Telegram Web Link
ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለክረምት ፕሮግራም ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል።

የነባር የክረምት ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 2 እና 3/2016 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

አዲስ የPGDT ኮርስ ተመዝጋቢዎች ምዝገባ ከሰኔ 25-30/2016 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

የክረምት ትምህርት ከሐምሌ 08/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#InjibaraUniversity

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የነባር የክረምት መርሐግብር ተማሪዎች የ2016 የትምህርት ዘመን የምዝገባ ጊዜ ከሐምሌ 15-17/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

@tikvahuniversity
#MattuUniversity

መቱ ዩኒቨርሲቲ የክረምት መርሐግብር የመጀመሪያ ዲግሪ እና የፒጂዲቲ ስልጠና ነባር ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 14 እና 15/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

ትምህርት ሐምሌ 16/2016 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

@tikvahuniversity
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የክረምት መርሐግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ነባር ተማሪዎች ምዝገባ ከሐምሌ 12-14/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

ትምህርት ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም እንደሚጀምር ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

የበጋ ኮርስ ተከታትላችሁ ነገር ግን ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት ያላስላካችሁ እስከ ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ድረስ ማስላክ ይኖርባችኋል፡፡

ይህ የጥሪ ማስታወቂያ የ PGDT ተማሪዎችን ያካትታል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ክረምት ትምህርት ምዝገባ ከሐምሌ 15-16/2016 ዓ.ም እንደሚካሔድ አሳውቋል።

ከሁለተኛ ክረምት/ዓመት በላይ የሆናችሁ ተማሪዎች በተጠቀሰዉ ቀን ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@tikvahuniversity
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት መርሐግብር ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከሐምሌ 15-16/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

ትምህርት የሚጀምረው፦
ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም

የአዲስ የ PGDT ሰልጣኞች ምዝገባ እስከ ሐምሌ 14/2016 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

@tikvahuniversity
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት መርሐግብር ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከሐምሌ 15-16/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

ትምህርቱ እስከ መስከረም 10/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
42A+ ያሳካው የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ

ደሴ ላንቲደር ይባላል፡፡ በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ምጣኔ ሃብት ትምህርት ክፍል ትምህርቱን ተከታትሎ አጠናቋል፡፡ ተማሪ ደሴ እጅግ ከፍተኛ ውጤት 3.99 CGPA እና 42A+ በማምጣት የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የዋንጫ እና የላፕቶፕ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

በተመሳሳይ ተማሪ ጥሩወርቅ አታሎ ከአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል ከጠቅላላ ሴት ተመራቂ ተማሪዎች ከፍተኛ ሆነውን 3.95 CGPA ውጤት በማምጣት የወርቅ የአንገት ሀብል ሽልማት ተበርክቶላታል።

በሌላ መረጃ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባልና የቡና ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት ዳኛቸው መሀሪ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት በሜዳሊያ ለተመረቁ ሴት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በቋሚነት የሥራ ዕድል ለመፍጠር ቃል ተገብቶላቸዋል።

ጂንካ ዩኒቨርስቲ ትናንት ሰኔ 27/2016 ዓ.ም 4ኛ ዙር የተማሪዎች የምረቃ ሥነ-ስርዓት ያካሔደ ሲሆን፤ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 871 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

@tikvahuniversity
#AAU_Commencement

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ሥነ-ስርዓት ነገ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም ያካሒዳል።


አጠቃላይ ተመራቂዎች - 5,911
በሦስተኛ ዲግሪ - 337
በሁለተኛ ዲግሪ - 2,837
በቅድመ ምረቃ - 2,737

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዳማ ከተማና አካባቢዋ ለሚገኙ ተማሪዎች ነፃ የክረምት ስልጠና አዘጋጅቷል።

የዩኒቨርሲቲው STEM ማዕከል ከአዳማ ት/ቤቶች ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችን አወዳድር ማሰልጠን ይፈልጋል።

ዘንድሮ ከ 7-11ኛ ክፍል ያጠናቀቃችሁ ተማሪዎች እስከ ሐምሌ 5/2016 ዓ.ም በኦንላይን ብቻ መመዝገብ እንደምትችሉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ስልጠናው በተቋሙ STEM ማዕከል ከሐምሌ 22 እስከ ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል፡፡

ምዝገባው የሚያበቃው 👇
ሐምሌ 05/2016 ዓ.ም

ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም ይመዝገቡ 👇
https://shorturl.at/aYXAj

@tikvahuniversity
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በኦንላይን እና በወረቀት እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል።

በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ፈተናው በኦንላይን እንደማይሰጥ የሚገልፁ መረጃዎች "በፍፁም ከእውነት የራቀ ሐሰተኛ" መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ፈተናው በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ ማምሻውን በተቋሙ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆች ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል።

በመሆኑም ተማሪዎች ይሄንን ተገንዝበው ዝግጅት ማድረግ እንዲቀጥሉ መክሯል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን የተሳካ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት እየሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል።

"የኦንላይን ፈተናው ቀርቷል" የሚሉ በማኅበራዊ ትስስር ገፆች የሚዘዋወሩ መረጃዎችን አስመልክተን የጠየቅናቸው የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር፤ "መረጃዎቹ ሐሰተኛ ናቸው" በማለት መልሰዋል።

@tikvahuniversity
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኦንላይን እና በወረቀት እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አረጋገጠ።

በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ፈተናው በኦንላይን እንደማይሰጥ የሚገልፁ መረጃዎች "ሐሰተኛ" ናቸው ያለው አገልግሎቱ፤ ፈተናው በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጥ በመሆኑ ተማሪዎች ይሄንን ተገንዝበው ዝግጅት ያድርጉ ብሏል።

@tikvahuniversity
2024/11/18 13:50:01
Back to Top
HTML Embed Code: