Telegram Web Link
300 ባለ ልዩ ተሰጥዖ አዳጊ ወጣቶች የሳይበር ታለንት ስልጠና መውሰድ ጀመሩ፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር የሚሰጠው 3ኛ ዙር የሳይበር ደኅንነት የክረምት ስልጠና ዛሬ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሯል።

በስልጠናው አዳጊ ወጣቶቹ ያላቸውን ተሰጥዖ የሚያጎለብቱበትና ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር እንዲቀይሩ የሚያስችላቸው እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ከመላ አገሪቱ የተውጣጡት አዳጊዎቹ ከሳይበር ስልጠናው በተጨማሪ የአገር ፍቅር ስሜት እንዲኖራቸው የሕይወት ክህሎት እንዲያገኙ ይደረጋል ተብሏል።

@tikvahuniversity
#Infinix_Note40_Pro_Plus

አዲሱ የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ለዕይታ እና ለአያያዝ ያማረ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ጥራት ያለው 108 ሜጋ ፒክስል ካሜራው ቁልጭ ያለ ፎቶን ያለምንም እንከንም ማንሳት ያስችላል፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
#WoldiaUniversity

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ መርሐግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታችሁን በተቋሙ ስትከታተሉ የነበራችሁ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና የእንስሳት ህክምና (DVM) ነባር ተማሪዎች ነሐሴ 20 እና 21/2016 ዓ.ም ሪፖርት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አድርጓል፡፡

የምዝገባ ቦታ፡-
► የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ዋናው ግቢ
► የእንስሳት ህክምና (DVM) ተማሪዎች መርሳ ካምፓስ፡፡

ትምህርት ነሐሴ 22/2016 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
#TVTI

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የስቴም ስልጠና ማዕከል ለመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞቹ የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

የማዕከሉ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኝ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ሂሳብ ክህሎታቸውን ለማጎልበት እንዲሁም የፈጣራ ሃሳባቸውን ለማሳደግ የሚያግዙ ስልጠናዎች እየወሰዱ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ሠልጣኝ ተማሪዎቹ በራሳቸው ድረ-ገፅ እያለሙ እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡

@tikvahuniversity
ከ95 ሺህ በላይ ወጣቶች የአምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ ስልጠናን ባሉበት ተመዝግበው በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።

https://www.ethiocoders.et/ ላይ በመመዝገብ የነፃ ስልጠናዎቹ ተጠቃሚ ይሁኑ።

ስልጠናው ለስድስት ሳምንታት የሚሰጥ ሲሆን፤ ስልጠናው የሚያጠናቅቅ ወጣት ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው ሰርቲፊኬት የሚያገኝ ይሆናል፡፡

ይመዝገቡ 👇
https://www.ethiocoders.et/

@tikvahuniversity
በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲሰጥ የነበረው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና ትናንትና ተጠናቋል፡፡

የስልጠናውን መጠናቀቅ ተከትሎ፥ መምህራኑ በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ለመመዘን የሚያስችል በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ የኦንላይን ፈተና ለመምህራኑ ተሰጥቷል፡፡

መምህራኑ ለ20 ቀናት (120 ሰዓታት) በ28 ዩኒቨርሲዎች ውስጥ ስልጠናቸውን የተከታተሉ ሲሆን፤ በቆይቸውም የሚያስተምሩትን የትምህርት አይነት እንዲሁም የማስተማሪያ ስነ-ዘዴ፣ የአዕምሮ ጤና፣ የስነ-ልቦና ድጋፍ እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ኮርሶች ስልጠና መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡

ምስል፦ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በከተማዋ በሚገኙ 14 የፖሊ-ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ያሰለጠናቸውን 5,180 ተማሪዎች አስመርቋል።

ሠልጣኞቹ በስድስት ፖሊ-ቴክኒክ እና በስምንት ኮሌጆች በ22 የሙያ መስኮች ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ተመራቂዎቹ ከደረጃ ሁለት እስከ አምስት፤ 30 በመቶ የንድፈ ሀሳብ እና 70 በመቶ የተግባር ስልጠና የወሰዱና በኮሌጅ ደረጃ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ያለፉ ናቸው ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
ነጻ የትምህርት ዕድል ጥቆማ

በሰዎች ለሰዎች ድርጅት የአግሮ ቴክኒክና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ለ 2017 የትምህርት ዘመን የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ በቴክኖሎጂ መስክ በዲግሪ መርሐግብር ማስተማር ይፈልጋል።

በ2013፣ 2014፣ 2015 እና 2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጣችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እንዲሁም የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጣችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን እንደምትችሉ ኮሌጁ ገልጿል።

የምዝገባ አማራጮች፦

► በአካል በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ሐረር፣ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ኮፒ ከአንድ ጉርድ ፎቶግራፍ ጋር በመያዝ ዘወትር በሥራ ሰዓት መመዝገብ ትችላችሁ።

የጉግል የምዝገባ ቅፅ፦
https://forms.gle/DatXbqGREbNAh8ncA
በቴሌግራም ቦት፦
https://www.tg-me.com/MFMATTC_bot
በድረ-ገፅ፦ http://www.mfmattc.edu.et

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት በተለያዩ #የነርሲንግ_ሙያ መስኮች ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት lmis.gov.et በመመዝገብ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በሚደረግ የምልመላ ሒደት የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን lmis.gov.et ላይ መመዝገብ እና አቅሪያቢያችሁ በሚገኝ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ በመገኘት የባዮሜትሪክስ መረጃ መስጠትና የሠራተኛነት መለያ ቁጥር ማግኘት ያስፈልጋል፡፡

ለአገልግሎቱ ምንም አይነት ክፍያ የማይጠየቅ መሆኑን አውቃችሁ ከአጭበርባሪዎች ራሳችሁን እንድትጠብቁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

@tikvahuniversity
49 ሺህ በላይ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የተሳተፉበት ልዩ አቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቋል፡፡

ለተከታታይ 24 ቀናት በተሰጠው ስልጠና፣ 49,505 መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች፣ 2,892 አሰልጣኞች እንዲሁም 224 ዋና አሰልጣኞች መሳተፋቸውን በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

መምህራኑ በሚያስተምሩበት የትምህርት አይነት፣ በማስተማር ስነ-ዘዴ እንዲሁም በዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት ላይ ብቃታቸውን ለማሻሻል የሚያስችል ስልጠና መውሰዳቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ሁሉም ሰልጣኝ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀን የብቃት ምዘና ፈተና በኦንላይን የወሰዱ ሲሆን፤ የምዘናው ውጤት በቀጣይ እንደሚገለፅ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ጠቁመዋል፡፡

ስልጠናው በቀጣይ ዓመት እንደሚሰጥም የገለፁት ኃላፊው፤ የመጀመሪያ ደረጃ መምህራን እና በዚህ ክረምት ስልጠና ያልተሳተፉ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን በቀጣዩ ዓመት ስልጠና ይሳተፋሉ ብለዋል፡፡ #MoE

@tikvahuniversity
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዳግም ምዝገባ አስፈላጊ መረጃና ሰነዶችና የሚያቀርቡበት የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል፡፡

362 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር የተካተተበት የሰነድ ማቅረቢያ ቅፁ፣ ጊዚያዊና ለአስተያየት የቀረበ መሆኑን ባለሥልጣኑ ጠቁሟል፡፡

በዚህም ተቋማቱ በጊዜ ሰሌዳ ቅፁ ላይ ያላቸውን አስተያየት እስከ ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም ድረስ መስጠት እንደሚችሉና ከምትሰጡት አስተያየት ጋር የተቋማችሁን ሙሉ ስም በመግለጽ በ [email protected] ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን ባለሥልጣኑ አሳስቧል፡፡

ለአስተያየት የቀረበውን ጊዚያዊ የጊዜ ሰሌዳ ቅፅ ለማግኘት 👇
https://bit.ly/4do4ZUJ

@tikvahuniversity
#UniversityOfGondar

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአመራር የትምህርት ፕሮግራም የድኅረ ምረቃ ዲፕሎማ መስጠት ጀመረ፡፡

ዩኒቨርሲቲው 25 ሰልጣኞችን በመቀበል ነሐሴ 12/2016 ዓ.ም ፕሮግራሙን በይፋ አስጀምሯል፡፡

በአመራር የትምህርት ፕሮግራም የድኅረ ምረቃ ዲፕሎማ (Post Graduate Diploma in Leadership) ለማስጀመር፣ የዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ካሪክለም በመቅረፅ ላለፉት ሁለት ዓመታት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

ፕሮግራሙ በሥራ ላይ ያሉ አመራሮችን አቅም ለማሳደግና አዳዲስ አመራሮችን ለማፍራት ታስቦ የተቀረፀ መሆኑን የኮሌጁ ዲን ደምስ አላምረው (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
🎉  ዘመናዊዎቹን ሳምሰንግ ጋላክሲ A15 እና A34 ስልኮችን ከሁሉም ሳፋሪኮም ሱቆች በማይታመን ዋጋ እንግዛ! ከሳፋሪኮም ጋር በአብሮነት ወደፊት!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC ላይ ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
#SamsungGalaxyA15
#SamsungGalaxyA53
#ጥቆማ

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተቀናጀ ክሊኒካልና የማኅበረሰብ አዕምሮ ጤና የማስተርስ ትምህርት ፕሮግራም መስጠት ጀምሯል።

(MS in Integrated Clinical and Community Mental Health)

ፕሮግራሙ በተለይ በክሊኒካል እና በማኅበረሰብ አዕምሮ ጤና ስፔሻላይዝ ለማድረግ ለሚፈልጉ የጤና ባለሙያዎች የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

የቅበላ መስፈርቶች፦

► የመጀመሪያ ዲግሪ በጤና መስኮች (ሳይካትሪ፣ ህክምና፣ ኅብረተሰብ ጤና፣ ነርሲንግ፣ ሚድዋይፈሪ፣ ... )
► እድሚያቸው ከ40 ዓመት በታች የሆኑ
► የመግቢያ ፈተና (የፅሁፍ እና የቃል) ማለፍ ይኖርባችኋል።

የፕሮግራሙ ቆይታ፦
ለሁለት ዓመት (44 ክሬዲት ሰዓት)

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

ካምፓሱ በአንድ የፒ.ኤች.ዲ እና በ12 የማስተርስ ፕሮግራሞች የድኅረ ምረቃ ትምህርት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አሳውቋል።

አመልካቾች ከነሐሴ 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ሬጅስትራር ጽ/ቤት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ካምፓሱ ገልጿል።

(ለማመልከት ልታሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶች እና የድኅረ ምረቃ ትምህርት የሚሰጥባቸው መስኮች ከላይ ተያይዘዋል።)

@tikvahuniversity
2024/10/03 06:18:37
Back to Top
HTML Embed Code: