Telegram Web Link
#OdaBultumUniversity

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ 1,170 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎቹ 64ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ 1,106 ተማሪዎች ደግሞ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የተመረቁ ናቸው፡፡

የዩኒቨርሲቲው 6ኛ ዙር ተመራቂዎች፤ በመደበኛ፣ በቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በክረምት መርሐግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#WachemoUniversity

ዋቸሞ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 2,115 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

13ኛ ዙር ተመራቂዎቹ፥ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች 86.1 በመቶዎቹ የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሀብታሙ አበበ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
#BuleHoraUniversity

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ትምህርት መስኮች ያሰለጥናቸውን 1,456 ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያ ጊዜ 5 የሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ሰልጣኞችን አስመርቋል።

281 በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም እንዲሁም 1,169 በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ተማሪዎች ሌሎች የዩኒቨርሲቲው 11ኛ ዙር ተመራቂዎች ናቸው።

@tikvahuniversity
#HaramayaUniversity

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 3,370 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በቅድመ እና በድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 4,800 ተማሪዎች አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው 3,024 የመጀመሪያ ዲግሪ፣ 1,211 የሁለተኛ ዲግሪ፣ 38 የህክምና ስፔሻልቲ፣ 46 የዶክትሬት ዲግሪ እና 481 ልዩ ልዩ የመምህራን ስልጠና የወሰዱ ሰልጣኞችን አስመርቋል።

የሎጅስቲክስ ትምህርት ክፍል ተመራቂዋ ቤተልሔም ተስፋዬ 4.0 ነጥብ CGPA በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች።

@tikvahuniversity
#AmboUniversity

አምቦ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2,607 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው 1,689 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 909 በሁለተኛ ዲግሪ፣ 6 በሦስተኛ ዲግሪ እንዲሁም 3 በህክምና ስፔሻሊቲ በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና በማኅበረሰብ አገልግሎት በርካታ ሥራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በመስራት እንደሚገኝ የተቋሙ ፕሬዝዳንት ባይሳ ለታ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
ተማሪ ረዴት ዮናስ አስፋዉ (ከሕግ ት/ቤት)👏

በ2016 የትምህርት ዘመን ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተመራቂ ተማሪዎች መካከል የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ከአጠቃላይ 4.00 ነጥብ ውስጥ 3.86 ያስመዘገበችዉ የህግ ት/ቤት ተመራቂ ተማሪ ረዴት ዮናስ አስፋዉ በከፍተኛ ማዕረግ የአመቱ ልዩ ሴት ተሸላሚ ሆናለች።

Wolaita Sodo University

@tikvahuniversity
ተማሪ ወጋየሁ ወራጆ 👏

" የአይቻልም እና የአይሆንም መንፈስን መስበር ከተቻለ የማይቻል ነገር የለም " - ተማሪ ወጋየሁ ወራጆ

ወጋየሁ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአማረኛ ቋንቋ ስነ-ጽሑፍ እና ፎክሎር ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘ እና የባለብዙ ተሰጥኦ ባለቤት ታታሪ ወጣት ነው።

በፈተና የታጀበና በድል የተጠናቀቀ ጉዞ የማዕረግ ምሩቁን ሕይወት ይገልጻል።

የገጠሙት ፈተናዎች ለበርካታ ዓመታት ትምህርት እንዲያቋርጥ ቢያስገድዱትም ህልሙን ለማሳካት ዳግም ወደ ትምህርት አለም ተመልሶ ትምህርቱን በጥሩ ውጤት በድል ያጠናቀቀ የማዕረግ ተመራቂ ነው።

#AAU

@tikvahuniversity
በለጠ ቡቱና👏

" ጠንካራ ስነ ልቦና ችግሮችን መሻገሪያ ድልድይ ነው "- ወጣት በለጠ ቡቱና

በለጠ ቡቱና የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል አንዱ ነው፡፡

ለ5 ዓመታት በማታው የትምህርት መርሐ ግብር በማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ተማሪ በለጠ ጠንካራ ስነ ልቦና ካለ የማይታለፍ መንገድ የለም ብሏል።

ወጣት በለጠ ወላጅ እናትን በልጅነት ማጣትን ጨምሮ ህይወቱን በርካታ ፈተናዎችን ተጋፍጧል።

የአካል ጉዳት ያለበት ወጣት በለጠ አጋዥ አባትም የሌለው በመሆኑ የመኖር ተስፋውን ሊያደበዝዝ ቢችልም ለችግርና ለፈተና እጅ ባለመስጠት ጉዞውን ማስቀጠል ችሏል።

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ሲያመጣ በሲዳማ ክልል አርቤጎና ወረዳ የ20 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ከተደረገለት በኋላ ወደ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ አቅንቷል።

ዩኒቨርሲቲውም ከ1 ዓመት የትሞህርት ቆይታ በኋላ ነፃ የትምህርት፣ የማደሪያና የምግብ አገልግሎቶችን አመቻችቶለታል።

አካል ጉዳተኝነት ሳያግደው የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ካስመረቃቸው 4 ሺህ 800 ተማሪዎች ውስጥ አንዱ በመሆን በ3 ነጥብ 2 አጠቃላይ ውጤት የመጀመሪያ ዲግሪውን  አግኝቷል። #ኤፍቢሲ

@tikvahuniversity
በ2015 ዓ.ም ተቋርጦ የነበረው የክረምት ትምህርት መርሐግብር በዚህ ዓመት ይቀጥላል።

የክረምት ስልጠና መርሐግብር ባለፉት ዓመታት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በፀጥታ ችግሮች ምክንያት ጫና ውስጥ መቆየቱ ይታወቃል።

ስልጠናው በ2015 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ መቋረጡ የአግባብነት ጥያቄ ሲነሳበት እንደነበር አይዘነጋም።

ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ ምክንያቶች ላለፉት ዓመታት የተዛነፈውን የትምህርት ካላንደር ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ለማስተካከል እየሠራ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።

በዚህም የ2016 ዓ.ም የክረምት መርሐግብር ትምህርት ከሐምሌ ወር መጀመሪያ ሳምንት ይጀምራል ተብሏል።

@tikvahuniversity
2024/09/30 11:31:17
Back to Top
HTML Embed Code: