Telegram Web Link
በአዲስ አበባ የተፈታኞች አሸኛኘት በፎቶ

የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች አሸኛኘት በኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት

@tikvahuniversity
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለማታ እና ቅዳሜና እሁድ ነባር ተማሪዎች አውጥቶት የነበረውን የምዝገባ ጥሪ በቀናት አራዝሟል።

ኢንስቲትዩቱ የ1ኛ፣ 2ኛ፣ 4ኛ እና 5ኛ ዓመት የማታ እንዲሁም የቅዳሜና እሁድ ተማሪዎች ምዝገባ ከሐምሌ 13-15/2016 ዓ.ም ይካሔዳል ብሎ የነበረ ሲሆን፤ ምዝገባው ከሐምሌ 19-22/2016 ዓ.ም ይካሔዳል ተብሏል።

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና በአስር የፈተና ማዕከላት በወረቀት እና በኦንላይን መሰጠቱ ይታወቃል።

ከማዕከላቱ መካከል ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ አንዱ ነው።

በሁለተኛው ዙር ፈተና፥ 184 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በኮሌጁ በኦንላይን ፈተናቸውን ወስደዋል።

@tikvahuniversity
በትግራይ ክልል እየተሰጠ የሚገኘው ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

በ2013/14 ዓ.ም በቀድሞ ስርዓተ ትምህርት ተምረው ፈተናውን ሳይወስዱ የቆዩ ተማሪዎች ፈተናቸውን ከሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲወስዱ ቆይተዋል፡፡

ዛሬ በጠዋቱ መርሐግብር እየተሰጠ ከሚገኘው የኬሚስትሪ ትምህርት ፈተና በኋላ፥ በክልሉ በሁለት ዙር የተሰጠው መልቀቂያ ፈተና ይጠናቀቃል።

23 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች፤ ለአራት ተከታታይ ቀናት በመቐለ፣ ራያ፣ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች የተሰጠውን ሁለተኛ ዙር ፈተና እንደወስዱ ይገመታል።

በተያያዘ መረጃ በራያ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ መልቀቂያ ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ገልጿል።

@tikvahuniversity
ከባንክ ወደ M-PESA አካውንታችን አሁኑኑ ብር እንላክ፣ እስከ 50 ብር ስጦታ እናግኝ፣ M-PESA በዘዴ ይቀጥላል!

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉 https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether
#Tigray_National_Exam

በትግራይ ክልል በቀድሞው ስርዓተ ትምህርት ከ9-12ኛ ክፍል ለተማሩና የመልቀቂያ ፈተና ሳይወስዱ ለቆዩ ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተጠናቋል፡፡

ዛሬ በጠዋት መርሐግብር የተሰጠውን የኬሚስትሪ ትምህርት ፈተና ተከትሎ፥ በክልሉ በሁለት ዙር የተሰጠው መልቀቂያ ፈተና መጠናቀቁ ተገልጿል።

በክልሉ በወረቀት እና በበይነ መረብ በሁለት ዙር ሲሰጥ የቆየው 12ኛ ክፍል ፈተና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡

በክልሉ በሁለት ዙር የተሰጠውን መልቀቀያ ፈተና በድምሩ 54 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች በመቐለ፣ ራያ፣ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች እንደወስዱ ይገመታል።

@tikvahuniversity
#MoE

ከሐምሌ 2-12/2016 ዓ.ም የተሰጠውን የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መጠናቀቅን በማስመልከት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ዝርዝር መግለጫ ዛሬ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡

ዘንድሮ ከ700,000 በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን እና በወረቀት ለመውሰድ መመዝገባቸው ይታወቃል፡፡

- በሁለት ዙር የተሰጠው ፈተና ምን ያህል ስኬታማ ነበር?
- ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ምን ልምድ ተገኘበት?
- የፀጥታ ችግር ባለባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች ለፈተና ያልተቀመጡ ተማሪዎች እጣ ፈንታ ምንድን ነው የሚሆነው?

በነዚህ እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ሚኒስትሩ የሚያነሷቸውን ጉዳዮች ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል፡፡

@tikvahuniversity
2024/10/01 22:42:48
Back to Top
HTML Embed Code: