Telegram Web Link
በሰዎች ለሰዎች ድርጅት የሐረር አግሮ ቴክኒክና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን 104 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ አስመርቋል።

ምሩቃኑ ለአምስት ዓመታት በማኑፋክቸሪንግ፣ በኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪክ እንዲሁም በአውቶሞቲቭና አግሮ ኢኮሎጂ ቴክኖሎጂ የትምህርት መስኮች ስልጠናቸውን ተከታትለው ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#NATIONAL_EXAM

ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች ዛሬ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች መግባት ጀምረዋል።

ሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሐምሌ 9-11/ 2016 ዓ.ም በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ለተፈታኞቹ አጠቃላይ ገለፃ ሐምሌ 8/2016 ዓ.ም እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

በተያያዘ መረጃ፣ በትግራይ ክልል ሁለኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 9-12/2016 ዓ.ም በመቐለ፣ ራያ፣ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

@tikvahuniversity
በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ነባር የክረምት መርሐግብር ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ምዝገባ ሐምሌ 13 እና 14/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በ PGDT ፕሮግራም መሰልጠን የምትፈልጉ አዲስ አመልካቾች በተጠቀሱት ቀናት በአሰላ ግብርና ከምፓስ ክና በቆጂ ከምፓስ በአካል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ለ Fulbright African Research Scholars Program (FARSP) ያመልክቱ!

የማመልከቻ ጊዜው ነገ ያበቃል!

የዩኒቨርሲቲ መምህር ነዎት? ምርምርዎትን በዩናይትድ ስቴትስ ማከናወን ይፈልጋሉ?

ለዓመታዊው የፉልብራይት አፍሪካ የምርምር ምሁራን ፕሮግራም (FARSP) 2025/26 ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን ያመልክቱ!

የማመልከቻ ጊዜው የሚያበቃው 👇
ሐምሌ 8/2016 ዓ.ም

ለማመልከት 👇
https://apply.iie.org/fvsp2025

ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እንዲሁም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት 👇 [email protected]

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት የመጀመሪያ ዲግሪ የማታ እና የእረፍት ቀናት ፕሮግራም እንዲሁም የድኅረ ምረቃ የእረፍት ቀናት ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም የክረምት ሴሚስተር ምዝገባ ሐምሌ 15 እና 16/2016 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ትምህርት ለማታ ተማሪዎች ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም፤ ለእረፍት ቀናት ተማሪዎች ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም የሚጀመር መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በክረምት መርሐግብር በመጀመርያ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም የክረምት ትምህርት ምዝገባ የሚካሄደው ሐምሌ 13 እና 14/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የቲቶሪያል ትምህርት ከሐምሌ 15 እስከ 17/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ምህንድስና የትምህርት መስክ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 29 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በሳምንት መጨረሻ ትምህርታቸውን ተከታትለው በማጠናቀቅና የወሰዱትን የመውጫ ፈተና በማለፍ ለምርቃት የበቁ መሆናቸው ተገልጿል።

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ጋር በመቀናጀት ተመራቂዎቹ በግልገል ጊቤ ቁጥር 3 ኃይል ማመንጫ ውስጥ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ መደረጉን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም ነባር የክረምት መርሀሐግብር ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ምዝገባ ሐምሌ 15 እና 16/2016 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን አሳውቋል።

ትምህርት ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።

በሌላ በኩል፤ ዩኒቨርሲቲው ለጤና ሳይንስ እና የእንስሳት ህክምና ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል።

የጤና ሳይንስ እና የእንስሳት ህክምና ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ቀሪ ትምህርታችሁን እንድታጠናቅቁ ሐምሌ 15 እና 16/2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታድርጉ ተብሏል።

@tikvahuniversity
2024/10/01 11:33:46
Back to Top
HTML Embed Code: