነግሯል።

ይህንን ተከትሎ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ ያወጡና ያስተላለፉ እንዲመልሱ ተቋሞቻቸው እያሳሰቡ ይገኛሉ።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ባንኩ የተፈጠረዉን ችግር በተመለከተ ፦
* ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፤
* የመረጃ እና ደህንነት እንዲሁም ከሌሎች ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ጋር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በባንኩ የተፈጠረዉን የሲስተም መቋረጥ ምክንያት እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ፦
➡️ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ #በካሽ ወጭ ያደረጉና በማንኛዉም የባንኩ የድጅታል አማራጮች የተቀበሉ
➡️ ወደ 3ኛ ወገን ያስተላለፉ ተማሪዎች እና የዩንቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት የወሰዱትን እና የተላለፈላቸውም አካላት ገንዘቡን ተመላሽ እንዲያደርጉ አስጠንቅቀዋል።

ገንዘቡ ተመላሽ የሚደረገው በአቅራቢያ ባለ የባንኩ ቅርንጫፍ መሆኑን አሳውቀዋል።

ለመመለስ ፈቃደኛ ካልሆኑ ጉዳዩ የሕግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑንም እየገለጹ ናቸው። ገንዘብ ያወጡ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ስም ዝርዝር እንዳላቸውም ጠቁመዋል።

@tikvahethiopia
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትላንት መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ምሽት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካጋጠመው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ የማይገባ ገንዘብ ከኤ.ቲ.ኤም (ATM) ማሽን ወጪ ያደረጉየዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት ካሉ ወደ ባንኩ ቅርንጫፎች በመሄድ ገንዘቡን ተመላሽ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

@tikvahuniversity
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት መደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች እየወሰዱ ከሚገኙት የማጠቃለያ ፈተና ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችን ለቲክቫህ አድርሰዋል።

ተማሪዎቹ ለቲክቫህ በላኩት መረጃ ፈተናዎቹ መሰረቃቸውን ጨምሮ በርካታ የዲሲፕሊን ጥሰት መፈፀማቸውን በመጥቀስ ዩኒቨርሲቲው የዕርምት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ግንኙነትና የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር እመቤት በቀለ (ዶ/ር) በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰጥተዋል።

በፈተናው ላይ የዲሲፕሊን ጥሰት መፈፀሙን የተመለከቱ ቅሬታዎች መቅረባቸው እውነት መሆኑን የጠቆሙት ዳይሬክተሯ፤ በተለይ አንድ ፈተና መሰረቁን አረጋግጠዋል።

በመሆኑም እንደተሰረቀ የተረጋገጠው ፈተና (Emerging Technology) መሠረዙን ገልፀዋል። ምትክ ፈተና መጋቢት 16/2016 ዓ.ም. ጠዋት 2፡30 ላይ የሚሰጥ መሆኑም ተገልጿል።

"ጉዳዩ እንዴት ተፈፀመ በሚለው ላይ የማጣራት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝና ወንጀሉን በፈፀሙት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ" ተናግረዋል።

ከዚህ ውጪ "ሁሉም ፈተና ተሰርቋል" የሚለው መረጃ ሐሰት መሆኑና የዩኒቨርሲቲውን ስም ለማጥፋት የሚደረግ ጥረት እንደሆነ ገልፀዋል።

ተማሪዎች ባልተረጋገጡ ሐሰተኛ የማኅበራዊ ሚዲያ መረጃዎች እንዳይደናገሩና በትዕግስት ውጤታቸውን እንዲጠብቁ ዳይሬክተሯ ጥሪ አድርገዋል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ፡፡

የብሪቲሽ ካውንስል IELTS የፈተና ማዕከል ሦስተኛ ዙር የ IELTS ፈተና ግንቦት 17/2016 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡

ፈተናውን ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ በመከናወን ላይ ይገኛል።

ሁለት አይነት የ IELTS ፈተናዎች (IELTS Academic and IELTS General Training) መውሰድ ለሚፈልጉ አመልካቾች እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡

የብሪቲሽ ካውንስል ድረገፅ ላይ በመግባት ኦንላይን መመዝገብ ይችላሉ 👇
https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts/dates-fees-locations

ለፈተናው ዝግጅት የሚያስፈልግዎትን ስልጠና እና ምክር ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማግኘት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ፦ 0925629589

@tikvahuniversity
2024/09/30 21:39:38
Back to Top
HTML Embed Code: