Telegram Web Link
ቅናሽ ተገኝቶማ አንምረውም ፤ ዕለታዊውን M-PESA ኢንተርኔት ፓኬጃችንን ገዝተን እስከ 50% ቅናሹን ማጣጣም ነው እንጂ!

የ M-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉 https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether
#ጥቆማ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ #ነርሲንግና_ሚድዋይፈሪ ትምህርት ቤት በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአራት የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደሚፈልግ አሳውቋል፡፡

የማስተርስ ፕሮግራሞች፦
- በ Adult Health Nursing
- በ Surgical Nursing
- በ Pediatrics and Child Health Nursing
- በ Clinical Midwifery

በተመሳሳይ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ #የዓሳ_ሃብትና_ውሃ_ሳይንስ ትምህርት ክፍል በአራት የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደሚፈልግ አሳውቋል፡፡

የማስተርስ ፕሮግራሞች፦
- MSc in Fisheries and Aquaculture
- MSc in Aquatic and Wetland Ecosystem Management

የፒ.ኤች.ዲ. ፕሮግራሞች፦
- PhD in Fisheries and Aquaculture
- PhD in Aquatic and Wetland Ecosystem Management

በፕሮግራሞቹ ለማመልከት ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) ማለፍ ያስፈልጋል፡፡ (የተቋማቱ ሙሉ መልዕክት ለከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የክረምት አቅም ግንባታ ስልጠናቸውን አጠናቀዋል፡፡

የትምህርት ቤት አመራሮቹ ከሐምሌ 23/2016 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው፣ ለአስር ቀናት (60 ሰዓታት) የተሰጣቸውን አቅም ማጎልበቻ ስልጠና አጠናቀዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎቹ ከትናንት ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀን የመለማመጃ ፈተና እየሰጡ መሆናቸው ታውቋል፡፡

የትምህርት ቤት አመራሮቹ በዛሬው ዕለት ዋናውን የምዘና ፈተና እንደሚወስዱ ይጠበቃል፡፡ የሚወስዱትን ምዘና ተከትሎ የምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡

በምዘና ፈተናው አጥጋቢ ውጤት ያላመጡ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች በቀጣይ የምዘና ሒደት ውስጥ የሚያልፉበት ዕድል እንደሚመቻች ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ከሐምሌ 23/2016 ዓ.ም ጀምሮ በስልጠና ላይ የሚገኙ መምህራንም ለ20 ቀናት (120 ሰዓታት) የሚሰጣቸውን ስልጠና ሲያጠናቅቁ ተመሳሳይ ፈተና ይወስዳሉ።

ምስል፦ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በ2011 ዓ.ም በመንግሥት ስፖንሰርነት በክረምት ትምህርት መርሐግብር የ PGDT ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም የክረምት ትምህርት ምዝገባ ነሐሴ 10 እና 11 / 2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦ በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ሬጅስትራር
ለተጨማሪ መረጃ 👉 0927432569 / 0938197896

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ቦረና ዩኒቨርሲቲ በ2017 የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና በተከታታይ መርሐግብር በ12 የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት መስኮች የመግቢያ መስፈርት ያሟሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

አመልካቾች የሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ማለፍ ይጠበቅባቸዋል።

(ቦረና ዩኒቨርሲቲ በቀጣይ ዓመት የሚያስተምራቸው የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም የትምህርት መስኮች ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
ዩኒቨርሲቲዎች ለሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ቤት አመራሮች ሲሰጡት የቆዩትን ልዩ የክረምት አቅም ግንባታ ስልጠና አጠናቀዋል፡፡

የትምህርት ቤት አመራሮቹ ከሐምሌ 23/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ቀናት (60 ሰዓታት) የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎቹ ስልጠናውን በአግባቡ መከታተላቸውን የሚመዝን ፈተና ለትምህርት ቤት አመራሮቹ በዛሬው ዕለት መስጠት ጀምረዋል፡፡

ሠልጣኞቹ ከ70% የበየነ-መረብ ፈተና እንዲሁም ከ30% በአሠልጣኝ መምህራን የተዘጋጀ ምዘና ወስደው በድምሩ 70% እና ከዚያ በላይ የሚያመጡ ሠልጣኞች የምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል ተብሏል።

በምዘና ፈተናው አጥጋቢ ውጤት ያላመጡ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች በቀጣይ የምዘና ሒደት ውስጥ የሚያልፉበት ዕድል እንደሚመቻች ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ምስል፦ ጅማ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

በክልሉ የ8ኛ ክፍል የማለፊያ ዝቅተኛ ነጥብ 50 በመቶ ሲሆን፤ ለአካል ጉዳተኞች 45 በመቶ እንደሆነ ተገልጿል።

በዚህም በክልሉ 110,772 መደበኛ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የወሰዱ ሲሆን፤ 48,728 ወይም 44 በመቶ ተማሪዎች 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ተማሪዎች https://ce.ministry.et/ ላይ የአድሚሽን ቁጥራቸውንና ስማቸውን በማስገባት ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ ተብሏል።

@tikvahuniversity
“ በነሐሴ ነበር መመረቅ የነበረብን ግን ት/ቤቱ ኮርሶችን አልጨርስም ስላለ ወደ ጥር ወስዶናል ” - ተመራቂ ተማሪዎች

የ2013 ባች "3,000" የቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው “አዲስ ህግ በማውጣት” የመመረቂያ ጊዜያቸውን ሊያራዝምባቸው በመሆኑ ቅሬታ እንዳደረባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የተማሪዎቹ አስተባባሪ ምን አሉ ?

“ ነሐሴ ወር ነበር መመረቅ የነበረብን ግን ት/ቤቱ ኮርሶችን አልጨርስም ስላለ ወደ ጥር ወስዶናል፡፡ አሁን ሪሰርች እየራን ያለን ልጆች ነን፡፡

አዲስ ህግ አወጣ ት/ቤቱ፣ ‘ከ C በታች ያላችሁ ተማሪዎች ኮርሱን ድገሙ’ ብሎ፡፡ እኛም ፒቲሽን አሰባስበን ለት/ቤቱ ይህ ነገር ተገቢ እንዳልሆነ፣ ጊዜ እንደሌለን አስረድተን አስገባን፡፡

ከዚያ ‘የእናንተ በልዩ ሁኔታ ይታያል ተረጋጉ፣ ትምህርታችሁን ቀጥሉ’ ብለውን እየቀጠልን በሳምንቱ ደግሞ ሌላ ማስታወቂያ ወጣ፡፡ በ‘Reexam ተፈተኑ፣ በReexam ፋቁት’ የሚል፡፡ ይህንንም ስንሰማ ፒቲሽን አሰባስበን በድጋሚ ት/ቤቱን ጠይቀን ነበር፡፡

16 ኮርሶች ናቸው የምንወስዳቸው፡፡ ከ16 ኮርሶች 5 ከ‘C’ ማይነስ በታች ያለባቸው ተማሪዎች አሉ፡፡ ት/ቤቱ የሚለው ለእያንዳንዱ ትምህርት 100 ጥያቄዎች ይውጡና ተፈትናችሁ ከ50 በላይ አምጡ ነው፡፡

‘Supportive class ነው ይፈጠራል’ ነው እያለ ያለው፤ ግን አይደለም፡፡ ስለ Supportive class በዝርዝር አስረዱን ስንላቸው ሊነግሩን ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ግዴታ ውሰዱ ከተባለ ደግሞ 2018 ዓ/ም ነው የምንመረቀው፡፡ ኮርሱን ጠብቀው ወስደው ነው ይፈተኑ እየተባልን ያለነው፡፡

ት/ቤቱ ደግሞ ስንገባ ህግና ደንብ ሰጥቶን ነበር፡፡ ‘ከቱ (ከ2) በታች ውጤት አታምጡ እና ‘F’ በታች መሆን የለበትም፡፡ ‘F’ ካልሆነ ደግሞ ምንም አይነት ኮርስ አትደግሙም’ ብሎን ነበር፡፡

አምና ጠይቀናቸው ነበር ሁሉንም የትምህርት ቤቱን አካል አስቀምጠን ‘C’ ውጤት ለመፋቅ ምንድን ነው ማድረግ ያለብን? ብለን፤ አሳሳቢ ቦታ ላይ ካልገባችሁ መድገም አይጠበቅባችሁም ብለውናል።

ያኔ ጊዜው በነበረን ወቅት ሳያስደግመን አሁን በመጨረሻው ሰዓት ላይ ድገሙ እያለን ነው፡፡ አሁን ደግሞ እንደ ግቢ የመውጫ ፈታና ብሎ አውጥቶ እየተፈተንን ነው፡፡

እንዲህ አይነት አሰራር በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም የለም፡፡ የኛም ትምህርት ቤት ዘንድሮ ‘C’ ያመጡ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡ ታዲያ ለኛ ሲሆን ነው እንዴ አዲስ ህግ የሚወጣው? ጠይቀናቸው ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም፡፡” የሚል ቅሬታ አቅርቧል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለቀረበበት ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጥ ለቀናት ብንጠብቅም፤ ጉዳዩ " የሚመለከታቸው አካላት ስብሰባ ላይ ናቸው" በመባሉ ለጊዜው ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡

በተጨማሪ በተማሪዎቹ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ያሏቸው የአካዳሚክ አካልን ያናገርን ሲሆን፣ በኮሚዩኒኬሽን በኩል ምላሽ እንድንጠይቅ፣ እሳቸው የማይመች ቦታ ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ወደ ኮሚዩኒኬሽን የተደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡ ምላሽ ከሰጡ በቀጣይ ሃሳባቸውን የምናቀርብ ይሆናል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ከ5,500 በላይ ትምህርት ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል። - ኢሰመኮ

በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ባሉ ግጭቶችና ሌሎች ምክንያቶች የተነሳ ከ5,500 በላይ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራቸውን ከማከናወን ውጪ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።

በዚህ ምክንያት በአገሪቱ የዜጎች የትምህርት መብት “በእጅጉ እየተጣሰ” ነው ተብሏል።

በስምንት ክልሎች 5,564 ትምህርት ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ በመሆናቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህጻናት ከትምህርት ገበታቸው መስተጓጎላቸውን ኮሚሽኑ አመልክቷል።

ትምህርት ቤቶች በተለያዩ አደጋዎች ምክንያት እየተዘጉ ሲሆን፤ በግጭት ውስጥ ባሉ አካባቢዎች ደግሞ የጦር ካምፕ ሆነው እያገለገሉ እንደሚገኙ የኢሰመኮ የሴቶች፣ የህጻናት፣ የአረጋውያን እና የአካል ጉዳተኞች መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገ/ሐዋሪያ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በአሁኑ ሰዓት ከአራት ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ውጭ እንደሆኑ ጠቅሷል።

የትጥቅ ግጭት እየተደረገበት ያለው አማራ ክልል በ2016 ዓ.ም. ከ2.6 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጪ መሆናቸውን ገልጿል።

ኢሰመኮ አሳሳቢ ሆኗል ባለው የትምህርት መብት አደጋ ላይ መውደቅ እና መፍትሔዎቹ ዙሪያ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከክልል ትምህርት ቢሮዎች እንዲሁም መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ባለፈው ሐምሌ ወር መምከሩን ገልጿል።

በምክክሩ የሚመለከታቸው አካላት ለችግሩ ፈጣን እና የተቀናጀ የመፍትሔ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ኮሚሽኑ አሳስቧል። #ቢቢሲ

@tikvahuniversity
#ይመዝገቡ
#ዛሬ_ይጠናቀቃል

በ2017 የትምህርት ዘመን በድኅረ-ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ አድርገዋል?

ምዝገባው ዛሬ ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

ለመመዝገብ 👇
https://NGAT.ethernet.edu.et

@tikvahuniversity
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ
#InjibaraUniversity

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

► የሥራ መደብ፦ በተለያዩ የሙያ መስኮች
► ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 114
► ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ
► የሥራ ቦታ፦ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የማመልከቻ ቦታ፦
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የሰው ሃብት አስተዳደር ወይም በአዲስ አበባ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ወኪል ቢሮ 4 ኪሎ ብርሃንና ሰላም ህንጻ

ለተጨማሪ መረጃ፦
0588270461 / 0913967604

(እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ያወጣው ሙሉ ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
2024/10/02 20:37:48
Back to Top
HTML Embed Code: