Telegram Web Link
#DebreBerhanUniversity

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1,248 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ፣ በማታ እና በተከታታይ መርሐግብር ያስተማራቸውን በመጀመሪያ ዲግሪ 882 እና በሁለተኛ ዲግሪ 366 በድምሩ 1,248 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

በምርቃት መርሐግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ፕሬዝዳንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር)፣ ዩኒቨርሲቲው የኢንዱስትሪ ትስስር አማካሪ ቦርድ መስርቶ ሥራ መጀመሩንና 14 ኢንዱስትሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ጋር እየሠሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
#InjibaraUniversity

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ እና በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ያስተማራቸውን ተማሪዎች አሰመረቀ ።

ዩኒቨርሲቲው 268 በድኅረ ምረቃ እና 428 በቅድመ ምረቃ ፕሮግራም በድምሩ 696 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት ባካሔደው 5ኛ ዙር የምረቃ ሥነ-ስርዓት፥ ከተመረቁ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ውስጥ 32 ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ በሕግ (LLB) ማስመረቁ ተገልጿል፡፡

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች መካከል 83 በመቶዎቹ የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
#WolkiteUniversity

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1,868 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው 1,760 ተማሪዎች በቅድመ ምረቃ ፕሮግራም እንዲሁም 108 ተማሪዎች በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም በድምሩ 1,868 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ እጅግ ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ልዩ ልዩ ሽልማቶች የተበረከተ ሲሆን፤ ተማሪ ከፋለ ጸጋዬ ከኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል 3.98 CGPA በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

@tikvahuniversity
#AdigratUniversity

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በ10ኛ ዙር ያስተማራቸውን 1,589 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 122 ተማሪዎች በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ 1,467 ተማሪዎች የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃን ናቸው፡፡

@tikvahuniversity
#WoldiaUniversity

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ የመውጫ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሁለተኛ ዲግሪ ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጠ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በቅድመ እና በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ያስተማራቸውን 544 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 103 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ ናቸው፡፡

በምርቃት መርሐግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ፕሬዝዳንት አበበ ግርማ (ዶ/ር)፣ ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች መካከል 93 በመቶ የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
#AASTU

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 1,067 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ውስጥ 97.6 በመቶዎቹ የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን የተቋሙ ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
#WerabeUniversity

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1,112 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው 5ኛ ዙር ተመራቂዎች፤ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ ናቸው፡፡

@tikvahuniversity
#MizanTepiUniversity

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በአማን እና ቴፒ ካምፓሶቹ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1,290 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ ናቸው፡፡

@tikvahuniversity
#OdaBultumUniversity

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ 1,170 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎቹ 64ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ 1,106 ተማሪዎች ደግሞ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የተመረቁ ናቸው፡፡

የዩኒቨርሲቲው 6ኛ ዙር ተመራቂዎች፤ በመደበኛ፣ በቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በክረምት መርሐግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#WachemoUniversity

ዋቸሞ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 2,115 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

13ኛ ዙር ተመራቂዎቹ፥ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች 86.1 በመቶዎቹ የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሀብታሙ አበበ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
#BuleHoraUniversity

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ትምህርት መስኮች ያሰለጥናቸውን 1,456 ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያ ጊዜ 5 የሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ሰልጣኞችን አስመርቋል።

281 በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም እንዲሁም 1,169 በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ተማሪዎች ሌሎች የዩኒቨርሲቲው 11ኛ ዙር ተመራቂዎች ናቸው።

@tikvahuniversity
#HaramayaUniversity

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 3,370 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በቅድመ እና በድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 4,800 ተማሪዎች አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው 3,024 የመጀመሪያ ዲግሪ፣ 1,211 የሁለተኛ ዲግሪ፣ 38 የህክምና ስፔሻልቲ፣ 46 የዶክትሬት ዲግሪ እና 481 ልዩ ልዩ የመምህራን ስልጠና የወሰዱ ሰልጣኞችን አስመርቋል።

የሎጅስቲክስ ትምህርት ክፍል ተመራቂዋ ቤተልሔም ተስፋዬ 4.0 ነጥብ CGPA በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች።

@tikvahuniversity
2024/10/01 22:15:33
Back to Top
HTML Embed Code: