Telegram Web Link
በአማራ ክልል የ2016 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፍ ሆኗል።

በክልሉ የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከወሰዱ 132,225 ተማሪዎች መካከል 97,859 (74.1%) ተማሪዎች የማለፊያ 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት እንዳስመዝገቡ የክልሉ ትሞህርት ቢሮ አሳውቋል።

በተመሳሳይ የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከወሰዱ 150,928 ተማሪዎች መካከል 84,522 (56%) ተማሪዎች የማለፊያ 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገልጿል።

በክልሉ 82 አይነ ስውር የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና ተቀምጠው 80 ተማሪዎች (95.18%) የማለፊያ 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን፤ ፈተናውን ከወሰዱ 148 የ8ኛ ክፍል አይነስውር ተማሪዎች  መካከል 105 (70.94%) ተማሪዎች 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

ውጤት ለማየት 👉 ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች፦
https://amhara.ministry.et/#/result

ውጤት ለማየት 👉 ለ6ኛ ክፍል ተፈታኞች፦
https://amhara6.ministry.et/#/result

በተጨማሪ በቴሌግራም ቦት ለማየት፦
@emacs_ministry_result_qmt_bot  

ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ለማቅረብ፦

👉 ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች፦
https://amhara.ministry.et/#/complaint

👉 ለ6ኛ ክፍል ተፈታኞች፦
https://amhara6.ministry.et/#/complaint

@tikvahuniversity
#Infinix_Note40_Pro_Plus

ኢንፊኒክስ ከታዋቂው ዓለም አቀፍ የስፒከር አምራች ኩባንያ ጄቢኤል ጋር በመተባበር አዲሱን ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልክ ከእጅግ አስገራሚ የድምፅ ጥራት ጋር ይዞ መጥቷል፡፡ ሙዚቃ ለማዳምጥ፣ ጌም ለመጫወት እንዲሁም ማኅበራዊ ሚዲያ ለመመልከት በኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ ልዩ ነው፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
Tikvah-University
Photo
በአማራ ክልል የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ትናንት ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠውን ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል፥ በደሴ ከተማ ሁለት ተማሪዎች ከፍተኛውን ውጤት አስመዝግበዋል።

በደሴ ከተማ በግል ትምህርት ቤቶች ተማሪ የሆኑት
ሳሚያ የሱፍ እና ሲትረላህ አሊ የአቬሬጅ እና ፐርሰንታል 100 በማምጣት በክልሉ ከፍተኛውን ውጤት አሳክተዋል።

ተማሪዎቹ በደሴ ከተማ በሚገኙት ካቶሊክ ትምህርት ቤት እና አልፍ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
በትምህርት ዘርፍ የሚስተዋሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ጥናት በቅርቡ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2ኛ ዙር የ'ትምህርት ለትውልድ' ክልል አቀፍ የንቅናቄ መድረክ በወራቤ ከተማ ተካሒዷል፡፡

በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) "በትምህርት ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ጥናት በሚኒስቴሩ እየተከናወነ እንደሚገኝና በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ትግበራ እንደሚገባ" ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕብረተሰብ ጤና ትምህርትን በሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም መስጠት ሊጀምሩ ነው።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ትምህርቱን መስጠት ለመጀመር የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን በጤና ሚኒስቴር የሰው ሃብት ልማትና ማሻሻያ መሪ ስራ አስፈፃሚ አሰግድ ሳሙኤል ለኢዜአ ተናግረዋል።

ጤና ሚኒስቴር በጤናው ዘርፍ በተለያዩ መስኮች የሙያተኞችን ቁጥር ለማሳደግ እየሠራ እንደሚገኝ ኃላፊው ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ በፒ.ኤች.ዲ ፕሮግራም የሕብረተሰብ ጤና ተማሪዎችን በዚህ ዓመት መቀበል እንደሚጀምሩ ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል 'የሰውሰራሽ የአካል ድጋፍ ባለሙያዎች ትምህርት' በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ ለመጀመር ዝግጅት መጠናቀቁን አስረድተዋል። #ኢዜአ

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት በምግብ አብሳይነት እና በመሳሰሉ ሙያዎች መሰማራት ለምትፈልጉ ዜጎች የቀረበ የስልጠና ጥሪ

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (E-LMIS) ተመዝግባችሁ በውጪ ሀገር የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን የምትፈልጉ በኢትዮጵያ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት (TTI) ተመዝግባችሁ ስልጠናውን መጀመር የምትችሉ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡

አድራሻ፦ ሜክሲኮ ቡናና ሻይ እንዲሁም ገነት ሆቴል
ፖ.ሳ.ቁ.፦ 4350 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ ቁ.፦ 0115308121 / 0115308126 / 0115519418
ዌብሳይት፦ tti.edu.et

@tikvahuniversity
#SPHMMC

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በ13 የትምህርት መስኮች የማስተርስ ፕሮግራም አመልካቾችን ለመቀበል ላወጣው ጥሪ የአመልካቾች የምዝገባ ጊዜን እስከ ነሐሴ 24/2016 ዓ.ም አራዝሟል፡፡

በሕክምና ትምህርት ቤት
- MS in Respiratory Therapy
- MS in Medical Microbiology
- MS in Medical Radiologic Technology

በማኅበረሰብ ጤና ትምህርት ቤት
- MPH in General Public Health
- MPH in Nutrition
- MPH in Epidemiology
- MPH in Health Communication and Promotion

በነርሲንግ ትምህርት ቤት
- MS in Critical Care Nursing
- MS in Cardiovascular Nursing
- MS in Neonatal Nursing
- MS in Clinical Oncology Nursing
- MS in Paramedics Science
- MS in Cardiothoracic Nursing

@tikvahuniversity
ጉርሻ መለያው የሆነው M-PESA ዕለታዊ ጥቅል ስንገዛ በቃችሁ አይለንም ፤ ከ 400 ሜጋባይት አልፎ ተጨማሪ 200 ሜጋባይት እያጎረሰ ያንበሸብሸናል!!

የ M-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👇
https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ጥቆማ

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የተለያዩ የአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎች አዘጋጅቷል፡፡

ስልጠናዎቹ ከጠዋት እስከ ማታ በአራት ፈረቃዎች እንዲሁም የስልጠና ፈላጊዎችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በቅዳሜ እና እሁድ መርሐግብር ይሰጣሉ፡፡

ስልጠናዎቹ እንደየመስካቸው እሰከ ሦስት ወር ቆይታ ይኖራቸዋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦ በገነት ካምፓስ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው 👉 ነሐሴ 20/2016 ዓ.ም

የስልጠና ርዕሶች፦

► Tourism and Hospitality Marketing
► Hospitality leadership Management
► Tour Operation Service
► Culinary Art
► Barista Service
► Bartender Service
► Food Safety Service
► Butchery Service
► Wellness and Spa Service
► Housekeeping and Laundry Service
► Pastry and Bakery
► Food Beverage Service
► Fast Food Preparation
► Food and Beverage Control
► Front Office Service

(የኢንስቲትዩቱ ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
#Infinix_Note40_Pro_Plus

ኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G የ100 ዋት ፈጣን የገመድ ቻርጅ ያለው ሲሆን፤ የገመድ ቻርጀር ባይኖርዎትም አያሳስብም! ምክንያቱስ ካሉ ባለ 20 ዋት ገመድ አልባ የቻርጂንግ ቴክኖሎጂን ይዞ ብቅ ብሏል!!

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚዲያ እና ቴክኖሎጂ ማዕከል አስመርቋል።

ማዕከሉ ኮምፒውተሮች፣ የስቱዲዮ ግብዓቶች እና የማሳያ ቁሳቁሶች የተሟሉለት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ማዕከሉ በተለይ የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርትን በተሻለ መንገድ ለማስተማር የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ማዕከሉን ለማደራጀት የተደረገው ወጪ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሰጠው የ500,000 ዶላር ድጋፍ ውስጥ የመጨረሻው መሆኑ ተሰምቷል።

ክፍሎቹ ተማሪዎች ተግባር ተኮር ትምህርት እንዲያገኙና በተለይም ሐሰተኛ መረጃን ለማጣራት የሚያስችሉ መሆናቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርት ቤት ዲን አብዱልአዚዝ ዲኖ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ ለ2017 የትምህርት ዘመን ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዕቅድ ይዟል፡፡

በክልሉ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምዝገባ ነሐሴ 20/2016 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡

ቢሮው በ2017 የትምህርት ዘመን በአንደኛ ደረጃ፣ በመካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በየነ በራሳ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

የተማሪዎች ምዝገባው በክልሉ በሚገኙ አራት ዞኖች እና በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንደሚካሔድ ኃላፊው ገልፀዋል፡፡ በርካታ የግል ትምህርት ቤቶች የተማሪ ምዝገባ አካሒደው ወደማጠናቀቁ መቃረባቸውን ኃላፊው ጠቅሰዋል፡፡

ከመፅሐፍ አቅርቦት ጋር በተያያዘ በ2017 የትምህርት ዘመን አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡

@tikvahuniversity
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ላወጣው የግብርና ቆጠራ መረጃ ሰብሳቢ ባለሙያነት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባለማው E-LMIS ፖርታል በኩል ተመዝግባችሁና መስፈርቱን አሟልታችሁ ማለፋችሁ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት የተላከላችሁ የሥራ ዕድል ፈጠራ ጽ/ቤት ድረስ በመሔድ የቅጥር ፎርማሊቲ እንድታሟሉ አገልግሎቱ አሳውቋል፡፡

የተቀመጡ መስፈርቶችን አሟልታችሁ የተመለመላችሁ ወደ ስልጠና ማዕከል በምትሔዱበት ጊዜ ልታሟሏቸው የሚገቡ፦

► የተመረጣችሁበት ቀበሌ በሚገኝበት ወረዳ የሥራ ዕድል ፈጠራ ጽ/ቤት በመሔድ የቅጥር ፎርም ሞልታችሁ ማጠናቀቅ ይጠበቅባችኋል።

► የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ኮፒ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡
► አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ መያዝ ይኖርባችኋል።
► ማንኛውም ክፍያ የሚፈፀምላችሁ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት እና በምትይዙት ስልክ ቁጥር በተከፈተ የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ስትችሉ ብቻ መሆኑን እንድታውቁ፡፡
► የተመደባችሁበትን የስልጠና ማዕከል ለማወቅ፦
http://www.statsethiopia.gov.et/wp-content/uploads/2024/08/list-of-training-centers.pdf
►ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት፦ ነሐሴ 16 እስከ 17/2016 ዓ.ም
►ሪፖርት ማድረጊያ ቦታ፦ በየተመደባችሁበት ዩኒቨርሲቲ (ካምፓስ)

@tikvahuniversity
ከሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ ልዩ የአቅም ማሻሻያ ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን ስልጠናቸውን በዛሬው ዕለት አጠናቀዋል፡፡

መምህራኑ በአምስት የትምህርት አይነቶች (እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ባይሎጂ፣ ኬሚስትሪ እና ፊዝክስ) የአቅም ማሻሻያ ስልጠና ወስደዋል።

በተመረጡ 28 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና መጠናቀቅን ተከትሎ፣ መምህራኑ ምን ያህል ስልጠናውን እንደተከታተሉ የሚለካ ፈተና በዛሬው ዕለት እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡

60 ሺህ የሚሆኑ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ከሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ የተሰጠውን ልዩ የአቅም ማሻሻያ ስልጠና እንደወሰዱ ይገመታል፡፡

ምስል፦ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡

በክልሉ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከወሰዱ 129,384 ተማሪዎች መካከል 55,076 ተማሪዎች (42.57 በመቶ) የማለፊያ ነጥብ ማስመዝገባቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡

ተፈታኝ ተማሪዎቹ በመደበኛ፣ በግል፣ በርቀት እና በማታ መርሐግብር ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ለመደበኛ ተፈታኞች 50 በመቶና ከዚያ በላይ፣ ለልዩ ፍላጎት ተፈታኞች 45 በመቶና ከዚያ በላይ እንዲሁም ለአርብቶ አደር አካባቢ ተፈታኞች 48 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ወደ ቀጣይ ክፍል ለመዘዋወር የማለፊያ ነጥብ መሆኑን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

1,787 ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ክልላዊ የ8ኛ ክፍል ፈተና ያስፈተኑ ሲሆን፤ 165 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ኃላፊው አብራርተዋል።

ተማሪዎች ከዛሬ ነሐሴ 15/2016 ዓ.ም ጀምሮ በ https://se.ministry.et/#/result ወይም @emacs_ministry_result_qmt_bot ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ ተብሏል፡፡ #SRTA

@tikvahuniversity
2024/10/03 04:39:31
Back to Top
HTML Embed Code: