Telegram Web Link
#HawassaUniversity👏

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ግዜ በወሰዱት አገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መውጫና የሙያ ፈቃድ ፈተና 99% ተፈታኞች ፈተናውን አልፈው ለመመረቅ ብቁ መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

@tikvahuniversity
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን የሪሚዲያል ተማሪዎች በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የተመደቡለትን የሪሚዲያል ተማሪዎች ለመቀበል ከየካቲት 11-13/2016 ዓ.ም. ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ 

ተቋሙ ከዚህ ቀደም ከ2ኛ-4ኛ ዓመት ያሉ ነባር ተማሪዎችን እንዲሁም የ2016 ዓ.ም. አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በጥር ወር መጨረሻ ሳምንት ተቀብሎ ማስተማር ጀምሯል፡፡

@tikvahuniversity
መቱ ዩኒቨርሲቲ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዓ.ም. ተማሪዎች ያስመርቃል።

የተቋሙ ጤና ሳይንስ ተማሪዎች እንዲሁም በተለያዩ መርሐግብሮች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን የተከታተሉ ተማሪዎች በዕለቱ እንደሚመረቁ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#GAT_COMPLAINTS

የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር ከድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (GAT) ጋር በተያያዘ ከአባላቱ የቀረቡለትን ቅሬታዎች ለመንግሥት አቅርቧል።

ማኅበሩ ከመግቢያ ፈተናው ጋር የተያያዙ ቅሬታዎች በተለያዩ መንገዶች እንደደረሱት ገልጿል።

ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ማለትም ከጤና ሚኒስቴር እና ከትምህርት ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ጋር ምክክር ማድረጉን ማኅበሩ ጠቁሟል።

ሁለቱ ተቋማት ተነጋግረው የደረሱበትን ውጤት ለማኅበሩ እስኪያሳውቁ ፈተናውን ወስደው ቅሬታ ያቀረቡ አባላቱ በትዕግስት እንዲጠብቁ ማኅበሩ ጠይቋል።

@tikvahuniversity
#DireDawaUniversity

የመውጫ ፈተና ከወሰዱ 152 የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 150 ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ተፈታኞች በአምስት የሙያ መስኮች ለፈተና የተቀመጡ ሲሆን 98.70 በመቶ ተፈታኞች ፈተናውን አልፈው ለምርቃት ብቁ መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#WallagaUniversity

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት የመውጫ ፈተና የወሰዱ የጤና መስክ ተማሪዎቹ ሙሉ በሙሉ ማለፋቸውን ገልጿል።

ተፈታኞቹ በሕክምና፣ ፋርማሲ፣ ሜዲካል ላቦራቶሪ ቴክኖሎጂ፣ አጠቃላይ ነርሲንግ እና በሚድዋይፈሪ የሙያ መስኮች ለመውጫ ፈተና የተቀመጡ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው አረጋግጧል።

@tikvahuniversity
#WachemoUniversity

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሀገር አቀፍ የመውጫ እና የሙያ ፈቃድ ፈተና ከወሰዱ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች 99.6 በመቶዎቹ ፈተናውን ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

258 ተፈታኞቹ በስምንት የሙያ መስኮች ፈተና የወሰዱ ሲሆን 257ቱ የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው አረጋግጧል።

@tikvahuniversity
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የወሰዱ 160 የጤና ሳይንስ ተማሪዎቹ ሙሉ በሙሉ ፈተናውን ማለፋቸውን አሳውቋል።

160 ተፈታኞቹ በአምስት የትምህርት መስኮች የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን ሁሉም የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በሌላ በኩል በዩኒቨርሲቲው Dryland Agriculture ኮሌጅ በHuman Nutrition የትምህርት መስክ ለፈተና የተቀመጡ ስምንት ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ አለማምጣታቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#HaramayaUniversity

ሰሞኑን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 98.62 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገለፀ።

ፈተናውን ከወሰዱ 363 የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 358 ተማሪዎች ፈተናውን ማለፋቸው ተገልጿል።

በዘጠኝ የጤናና ህክምና ትምህርት ክፍሎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተናውን ወስደው፤ ከአካባቢ ጤና ሳይንስ ትምህርት ክፍል ሦስት እንዲሁም ከፋርማሲ ትምህርት ክፍል ሁለት ተማሪዎች ፈተናውን ሳያልፉ ቀርተዋል።

@tikvahuniversity
#ArsiUniversity

በአርሲ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ የህክምናና ጤና ሳይንስ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ፈተናውን ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በሕክምና፣ አንስቴዥያ፣ ፋርማሲ እና ሕብረተሰብ ጤና የትምህርት መስኮች ፈተናቸውን የወሰዱ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#MattuUniversity

ሰሞኑን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የመቱ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 96.38 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ፈተናውን ከወሰዱ 138 የመቱ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 133 ተማሪዎች ፈተናውን ማለፋቸው ተገልጿል።

በስድስት የጤናና ህክምና ትምህርት ክፍሎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተናውን ወስደው፤ ከሚድዋይፈሪ ትምህርት ክፍል ሁለት እንዲሁም ከሔልዝ ኢንፎርማቲክስ ትምህርት ክፍል ሦስት ተማሪዎች ፈተናውን ሳያልፉ ቀርተዋል።

@tikvahuniversity
#AssosaUniversity

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች 97.56 በመቶ ፈተናውን ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በሕብረተሰብ ጤና፣ ሚድዋይፈሪ እና ነርሲንግ የትምህርት መስኮች ፈተናቸውን ከወሰዱ 123 ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 120 ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

በነርሲንግ የትምህርት መስክ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ 34 ተማሪዎች መካከል ሦስቱ የማለፊያ ነጥብ አለማምጣታቸው ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#WolkiteUniversity

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ውስጥ 97.6 በመቶዎቹ ፈተናውን ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በሕክምና፣ ሜዲካል ላቦራቶሪ፣ ሚድዋይፈሪ፣ ነርሲንግ እና ሕብረተሰብ ጤና የትምህርት መስኮች ፈተናቸውን ከወሰዱ 253 ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 247 ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ ዕጩ ተመራቂዎች መካከል በሜዲካል ላቦራቶሪ የትምህርት መስክ ሦስት እንዲሁም በሕብረተሰብ ጤና የትምህርት መስክ ሦስት ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ አለማምጣታቸው ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#AmboUniversity

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ የህክምና ሳይንስ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ፈተናውን ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በሕብረተሰብ ጤና፣ አጠቃላይ ነርሲንግ እና በሜዲካል ላቦራቶሪ የትምህርት መስኮች ፈተናቸውን የወሰዱ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#BuleHoraUniversity

ባለፈው ሳምንት የተሰጠውን አገር አቀፍ የመውጫ እና የሙያ ፍቃድ ፈተና ከወሰዱ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 81.66 በመቶ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/10/01 13:33:57
Back to Top
HTML Embed Code: