Telegram Web Link
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን ከዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የገባችው የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ብስራት ጌታነው ሴት ልጅ ተገላግላለች።

ተፈታኟ ሐምሌ 07/2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት አካባቢ በወልድያ ጠቅላላ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሴት ልጅ ወልዳለች፡፡

"እሷም፣ ልጇም በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ" የተናገረችው ተማሪ ብስራት፤ ፈተናዋና ለመውሰድ መዘጋጀቷን ገልጻለች፡፡ ዩኒቨርሲቲውም ፈተናዋን እስክትጨርስ አስፈላጊውን ድጋፍ አደርግላታለሁ ብሏል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በቅርቡ የተመረቀው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከነገ ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ይጀምራል፡፡

በሕጻናት፣ በማህፀንና ጽንስ፣ በአጠቃላይ ቀዶ ጥገና እና በውስጥ ደዌ ተመላላሽ ሕክምና እንዲሁም የተለያዩ የላቦራቶሪ እና ኢሜጂንግ አገልግሎቶች አገልግሎት መስጠት የሚጀምር መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከሰባት ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አገልግሎት ይሰጣል የተባለው ሆስፒታሉ፤ 600 የህሙማን አልጋዎች እና የተለያዩ ዘመናዊ የህክምና ግብዓቶች የተሟላለት ነው፡፡

@tikvahuniversity
#DebreMarkoUniversity

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የነባር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ የክረምት መርሐግብረ ተማሪዎች የምዝገባ ጌዜን በቀናት አራዝሟል።

የ2016 ዓ.ም ነባር የክረምት ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ሐምሌ 16 አና 17/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የክረምት መርሐግብር ነባር ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል።

3ኛ እና 4ኛ ዓመት ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ሐምሌ 21/2016 ዓ.ም ሲሆን፤ ምዝገባ የሚደረገው ሐምሌ 22 እና 23/2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

6ኛ ዓመት PGDT ተመራቂ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ሐምሌ 28/2016 ዓ.ም ሲሆን፤ ምዝገባ ሐምሌ 29 እና 30/2016 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የነባር የመጀመሪያ ዲግሪ እና የ PGDT የክረምት መርሐግብር ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም የምዝገባ ጊዜ ሐምሌ 15 አና 16/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በርቀት ለሚሰጡ ኮርሶች የሁለተኛ ዙር ቲቶሪያል ሐምሌ 17 እና 18/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#NATIONAL_EXAM

ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ይጀምራል።

ሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተና ከዛሬ ሐምሌ 9/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል።

በዛሬው የመጀመሪያ ቀን ፈተና የእንግሊዝኛ እና የሒሳብ ትምህርት ፈተናዎች ይሰጣሉ።

በተመሳሳይ በትግራይ ክልል ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ከዛሬ ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት በመቐለ፣ ራያ፣ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

@tikvahuniversity
የግል ተፈታኞች ቅሬታና የት/ት/ሚ/ር ምላሽ

ባለፈው ወር የተሰጠውን የመውጫ ፈተና የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከፈተናው ጋር ተያይዞ ያላቸውን ቅሬታ ለቲክቫህ አቅርበዋል።

"የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እኩል ፈተናውን ወስደው፣ ውጤት ለምን በተለያየ ጊዜ ተገለፀ?" "የመንግሥት ተፈታኞች በብዛት ሲያልፉ በርካታ የግል ተቋማት ተፈታኞች ለምን ወደቁ?" "እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ነጥብ ያላቸው መቶ ጥያቄዎች ተፈትን 37.92 አይነት ውጤት እንዴት ተመዘገበ?" የሚሉ ጥያቄዎች በተፈታኞቹ ተነስቷል።

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ የሆኑትን እዮብ አየነው (ዶ/ር) ጠይቋል።

ከውጤት ነጥብ ጋር በተያያዘ ለተነሳው ጥያቄ ኃላፊው ተከታዩን ብለዋል፦

1. የጤና ትምህርት ዘርፍ ሁለት ፈተና (ጠዋት ከ100 ከሰዓት ከ100 በድምሩ ከ200) ስለሚፈተኑና ለማለፊያ የሁለቱ ፈተናዎች ውጤት ተደምሮ አማካኝ ውጤት ስለሚያዝ ውጤታቸው በነጥብ ሊቀመጥ ይችላል፡፡

2. አንዳንድ የትምህርት ፕሮግራሞች ለምሳሌ ሒሳብ እና ማርኬቲንግ ማኔጅመንት በተለያዩ ምክንያቶች ተማሪዎች የተፈተኑት ጥያቄ ቁጥር ከመቶ ያነሰ ስለነበር ያገኙት ውጤት ወደ መቶ ሲቀየር በነጥብ ሊቀመጥ ይችላል፡፡

"ውጤት ሲገለፅ የጊዜ መቀዳደም ካልሆነ በስተቀር በሲሰተሙ ላይ ምንም አይነት ችግር እንዳልነበረ" ኃላፊው አረጋግጠዋል።

የማለፍ ምጣኔን በተመለከተ "ተፈታኞቹ የተማሩባቸውን ተቋማት እንዲሁም የራሳቸውን ብቃት መመልከት" አለባቸው ብለዋል።

ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች 100% ያሳለፉ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዳሉ ኃላፊው ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
#NATIONAL_EXAM

ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና በመላ አገሪቱ በመሰጠት ላይ ይገኛል።

ሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከዛሬ ሐምሌ 9/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

በዛሬው የመጀመሪያ ቀን ፈተና በጠዋቱ መርሐግብር የእንግሊዝኛ ፈተና እየተሰጠ ሲሆን፤ ከሰዓት የሒሳብ ትምህርት ፈተና ይሰጣል።

ምስል፦ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

@tikvahuniversity
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ የገቡ ሚላሹ በርኸ እና ወይኒ ንጉሱ የተባሉ ሁለት ነፍሰጡር ተማሪዎች ትናንት ልጆቻቸውን በሰላም ተገላግለዋል፡፡

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጁ ሪፈራል ሆሰፒታል የህክምና ባለሙያዎች አስፈላጊውን እንክብካቤ ለአራስ ተፈታኝ ተማሪዎቹ እያደረጉላቸው እንደሚገኙ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ተፈታኞቹ እናቶች በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት ፈተናቸውን እየወሰዱ ነው ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
የ12ኛ ክፍል ፈተናቸውን አብረው እየወሰዱ የሚገኙት እናት እና ልጅ

የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርታቸውን አብረው ሲከታተሉ የነበሩት እናት እና ልጅ ሀገር አቀፍ ፈተናውን በጥሩ ውጤት ለማለፍ በጋራ ሲዘጋጁ መቆየታቸውን ይናገራሉ፡፡

እናት ወ/ሮ ፍሬህይወት ኃይሉ የ8ኛ ክፍል ተማሪ እያለች ልጇን በመውለና በማኅበራዊ ጫና ትምህርቷን አቋርጣ ነበር። በሒደት ያቋረጠችውን ትምህርት በመቀጠል፣ ከልጇ ተማሪ ሰብሪና ታጅር ጋር ትምህርቷን በመከታተል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በጥሩ ውጤት ለማጠናቀቅ ሲዘጋጁ መቆየታቸውን ገልፃለች።

እናት እና ልጅ እየተደጋገፉ ልጅ ቀን እናት በማታ ትምህርታቸውን እየተማሩ በመደጋገፍ ለፈተናው ሲዘጋጁ እንደነበር ወ/ሮ ፍሬህይወት ጠቁመው፤ ባለቤታቸውም ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ ድጋፍ ሲያደርግላቸው እንደነበረ ተናግራለች።

እናት እና ልጅ ፈተናቸውን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እየወሰዱ ሲሆን፤ ጥሩ ውጤት በማምጣት በቀጣይም አብረው ትምህርታቸውን ለመማር ማቀዳቸውን ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ሬዲዮ ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
እግሮቿን እንደ እጆቿ በመጠቀም የ12ኛ ክፍል ፈተናዋን እየወሰደች ያለችው ተማሪ

ተማሪ ኬይራ ጀማል በተፈጥሮ ሁለት እጆች የሌላት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ስትሆን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፈተናውን እየወሰደች ትገኛለች።

መምህራንና የዩኒቨርሲቲው አመራር በተማሪዋ ብቃት ብቻ ሳይሆን በስነ-ልቦና ጥንካሬዋ መደመማቸውን ይገልፃሉ።

ተማሪ ኬይራ በአንደኛ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷም የደረጃ ተማሪ እንደነበረች መምህራኖቿ ይመሰክራሉ።

ተማሪ ኬይራ ዛሬ በተጀመረው የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ መልቀቂያ ፈተና ከእኩዮቿ ጋር በመውሰድ ላይ ትገኛለች።

ፈተናውን በአንድ ድጋፍ ሰጪ መምህር በመታገዝ እግሮቿን እንደ እጆቿ በመጠቀም በኦንላይን እየተፈተነች ስትሆን፤ የኮምፒውተሩን ማውዝ የምትጠቀመው በእግሮቿ ነው።

"አካል ጉዳተኝነት ከምትፈልግበት መዳረሻ የማያግዳት፣ ይልቁንም ይበልጥ የሚያተጋት" መሆኑን ተማሪ ኬይራ ለኢዜአ ተናግራለች።

ፈተናውን በጥሩ ውጤት በማለፍ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደምትገባም በሙሉ ልብ ተናግራለች። #ENA

@tikvahuniversity
በትግራይ ክልል ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

በዚህኛው ዙር በ2013/14 የትምህርት ዘመን በቀድሞ ስርዓተ ትምህርት ተምረው ፈተናውን ሳይወስዱ የቆዩ ተማሪዎች ፈተናቸው እየወሰዱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

23 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች፤ ከዛሬ ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት በመቐለ፣ ራያ፣ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን ፈተና እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
ለቻርጀር መሯሯጥ ድሮ ቀረ! ገና ቀኑ ሳይጋመስ የሚያልቅ ባትሪ አላማረራችሁም? እንደዛ ከሆናችሁ ቅመም Itel Pro ለእናንተ ነው! ትልቅ የ4000mAh የባትሪ አቅም ስላለው በአንድ ጊዜ ቻርጅ ብቻ ለሁለት ቀናት እንደልባችሁ ስልካችሁን መጠቀም ያስችላችኋል! ቅመም Itel Pro በሄዳችሁበት ሁሉ አብሯችሁ ነው!

#SafaricomEthiopia
#MpesaSafaricom
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የክረምት መርሐግብር የ2016 ዓ.ም ምዝገባ የሚካሔደው ከሐምሌ 17 እስከ 19/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

ሰኞ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ትምህርት የሚጀምረው መሆኑ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
2024/10/01 15:40:04
Back to Top
HTML Embed Code: