Telegram Web Link
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን የሕክምና ዶክተሮች ቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዓ.ም. ያስመርቃል፡፡

የሕክምና ዶክተሮቹ የምረቃ ሥነ-ስርዓት በተቋሙ ዋና ግቢ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚከናወን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

@tikvahuniversity
በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የሦስተኛ ዓመት የሰርቬይንግ ቴክኖሎጂ ተማሪ የነበረው ሙሉቀን ከሮ ሰሞኑን ባጋጠመው የመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል፡፡

በተማሪ ሙሉቀን ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን የገለፀው ኢንስቲትዩቱ ፤ ለቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹ እና ዘመዶቹ መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

@tikvahuniversity
#SalaleUniversity

በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች በሁሉም የትምህርት መስኮች ሙሉ በሙሉ ፈተናውን ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#SamaraUniversity

በሠመራ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ የህክምናና ጤና ሳይንስ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ፈተናውን ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በአጠቃላይ ነርሲንግ፣ በሕብረተሰብ ጤና እና በሔልዝ ኢንፎርማቲክስ የትምህርት መስኮች ፈተናቸውን የወሰዱ 60 ተማሪዎች ሁሉም የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#WolaitaSodoUniversity

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የወሰዱ የጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ተማሪዎች እጅግ አመርቂ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በሜዲካል ላቦራቶሪ፣ ሕብረተሰብ ጤና፣ ሚድዋይፈሪ እና ነርሲንግ የትምህርት መስኮች የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በዩኒቨርሲቲው ለመውጫ ፈተና ከተቀመጡ የፋርማሲ ተማሪዎች 97 በመቶዎቹ ማለፋቸውም ተገልጿል።

@tikvahuniversity
በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የወሰዱ #የፔትሮሊየም_ኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና የወሰዱ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን ውጤት ይፋ አድርጓል።

በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለፈተና ከተቀመጡ 201 ተማሪዎች ውስጥ 200 ተማሪዎች (99.5 በመቶ) የማለፊያ ነጥብ ማስመዝገባቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በፋርማሲ ትምህርት ዘርፍ አንድ ተማሪ ብቻ የማለፊያ ነጥብ ሳታስመዘግብ መቅረቷ ተገልጿል።

እንዲሁም #በኪነ_ህንጻ ትምህርት ክፍል የመውጫ ፈተና ከተፈተኑ 34 ተማሪዎች ውስጥ 25 ተማሪዎች (73.53 በመቶ) የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች የ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ፈተናዎችን እንዳይሰጡ ተጥሎባቸው የቆየው ዕገዳ ተነሳላቸው፡፡

በከተማዋ በሚገኙ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች የ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ፈተናዎች እንዳይወስዱ በአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ዕግድ ተጥሎባቸው መቆየቱ ይታወቃል።

በእነዚህ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እያሉ፤ የሌላ ሀገር ስርዓተ ትምህርት ተምረው የሀገሪቱን ፈተና መስጠት አግባብነት እንደሌለውም ቢሮው መናገሩ ይታወሳል፡፡

ትምህርት ቤቶቹ የኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምህርትን ጎን ለጎን ለተማሪዎቻቸው ማስተማር መጀመራቸውን ሸገር ኤፍ.ኤም. ዘግቧል።

በመሆኑም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ጨምሮ ክልላዊ ፈተናዎችን እንዳይሰጡ ተጥሎባቸው የቆየው ዕገዳ እንደተነሳላቸው ተነግሯል፡፡

በአዲስ አበባ 19 ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ የሸገር ኤፍ.ኤም. ዘገባ ያሳያል፡፡

@tikvahuniversity
#DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ እንዲሁም የኪነ-ህንጻ ተማሪዎቹን ነገ የካቲት 16/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

በቅርቡ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ከወሰዱ 235 የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንዲሁም የኪነ-ህንጻ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች 225 ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው መግለፁ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#RayaUniversity

ራያ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች 96.47 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ፈተናውን ማለፋቸውን አሳውቋል።

በራያ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ለመስጠትን የሚያስችል የተሟላ የአይ.ሲ.ቲ. መሰረተ ልማት ባለመኖሩ ምክንያት ተማሪዎቹ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን እንዲወስዱ መደረጉ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን ጆርናል ይፋ አድርጓል።

'Salale Journal of Social and Indigenous Studies' (SJSIS) የተሰኘው የምርምር ውጤቱ፤ በዩኒቨርሲቲው የሶሻል ሳይንስ እና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ይፋ ሆኗል።

ጆርናሉ በተለያዩ የማኅበራዊ እና አገር-በቀል ጥናቶች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ጆርናሉ በጥልቅ የሚዘጋጁ የምርምር ውጤቶችን በኦንላይን እና በህትመት ተደራሽ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
ውጤትዎን ይመልከቱ!

በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ #የመንግሥት_ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል።

ውጤትዎን ለመመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ፦

https://result.ethernet.edu.et/


@tikvahuniversity
በርከት ያሉ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ዛሬ ያስመርቃሉ፡፡

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በመደበኛ እንዲሁም በተከታታይ የትምህርት መርሐግብር ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲዎቹ በቅርቡ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ያለፉ ተማሪዎችን ቁጥር ይፋ ሲያደርጉ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ፣ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ፣ መቱ ዩኒቨርሲቲ፣ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ እና ነገ ተማሪዎቻቸውን ከሚያስመርቁ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

@tikvahuniversity
#MattuUniversity

መቱ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 631 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ 479 በመጀመሪያ ዲግሪ እና 152 በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ትምህርታቸዉን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#ArbaMinchUniversity

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 70 የሕክምና ዶክተሮችን አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ምክንያቶች ሳይመረቁ የቆዩ ሦስት የሦስተኛ ዲግሪ፣ 237 የሁለተኛኛ ዲግሪ እና 509 የመጀመሪያ ዲግሪ በድምሩ 749 ተማሪዎችንም በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 33 ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ በጊዚያዊነት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁም ይገኙበታል፡፡

ዛሬ የተመረቁት 70 የሕክምና ዶክተሮች በቅርቡ የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ያለፉ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዳምጠው ዳርዛ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
2024/10/01 15:41:05
Back to Top
HTML Embed Code: