Telegram Web Link
በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናዋን በመውሰድ ላይ የነበረችው ተማሪ የወንድ ልጅ እናት ሆናለች፡፡

በቀሉ ተስፋ ከቄለም ወለጋ አካባቢ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተናዋን ለመውሰድ ነበር በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተገኘችው፡፡

ፈተናዋን እየወሰደች የልጅ እናትም ሆናለች፡፡ ልጇም እሷም በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ ተማሪ በቀሉ ፈተናዋን እየወሰደች እንደምትገኝ ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

@tikvahuniversity
በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናዋን እየወሰደች የምትገኘው ተማሪ ኒሞ ኢብራሂም የልጅ እናት ሆናለች፡፡ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ልጇን ወልዳለች፡፡

ብዙ የለፋችበትና የተዘጋጀችበት የ12ኛ ክፍል ፈተና እንዲያመልጣት ያልፈለገችው ተማሪ ኒሞ፤ ከሆስፒታል ሆና የመጨረሻ ቀን ፈተናዋን በመውሰድ ላይ ትገኛለች፡፡

@tikvahuniversity
ለቻርጀር መሯሯጥ ድሮ ቀረ! ገና ቀኑ ሳይጋመስ የሚያልቅ ባትሪ አላማረራችሁም? እንግዲያውስ ቅመም Itel Pro ለእናንተ ነው! ባለ የ4000mAh የባትሪ አቅም ያለው ቅመም Itel በአንድ ጊዜ ቻርጅ ብቻ ለሁለት ቀናት እንደልባችሁ ስልካችሁን መጠቀም ያስችላችኋል! ቅመም Itel Pro በሄዳችሁበት ሁሉ አብሯችሁ ነው!

#SafaicomEthiopia
#MpesaSafaricom
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether
#WallagaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የ2016 የክረምት መርሐግብር ነባር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም የ PGDT ተማሪዎች ምዝገባ ከሐምሌ 15-16/2016 ዓ.ም እንደሚካሔድ ገልጿል።

ምዝገባ የሚካሔደው በነበራችሁበት ካምፓስ ሲሆን፤ የ PGDT ተማሪዎች ምዝገባ በዋናው ካምፓስ መሆኑ ተገልጿል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#NATIONAL_EXAM

ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከትግራይ ክልል ውጪ ዛሬ ተጠናቋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከማክሰኞ ሐምሌ 9/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በወረቀት እና በኦንላይን ሰሰጥ ቆይቷል።

ዛሬ ከሰዓት ከተሰጠው የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና በኋላ፣ ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከትግራይ ክልል ውጪ መጠናቀቁ ታውቋል። በዚህም ተፈታኞች ወደየቤተሰቦቻቸው መመለስ ጀምረዋል፡፡

በትግራይ ክልል ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ነገ ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡

@tikvahuniversity
#EAES

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

"በወረቀት እና በበይነ መረብ እየተሰጠ ያለው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና፥ በሰላምና እጅግ በጣም በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል" ብሏል አገልግሎቱ።

በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ ክልል እየተሰጠ ያለው የመልቀቂያ ፈተና ነገ ከሰዓት በፊት እንደሚጠናቀቅ አገልግሎቱ ገልጿል።

አገልግሎቱ በፈተና የመስጠት ሒደቱ ለተሳተፉ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ትምህርት ቢሮዎች፣ የፀጥታና ደህንነት ተቋማት፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮጵያ መብራት ኃይል፣ የፈተና አስፈጻሚዎች፣ አመራሮች እና ተማሪዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahuniversity
2024/10/01 19:14:49
Back to Top
HTML Embed Code: