Telegram Web Link
የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት መለቀቅን ተከትሎ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ የድኅረ ምረቃ አመልካቾችን ለመቀበል ማስታወቂያ እያወጡ ይገኛሉ።

አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን የመግቢያ ፈተና (NGAT) ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

(የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ያወጧቸው የጥሪ ማስታወቂያዎች ከላይ ተያይዘዋል፡፡)

@tikvahuniversity
#AAU

የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የወሰዳቹ ተፈታኞች ውጤታችሁን ኦንላይን ማየት እንደምትችሁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ውጤት ለማየት 👇
https://portal.aau.edu.et/Web/ApplyForAdmission/TestingStatus

በተመሳሳይ በመንግስት ስፖንሰር ተደርጋችሁ የቅድመ ምረቃ ትምህርታችሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመከታተል ፈተና የወሰዳችሁ አመልካቾች፣ ውጤታችሁን https://portal.aau.edu.et/ ላይ ገብታችሁ Username (email) እና Password በማስገባት መመልከት ትችላላችሁ።

ዩኒቨርሲቲው ሦስተኛ ዙር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) በቅርቡ ይሰጣል ማለቱ አይዘነጋም።

@tikvahuniversity
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማሳለፍ የቻሉ ትምህርት ቤቶች ሰባት ብቻ ናቸው።

ከነዚህ ጥቂት ስኬታማ ትምህርት ቤቶች መካከል በጅግጅጋ ከተማ የሚገኘው The Spark Academy አንዱ ነው።

ትምህርት ቤቱ ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ያስፈተናቸውን 35 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማሳለፍ ችሏል። ሁለት ተማሪዎች ደግሞ ከ500 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

የተገኘው ውጤት የት/ቤቱ ማኅበረሰብ የተቀናጀ ጥረት ፍሬ መሆኑን የአካዳሚው ባለቤት ክፍለገብርኤል ወ/ተንሳይ ለ SRTV አማርኛ ተናግረዋል።

አካዳሚው በ2017 ዓ.ም 25 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንደሚያስፈትን የገለፁት ባለቤቱ፤ ሁሉንም ተማሪዎች ለማሳለፍና የሀገሪቱ ከፍተኛ ውጤት በትምህርት ቤቱ እንዲመዘገበ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ መደበኛ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች እንዲሁም ለነባር የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ጥሪ አለማድረጉን አረጋግጧል።

ወደፊት በ EBC እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ማኅበራዊ ሚዲያ ገፆች ጥሪ የሚደረግ መሆኑን የገለፀው ዩኒቨርሲቲው፤ እስከዛ ድረሰ ተማሪዎቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል።

@tikvahuniversity
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ ዙር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) የማመልከቻ ግዜን እስከ መስከረም 25/2017 ዓ.ም አራዝሟል፡፡

ለ GAT ፈተና ለማመልከት 👇
https://portal.aau.edu.et

ለማመልከት፦

https://Portal.aau.edu.et ይክፈቱ።
► Exam Application የሚለውን ይጫኑ።
► Test Taker Registration ቅፅን ይሙሉ።
► ፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶዎን ያስገቡ።
► Submit የሚለውን ይጫኑ።
► ሲስተሙ የሚሰጥዎትን ቁጥር ኮፒ ያድርጉ።
► የGAT ፈተና ክፍያ ብር 1000 በቴሌብር ይክፈሉ።
► የክፍያ ቲኬትዎን አውርደው ፕሪንት ይበሉ። የፈተና ቀን ወደመፈተኛ አዳራሽ ለመግባት ያስፈልግዎታል።

@tikvahuniversity
#EthiopianCivilServiceUniversity

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ነባር ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚካሔደው መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

የተከታታታይ (የማታ እና የቅዳሜና እሑድ) ትምህርት ፕሮግራሞች ነባር ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 22 እና 23/2017 ዓ.ም የሚካሔድ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሁሉም ፕሮግራሞች የዘገዩ ተማሪዎች ምዝገባ በቅጣት መስከረም 24/2017 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን፤ የሁሉም ትምህርት መርሐግብሮች ትምህርት መስከረም 24/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

@tikvahuniversity
#AAU #UAT #Cutoff_Points

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመንግስት ስፖንሰርነት እና በግል የቅድመ ምረቃ አመልካቾች ለ2017 ዓ.ም የ UAT መቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል።

በዚህም በመንግስት ስፖንሰር ለተደረጉ የቅድመ ምረቃ አመልካቾች ለ2017 ዓ.ም የ UAT መቁረጫ ነጥብ ለተፈጥሮ ሳይንስ 64 እና ለማኅበራዊ ሳይንስ 51 መሆኑ ታውቋል።

በግል ለመማር ያመለከቱ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ለ2017 ዓ.ም የ UAT መቁረጫ ነጥብ ከ54-79 (እንደየትምህርት ክፍሉ) መሆኑ ተገልጿል።

በግል ለመማር ያመለከቱ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ከፍተኛ የመቁረጫ ያስቀመጡ ት/ት ክፍሎች፦
► ህክምና ትምህርት ክፍል - 79
► ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ እና ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ - 78
► ኮምፒውተር ሳይንስ ት/ት ክፍል - 77
► የጥርስ ህክምና ትምህርት ክፍል - 75
► ህግ ትምህርት ክፍል - 70

(አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይፋ ያደረገው ለመንግስት እና የግል የቅድመ ምረቃ UAT አመልካቾች የመቁረጫ ነጥብ ከላይ ተያይዟል።)

በመንግስት ስፖንሰርነት እና በግል የቅድመ ምረቃ ትምህርታችሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመከታተል የመግቢያ ፈተና (UAT) ወስዳችሁ ያለፋችሁ አመልካቾች፣ የምደባ ውጤታችሁን http://admission.aau.edu.et/login ላይ ገብታችሁ Username (email) እና Password በማስገባት መመልከት ትችላላችሁ።

@tikvahuniversity
የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት መለቀቅን ተከትሎ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ የድኅረ ምረቃ አመልካቾችን ለመቀበል ማስታወቂያ እያወጡ ይገኛሉ።

አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን የመግቢያ ፈተና (NGAT) ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

(የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ያወጧቸው የጥሪ ማስታወቂያዎች ከላይ ተያይዘዋል፡፡)

@tikvahuniversity
2024/09/30 19:26:26
Back to Top
HTML Embed Code: