Telegram Web Link
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት መርሐ ግብር የመጀመርያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ምዝገባ ሐምሌ 21 እና 22/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

ነባር የክረምት ተማሪዎች የምዝገባ ቦታ በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ሬጅስትራር ቢሮ ሲሆን፤ በመንግሥት ስፖንሰርነት የምትማሩ የመገጣጠሚያ ደብዳቤ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

በ2016 ዓ.ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ እንድትሰለጥኑ የተመደባችሁ አዲስ ሰልጣኝ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የምዝገባ ቀን ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

አዲስ ሰልጣኝ መምህራንና የትምህርት አመራሮች ለምዝገባ ስትሔዱ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

Note: ነባር የ PGDT ተማሪዎች የምዝገባ ቀን በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለጤና ሳይንስ እና የእንስሳት ህክምና ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል፡፡

የጤና ሳይንስ እና የእንስሳት ህክምና ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 29 እና 30/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም ነባር የክረምት መርሐግብር የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም እንዲሁም የ PGDT ሰልጣኞች ምዝገባ ሐምሌ 22 እና 23/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል፡፡

ከሐምሌ 24/2016 ዓ.ም ጀምሮ የቲቶሪያል ትምህርት የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሁሉም ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው በኦንላይን ብቻ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፤ http://estudent.mwu.edu.et/auth/login በመግባት ምዝገባችሁን መማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል።

@tikvahuniversity
#EthiopianCivilServiceUniversity

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት ትምህርት መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 15 እና 16/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል፡፡

የማታ ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 16/2016 ዓ.ም እንዲሁም የዕረፍት ቀናት ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 20 እና 21/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተከታታይ መርሐግብር በመጀመርያ ዲግሪ #በፋሽን_ዲዛይን ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

የምዝገባ ጊዜው የሚያበቃው ➭ ሐምሌ 19/ 2016 ዓ.ም

አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር የወጣውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መስፈርት ወይም መቁረጫ ነጥብ የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
#NATIONAL_EXAM

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የሁለተኛ ቀን ፈተና እየተሰጠ ነው፡፡

ሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀት እና በኦንላይን እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በዛሬው የሁለተኛ ቀን ፈተና በጠዋቱ መርሐግብር የስኮላስቲክ አፕቲትዩድ ፈተና እየተሰጠ ሲሆን፤ ከሰዓት የፊዚክስ ትምህርት ፈተና ይሰጣል፡፡

ምስል፦ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ ሁሉም የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የ2017 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባን በኦንላይን ብቻ እያካሔዱ ነው።

በከተማዋ ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ የሚያስተምሩ ሁሉም የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የ2017 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባን በኦንላይን ብቻ እንዲያካሒዱ ተደረገ።

አሰራሩ በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ እየተደረገ ሲሆን፤ በዚህም በከተማዋ የነባር ተማሪዎች ምዝገባ እና የመጽሐፍት ስርጭት ከሰኔ 30/2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የኦንላይን ምዝገባው በከተማዋ በሚገኙ ከቅድመ አንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል በሚያስተምሩ 555 የመንግሥት ትምህርት ቤቶች እየተካሄደ መሆኑን በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት እና ማስፋት ዳይሬክተር ደረጀ ዳኜ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

በአዲሱ አሰራር ከ600 ሺህ በላይ ተማሪዎች ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የጠቆሙት አቶ ደረጀ፤ በመጀመሪያው ሳምንት የምዝገባ ጊዜ ብቻ 16 ሺህ ተማሪዎች መመዘገባቸውን ገልፀዋል።

አዲሱ አሰራር ተማሪዎች ኢንተርኔትን በመጠቀም ከየትኛውም ቦታ ሆነው “E-School System” በተባለ ሶፍትዌር አማካኝነት እንዲመዘገቡ የሚያደርግ ነው።

እስከ ሐምሌ መጨረሻ ድረስ ይቆያል ተብሎ የተገመተው የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የኦንላይን ምዝገባ ሲጠናቀቅ፤ የግል ትምህርት ቤቶችም አዲሱን አሰራር ተግባራዊ ያደርጋሉ ተብሏል፡፡ #ኢትዮጵያኢንሳይደር

ሙሉውን ያንብቡ 👉 https://ethiopiainsider.com/2024/13585/

@tikvahuniversity
የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞቹ እናት እና ልጅ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

እናት የሺወርቅ ደስታ እና ልጅ አዳነች ኃይሌ እናትና ልጅ ሲሆኑ፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናቸውን ለመውሰድ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ይገኛሉ።

46 ዓመቷ እናት የሺወርቅ፣ ትምህርት የጀመሩት ሦስት ልጆች ከወለዱ በኋላ መሆኑን ገልፀው፤ ከተማሪ ልጃቸው አዳነች ጋር እኩል ጀምረው ለዚህ መብቃታቸውን ይናገራሉ።

ከእናቷ ጋር አብረው ፈተና እየወሰዱ መሆናቸው እንዳስደሰታት የገለፀችው ተማሪ አዳነች ኃይሌ፤ ቤትም አብረው በማጥናት ይተጋገዙ እንደነበር አክላለች።

@tikvahuniversity
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሪሚዲያል ተማሪዎች የፕሮግራም ድልድል የሚሰሩበትን መስፈርት አሳውቋል።

በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) በቀን ሐምሌ 10/2016 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከ ደብዳቤን ቲክቫህ ተመልክቷል።

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ የደብዳቤውን ትክክለኛነት ከዋና ሥራ አስፈፃሚው አረጋግጧል።

የሪሚዲያል ተማሪዎቹን ወደ ፕሮግራም ለመመደብ በሚደረግ ድልድላ ተመሳሳይ መሰፈርት መጠቀም እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

በዚህም ሁሉም ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 20%፣ በአንደኛ ሴሚስተር አማካይ ውጤት 50% እና ወደ መስክ መግቢያ ፈተና 30% ብቻ የሚደለደሉ መሆኑን ደብዳቤው ያስረዳል።

@tikvahuniversity
መንትዮቹ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ

ምስጋና አለምዬ እና በረከት አለምዬ መንትዮች ናቸው። በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንሰ ፈተናቸውን እየወሰዱ ነው።

መንትዮቹ በባቢሌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ለሀገር አቀፍ ፈተናው ሲዘጋጁ እንደነበር ይናገራሉ።

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለፈተና በአንድ ላይ በመመደባቸው ደስተኛ ሆነናል ያሉት መንትዮቹ፤ "ጠንክረን በጋራ ስናጠና ነበር፣ በቀጣይም ውጤት አስመዝግበን ወደ ዩኒቨርሲቲ አንድ ላይ ለመግባት እየጣርን ነው" ለዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰብ ሬዲዮ ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
መናገር እና መስማት አለመቻል ከትምህርት ገበታዋ ያላስቀራት ብርቱ ተማሪ

ተማሪ ንፁህ ጌታቸው ትባላለች፡፡ ተወልዳ ያደገችው በመተከል ዞን በቡለን ወረዳ ነው፡፡ መናገርና መስማት የተሳናት ወጣት ብትሆንም እነዚህ ከባድ ችግሮች ከመማር አላገዷትም፡፡

በህይወቷ በርካታ ፈተናዎችን እንዳሳለፈች ተማሪዋ በአስተርጓሚዋ በኩል ትናገራለች፡፡ ትምህርት ቤት ደርሶ መመለስ ባይቸግራትም፥ መናገር እና መስማት ባለመቻልዋ የሰዎችን ድጋፍ ሁሌም ትሻለች፡፡

ለዚህ ደግሞ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እስከዛሬው ፈተና ድረስ ተለያይተው የማያውቁ ዝምድናም ጭምር ያላቸው ተማሪ አዳነች ሀይሌ ሁሌም ከጎኗ ናት። ሁለቱም በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህር መስክ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን እየወሰዱ ነው።

ተማሪ ንፁህ መናገርም ሆነ መስማት ባትችልም ከፊቷ ፈገግታ አይጠፋም ሁሌም ደስተኛ ናት፡፡ "ለውጤት ሁሌም ጠንክሬ እሰራለሁ" የምትለው ተማሪ ንፁህ፤ ለፈተናው በእጅጉ እንደተዘጋጀች በአስተርጓሚዋ አማካኝነት ተናግራለች፡፡

@tikvahuniversity
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የነባር የክረምት ትምህርት መርሐግብር ተመራቁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ሐምሌ 13 እና 14/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

የተማሪዎቹ ምዝገባ ሐምሌ 15 እና 16/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡

የቲቶሪያል ትምህርት ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም መሰጠት ይጀምራል ተብሏል።

@tikvahuniversity
#WoldiaUniversity

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የነባር የክረምት መርሐግብር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች እንዲሁም የ PGDT ሰልጣኞች ምዝገባ ሐምሌ 15 እና 16/2016 ዓ.ም ያከናውናል።

ትምህርት ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

አዲስ የ PGDT ሰልጣኞች ምዝገባ እስከ ሐምሌ 14/2016 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

@tikvahuniversity
አምቦ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም ነባር የክረምት መርሐግብር የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች እንዲሁም የ PGDT ፕሮግራም ሰልጣኞች ምዝገባ ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
➧ የተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች በዋናው ካምፓስ
➧ የሌሎች ትምህርት ክፍል ተማሪዎች በሙሉ ሀጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ

ትምህርት ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም በተመዘገባችሁበት ካምፓስ የሚጀምር መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመንግሥት ስፖንሰርነት የምትማሩ የመገጣጠሚያ ደብዳቤ መያዝ ይጠበቅባችኋል።

@tikvahuniversity
#NATIONAL_EXAM

ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል፡፡

ሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 09/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በወረቀት እና በኦንላይን በመላ አገሪቱ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

በዛሬው የሦስተኛ ቀን ፈተና፤ በጠዋቱ መርሐግብር የኬሚስትሪ ትምህርት ፈተና የተሰጠ ሲሆን፤ በከሰዓቱ መርሐግብር የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና የሚሰጥ ይሆናል፡፡

በትግራይ ክልል ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ ሲሆን፤ ነገ ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይታወቃል፡፡

ምስል፦ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ፣ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
2024/10/01 17:32:48
Back to Top
HTML Embed Code: