Telegram Web Link
ትምህርት ሚኒስቴር "ለትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥና ለአቻ ግመታ" የወጣ መመርያ ፀድቆ ሥራ ላይ መዋሉን አስታውቋል፡፡

ሥራ ላይ ከዋለ አንድ ሳምንት ያለፈው መመርያው፤ የኃይማኖት ነክ ተመራቂዎች የትምህርት ማስረጃ የምዘና አገልግሎት እንደማያገኙ መገለፁን ሪፖርተር ጋዜጣ የደረሰውን ሰነድ በመጥቀስ ዘግቧል፡፡

የትምህርት ማስረጃ ለማረጋገጥ መሟላት ያለባቸው፦

- የሚረጋገጠው ማስረጃ ትምህርት ማጠናቀቁን ለማረጋገጥ የተጠየቀበት ማመልከቻ፣
- አስፈላጊ መረጃዎች በባለሥልጣኑ የመረጃ ቋት ውስጥ አስቀድሞ ማስመዝገብ፣
- የከፍተኛ ትምህርት የመግቢያ ሰርተፊኬት ማቅረብ፡፡

የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ለማጣራት መሟላት ያለባቸው፦

- የመጀመሪያ ዲግሪ ትራንስክሪፕት፣
- የከፍተኛ ትምህርት የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ መግለጫ ሰርተፊኬት፣
- የዲፕሎማ ትራንስክሪፕት፡፡

የድኅረ ምረቃ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ለማረጋገጥ መሟላት ያለባቸው፦

- የሁለተኛ ዲግሪ የምስክር ወረቀት፣
- የመመረቂያ ጽሑፍ፣
- የመጀመሪያ ዲግሪ ትራንስክሪፕትና ሌሎችም ይጠቀሳሉ፡፡

በባለሥልጣኑ ዕውቅና ከተዘጋ ተቋም የተዘዋወሩ ተማሪዎች የትምህርት ማስረጃቸው ተቀባይነት እንደማያገኝ ሰነዱ ያብራራል፡፡

የምዘና አገልግሎት ምስክር ወረቀት የጠፋበት ግለሰብ ሁሉንም መሥፈርቶች በድጋሚ በማሟላት ምትክ የምዘና ምስክር ወረቀት እንደሚሰጠው መመርያው ይገልጻል፡፡

በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ የሆነውን መመርያው አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የትምህርት ሚኒስቴር በማንኛውም ጊዜ ሊያሻሽለው እንደሚችል በመመርያው ውስጥ ተካቷል፡፡ #ሪፖርተር

@tikvahuniversity
#DebreTaborUniversity

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት እና ሪሚዲያል ተማሪዎች እስከ አርብ መጋቢት 06/2016 ዓ.ም. ምዝገባ ማድረግ እንደሚችሉ አሳውቋል፡፡

የአንደኛ ዓመት እና ሪሚዲያል ተማሪዎች ምዝገባ ከየካቲት 25 እስከ 27/2016 ዓ.ም. መከናወኑን ዩኒቨርሲቲው አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች ለምዝገባ መድረስ ያልቻሉ ተማሪዎች እስከ አርብ መጋቢት 06/2016 ዓ.ም. ድረስ ብቻ መመዝገብ እንደሚችሉ ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#MoE

የመውጫ ፈተና ኩረጃ እና ሌሎች የፈተና ስነ-ምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ መሰረዙን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

ሚኒስቴሩ ዛሬ መጋቢት 2/2016 ዓ.ም. ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ ውሳኔውን አሳውቋል።

የፈተና ስነ-ምግባር ጥሰት የፈጸሙት 114 ተፈታኞች ውጤታቸው ሙሉ በሙሉ መሰረዙንና የሚወሰዱ ተጨማሪ እርምጃዎች በቀጣይ የሚገለጽ መሆኑ በደብዳቤው ተመልክቷል።

ከየካቲት 6 እስከ 11/2016 ዓ.ም. በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተሰጠው ሁለተኛ ዙር የመውጫ ፈተና ከ119 ሺህ በላይ ተፈታኞች ለፈተና መቀመጣቸው ይታወሳል።

@tikvahuniversity
#WolkiteUniversity

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ መጋቢት 9 እና 10/2016 ዓ.ም. መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ተመዝጋቢዎች ከምዝገባ ቀናት አስቀድመው የመጀመሪያ ዲግሪ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጂስትራር በፖ.ሳ.ቁ. 07 ወይም በኢ-ሜይል አድራሻ [email protected] ማስላክ ይኖርባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
የካቲት 12 ሆስፒታል ሕክምና ኮሌጅ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ መጋቢት 9 እና 10/2016 ዓ.ም. መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

• የቅድመ-ምረቃ ዲግሪ እና Student Copy ዋናውና ኮፒው፣
• ሁለት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
• የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ፣
• ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት ለኮሌጁ በፖ.ሳ.ቁ. 257 ማስላክ፣
• የ Clearance ደብዳቤ፡፡

@tikvahuniversity
#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ መጋቢት 5 እና 6/2016 ዓ.ም. መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ተመዝጋቢዎች ከምዝገባ ቀናት አስቀድመው የመጀመሪያ ዲግሪ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት ለጅማ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር በፖ.ሳ.ቁ. 378 ማስላክ ይጠበቅባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች የፊታችን ሐሙስ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም. ያስመርቃል፡፡

በተቋሙ ዋናው ግቢ በሚካሔደው የምረቃ ስነ-ስርዓት፤ በዩኒቨርሲቲው ጤና ኢንስቲትዩት እንዲሁም በተለያዩ ኮሌጆች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ተማሪዎች እበንደሚመረቁ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#WolloUniversity

በ2016 ዓ.ም. በወሎ ዩኒቨርሲቲ በ General Surgery, Internal Medicine, Gynecology and Obstetrics እና Pediatrics and Child Health የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች የምዝገባ ጊዜ መጋቢት 5 እና 6/2016 ዓ.ም. መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት መጋቢት 9/2016 ዓ.ም. እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
# HaramayaUniversity

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ መጋቢት 9/2016 ዓ.ም. መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
የ Clearance ደብዳቤ፣
የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ፣
ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት ለዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር በፖ.ሳ.ቁ. 235 ማስላክ፡፡

@tikvahuniversity
#MaddaWalabuUniversity

በ2016 ዓ.ም ለቀዶ ሕክምና እና ለማህፀንና ፅንስ ሕክምና ስፔሻሊቲ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ መጋቢት 12 እና 13/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በተጠቀሱት ቀናት ብቻ በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር (ጎባ ካምፓስ) በአካል በመገኘት ምዝገባ አድርጉ የተባለ ሲሆን ትምህርት መጋቢት 16/2016 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#DebreMarkosUniversity

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ.ም ነባር እና አዲስ አንደኛ ዓመት መደበኛ የቅድመ-ምረቃ እና የሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል፡፡

➢ የ1ኛ ዓመት ነባር ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያላችሁ ነባር ተማሪዎች ምዝገባ መጋቢት 16 እና 17/2016 ዓ.ም በየነበራችሁበት ካምፓስ ይከናወናል ተብሏል።

➢ በ2016 ዓ.ም የተመደባችሁ አዲሰ ገቢ ፍሬሽማን እና የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ መጋቢት 16 እና 17/2016 ዓ.ም ይከናወናል።

የምዝገባ ቦታ፦

- ለአዲስ ገቢ ፍሬሽማን ተማሪዎች፦ በዋናው ግቢ
- የ2016 ዓ.ም አዲስ ገቢ የሪሚዲያል ተማሪዎች ስማችሁ ከA-G የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እና ስማችሁ ከA-H የሚጀምር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በቡሬ ካምፓስ፤ ሌሎች ደግሞ በዋናው ካምፓስ።

አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ ለምዝገባ ስትሔዱ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት እና የ12ኛ ክፍል ስርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው እንዲሁም ስምንት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

በተለያየ ምክንያት ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ የ1ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች መመዝገብ የምትችሉ መሆኑም ተገልጿል።

@tikvahuniversity
በ2016 የትምህርት ዘመን በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የተመዘገባችሁ አዲስ መደበኛ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ትምህርት ለመጀመር በመጠባበቅ ላይ እንደምትገኙ ይታወቃል፡፡

በአጠቃላይ የትምህርት አጀማመርና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ኦሬንቴሽን መጋቢት 9/2016 ዓ.ም ጠዋት 3:00 በተቋሙ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚሰጥ ኢንስቲትዩቱ ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#WallagaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ቤት አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ መጋቢት 11 እና 12/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

ዲግሪ/ቴምፖራሪ/ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣
ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ፣
ስምንት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ለሁለት ቀናት የሚቆይ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ፎረም ሊካሔድ ነው፡፡

"ከፍተኛ ትምህርት ለከፍተኛ ውጤት" በሚል ጭብጥ ላይ የሚመክረው ፎረም፤ ከነገ መጋቢት 6/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት በጅማ ዩኒቨርሲቲ ይካሔዳል፡፡

ፎረሙ በትምህርት ሚኒስቴር እና በጅማ ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿ፡፡

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#DebarkUniversity ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም. የተመደባችሁ አዲስ የአንደኛ ዓመት እና የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም. በሪሚዲያል ፕሮግራም በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን የካቲት 20 እና 21/2016 ዓ.ም. እና በቅጣት ምዝገባ የካቲት 22/2016 ዓ.ም. መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። ወደ ተቋሙ…
በ2016 ዓ.ም ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት እና የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የካቲት 20 እና 21/2016 ዓ.ም መካሔዱ ይታወቃል፡፡

ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ሳትመዘገቡ የቀራችሁ ተማሪዎች እሰከ ነገ መጋቢት 6/2016 ዓ.ም ብቻ መመዝገብ እንደምትችሉ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/09/30 23:47:04
Back to Top
HTML Embed Code: