Telegram Web Link
#ጥቆማ

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቅርንጫፉ የማስተርስ ዲግሪ ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ የሚሰጡ የማስተርስ ዲግሪ ፕሮግራሞች፦
1. MSc in Fashion Design
2. MSc in Textile Manufacturing
3. MSc in Fashion Technology
4. MSc in Fiber Science and Technology
5. MSc in Textile Chemistry
6. MSc in Leather Products Design and Engineering

በመሆኑም በተከታታይ እና በማታ መርሐግብር መማር የምትፈልጉ እስከ ነሐሴ 28/2016 ዓ.ም ድረስ መማር የምትፈልጓቸውን የትምህርት ዘርፎች በመለየት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ኢንስቲትዩቱ አሳውቋል፡፡

አመልካቾች የተሞላና የተፈረመ የማመልከቻ ቅፅ፣ ከመመዝገቢያ ክፍያ 200 ብር የባንክ ደረሰኝ ጋር በማያያዝ በኢሜይል አድራሻ [email protected] መላክ ትችላላችሁ፡፡

የማመልከቻ ቅፅ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ድረ-ገፅ https://bdu.edu.et/registrar/ ላይ ማግኘት የሚቻል ሲሆን፤ ትምህርት የሚጀመርበት ጊዜ ወደፊት በማስታወቂያ ይገለፃል ተብሏል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፦ 0920771481

(የተቋሙ ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
Forwarded from TEST CHANNEL BIRUKSA
#Infinix_Note40_Pro_Plus

የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G አጅግ ፈጣን እና በአለማችን የመጨረሻው የኔትወርክ ቴክኖሎጂ የሆነውን የ5G ኔትወርክ ማስጠቀም የሚያስችል ነው፡፡ ከፍተኛ አቅም የሚፈልጉ ሥራዎችን በስልካቸው በሚያከናውኑ ሰዎች ተመራጭ የሆነው የ Mediatek Dimesnty 7020 ፕሮሰሰር የተገጠመለት ፈጣን ስልክ ነው፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ እና እንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል በጋራ የአንጎል እና ህብለ ሰረሰር ቀዶ ህክምና (Neuro Surgery) አገልግሎት ለመሰጠት ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል የማይሰጡ አግልግሎቶችን ከሆስፒታሉ አስተዳደር እና ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመቀናጀት ደረጃ በደረጃ የማስጀመር እና የሆስፒታሉን ደረጃ የማሻሻል ስራ እንደሚሰራ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ሆስፒታሉ የአንጎልና ህብለ ሰረሰር ህክምና፣ የአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ፣ የአዋቂዎች እና ህፃናት አንጎል እጢ ህክምና፣ የአንጎል ውስጥ ፈሳሽ ግፊት መጨመር፣ የአንጎል ውስጥ ድንገተኛ የደም ፍሠት መቋረጥ ወይም መፍሠስ (Stroke) እና ተያያዥ ህክምናዎች መሰጠት እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በቅርቡ የተመረቀው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እየሰጠ ካለው የሕክምና አገልግሎቶች በተጨማሪ ከዛሬ ነሐሴ 10/2016 ዓ.ም ጀምሮ የጥርስ፣ የኤም.አር.አይ. እና የስነ-ደዌ/Pathology/ የሕክምናና ምርመራ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት እየተሰጠ ያለውን የመምህራን ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተመልክተዋል።

ከሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ በ28 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው የመምህራን ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና እስከ ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

ምስል፦ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ፣ በሦስት የዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲዎች እና በትምህርት ሚኒስቴር ትብብር ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲሰጥ የቆየው የአመራር እና አስተዳደር (LMG) ፕሮግራም የመዝጊያ ስነ-ስርዓት በአዲስ አበባ ተካሒዷል፡፡

ከ37 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ 50 የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች በፕሮግራሙ የተሳተፉ ሲሆን፤ የከፍተኛ ትምህርት የአመራር እና የአስተዳደር ክህሎታቸውን ለማጎልበት የሚያስችል ስልጠና ተከታትለዋል፡፡ ተሳታፊዎቹ በዩናይትድ ስቴትስ የሥራ ጉብኝትም አድርገዋል፡፡

ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ፣ በቴክሳስ ቴክ ዩኒቨርሲቲ፣ በኦሀዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ፣ በኦክላሆማ ስቴት ዩኒቨርስቲ እና በትምህርት ሚኒስቴር ትብብር ላለፉት ሁለት ዓመታት ተፈጻሚ ሆኗል፡፡

@tikvahuniversity
በሲዳማ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠውን የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ75 በመቶ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ማለፋቸው ተገለፀ፡፡ 

996 ትምህርት ቤቶች ለ48,763 ተማሪዎች የ6ኛ ክፍል ፈተናን የሰጡ ሲሆን፤ 152 ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ሙሉ በሙሉ ማሳለፋቸውን የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በየነ በራሳ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል 69,880 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና የወሰዱ ሲሆን፤ 37,845 ወይም 54.1 በመቶ ተማሪዎች 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

792 ትምህርት ቤቶች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ያስፈተኑ ሲሆን 44 ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ ማሳለፉፍ መቻላቸው ተገልጿል። 23 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አለመቻላቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል።

አንድ ተማሪ ብቻ ያሳለፉ እና ምንም ተማሪ ባላሳለፉ ትምህርት ቤቶች ላይ ችግሮችን የመለየትና የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
#Sidama የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ የስምንተኛና ስድስተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መለቀቁን በቲክቫህ ገልጿል።

የቢሮዉ ኮሚዩኒኬሽን ሀላፊ ወይዘሮ ጸጋ ሀጎስ ለቲክቫህ በሰጡት ቃል ተማሪዎች ዉጤታቸዉን በሊንክ ማየት እንደሚችሉ ገልጸዉልናል።

በዚህም መሰረት
ለስድስተኛ ክፍለ
https://sidama6.ministry.et/#/

ለስምንተኛ ክፍል
https://sidama.ministry.et/#/

@tikvahuniversity
#Infinix_Note40_Pro_Plus

ኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ከዘመኑ ጋር አብሮ የዘመነ ዓለም የደረሰባቸውን ቴክኖሎጂዎች በአንድ ላይ ያጣማረ ለእርሶ የሚገባ ዘመናዊ ስልክ!!

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
የጅማ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር ተመስርቷል።

በምስረታ ጉባኤው ላይ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ የቀድሞ ተማሪዎች በአካልና በኦንላይን ተሳትፈዋል፡፡

በማኅበሩ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤ የማኅበሩ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ፣ የውስጥ ቁጥጥር ኦዲተር እና ሌሎች የቦርድ አባላት ምርጫ ተካሒዷል።

@tikvahuniversity
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ

ለስፖርት ፀሀፊነት የወጣ የስራ ማስታወቂያ (ቲክቫህ ስፖርት)

የቅጥር ሁኔታ፦ ቋሚ

በዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮች ላይ ዜና መስራት የሚፈልግ/የምትፈልግ፣

- ወቅታዊ ዜናዎችን ተከታትሎ በሰዓት በፅሁፍ ማቅረብ የሚችል፣

- ሥራውን ካለበት ሆኖ ማከናወን የሚችል/የምትችል፣

- እንደስፈላጊነቱ በተለያዩ መርሐግብሮች ላይ ሪፖርት ማዘጋጀት የሚችል/የምትችል፣

- አማርኛ ሥርዓቱን ጠብቆ መጻፍ የሚችል። እንዲሁም ዓለም አቀፍ ዜናዎችን ወደ አማርኛ ምልስ ትርጉም ጠንቅቆ ማዘጋጀት የሚችል/የሞትችል፣

- ለሥራው የሚሆን ጥሩ ስልክ ያለው፤ የኢንተርኔት አገልግሎት በአስተማማኝ ሁኔታ ማግኘት የሚችል/የምትችል፣

- ዜናዎችን ተከታትሎ ፈጣን መረጃ ለመስጠት ንቁ (Active) የሆነ/የሆነች፣

- ለሚሰራው ሥራ ታማኝ፣ ፈጣን፣ ስልቹ ያልሆነ እንዲሁም የሚሰጡ አስተያየቶችን ተቀብሎ ለማስተካከል ዝግጁ የሆነ/የሆነች፣

- ለረጅም ጊዜ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች።

ደምወዝ፦ በድርጅቱ ስኬል መሠረት

የሥራ ቦታ፦ አዲስ አበባ፣ ሃያ ሁለት

የሥራ ልምድ፦ ስለ ሁሉም አይነት ስፖርት በቂ ዕውቀት ያለው/ያላትና ወቅታዊ ስፖርታዊ መረጃዎችን የሚከታተል/የምትከታተል።

🔴 አመልካቾች ለማመልከት ማስረጃዎችን ሲልኩ ማሳያ የሚሆን ዜናዎችን ቢልኩ ይመረጣል።

🔴 ማመልከቻችሁን ለመላክ፦ @Tikvahsportcv
#Infinix_Note40_Pro_Plus

አዲሱ የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ከፍተኛ ጥራት ያለው 108 ሜጋ ፒክስል ካሜራው በተለያዩ አማራጮች ቁልጭ ያለ ፎቶን ይሰጦታል በተጨማሪም የሱፐር ዙም ቴክኖሎጂው ከርቀት ሆነው ጥራት ያለው ምስልን ማንሳት ያስችላል፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ክልላዊ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

በ2016 ዓ.ም በክልሉ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 42.93 ከመቶ ተማሪዎች የማለፊያውን 50 ከመቶ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

በክልሉ በ2016 ዓ.ም 45,086 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ሲሆን፤ 19,355 ተማሪዎች (42.93 በመቶ) የማለፊያ 50 ከመቶ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የቢሮው ኃላፊ አልማው ዘውዴ ተናግረዋል።

ውጤት ለማየት፦ www.sw.ministry

ተማሪዎች ከላይ የተገለፀው አድራሻ ላይ በመግባት View Result የሚለውን በመጫን፣ የመመዝገቢያ ቁጥራችሁንና ስማችሁን በማስገባት ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ። #SouthWestCommunications

@tikvahuniversity
2024/10/03 02:39:38
Back to Top
HTML Embed Code: