Telegram Web Link
630 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከጃፓኑ የመኪና አምራች ኩባንያ ሚትሱቢሺ የገንዘብ ስኮላርሺፕ ድጋፍ ማግኘታቸው ተገለፀ፡፡

የገንዘብ ድጋፉ የአቅም ውስንነት ላለባቸው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መደረጉ ተገልጿል፡፡

ኩባንያው ላለፉት ዓመታት ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች ዕርዳታ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ተማሪዎቹ ተመርቀው እስከሚወጡ ባላቸው አፈፃፀም ላይ ኩባንያው እና ዩኒቨርሲቲው ተወያይተዋል፡፡

@tikvahuniversity
የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ 29 ተማሪዎችን አስመርቋል።

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለኤመሪተስ ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ የህይወት ዘመን አገልግሎት ዕውቅና ሰጠ።

ኤመሪተስ ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ እና ኮምፒዩቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ለረጅም ዓመታት በማስተማር፣ በምርምር እና በመሪነት አገልግለዋል።

ኤመሪተስ ፕ/ር ሽብሩ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ምሥረታ ላይ ጉልህ ሚና የተጫወቱ ሲሆን ከበርካታ ተቋማት ሽልማቶችን በተለያዩ ጊዜያት ተቀብለዋል።

የጮቄ ተራራ መልሶ እንዲያገግም ባደረጉት ጥረት የሚታወቁት ኤመሪተስ ፕ/ር ሽብሩ፤ በሚፅፏቸው የሥነ-ፅሁፍ ውጤቶችም ይታወቃሉ።

@tikvahuniversity
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለድኅረ ምረቃ ሬዚደንሲ ፕሮግራም የተመደቡ ተማሪዎች አቀባበል አድርጓል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ አገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና ወስደው ያለፋና በጤና ሚኒስቴር የተመደቡ 58 ተማሪዎችን ተቀብሏል።

ተማሪዎቹ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ኮምፕርሔንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቆይታ ይኖራቸዋል።

@tikvahuniversity
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የግዥ ሠራተኞች 882 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ይዘው መጥፋታቸው ተገለጸ፡፡

ሠራተኞቹ ቅድመ ክፍያውን ይዘው በመጥፋታቸው ጉዳዩ በሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ተይዞ እየተፈለጉ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) በሕ/ተ/ም/ቤት ለመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተናግረዋል፡፡

በ2013 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ስፖንሰር ተደርገው፣ ትምህርታቸውን አጠናቀው በገቡት የውል ጊዜ ወደ ሥራቸው ያልተመለሱ ሠራተኞች፣ በውል ስምምነቱ መሠረት ለዩኒቨርሲቲው መክፈል የነበረባቸው 7.3 ሚሊዮን ብር ተመላሽ አለመደረጉም ተገልጿል፡፡

18 መምህራን ትምህርታቸውን በተቀመጠላቸው ጊዜ አጠናቀው ባለመመለሳቸው የተለያዩ ዕርምጃዎች መወሰዳቸውን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፤ ከመምህራኑ ውስጥ አምስቱ የት እንዳሉ ባለመታወቁ በዋሶቻቸው ላይ ክስ ተመሥርቶ ገንዘቡን እንዲመልሱ በፍርድ ቤት መወሰኑን ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በቋሚ ኮሚቴው እና በፌደራል ዋና ኦዲተር በርካታ የግዥ እና የክፍያ ክፍተቶችና የአሰራር ጥሰቶች መፈፀሙ ተነስቶበታል።

ዩኒቨርሲቲው የተነሱበትን የኦዲት ግኝቶች መሠረት በማድረግ የመንግሥትን ሀብትና ንብረት ማስመለስ እንደሚገባ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሺመቤት ደምሴ (ዶ/ር) ማሳሰባቸውን የሪፖርተር ዘገባ ያሳያል፡፡

የተሰበሰበ ገንዘብ መረጃ እስከ የካቲት 15/2016 ዓ.ም ድረስ እንዲሁም አጠቃላይ የኦዲት ግኝቶች ማስተካከያ በዝርዝር እስከ ግንቦት 30/2016 ዓ.ም ለገንዘብ ሚኒስቴር፣ ለዋና ኦዲተር እና ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት እንዲያቀርብ ቋሚ ኮሚቴው ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

የሪፖርተር ጋዜጣን ዘገባ ለማግኘት፦ www.ethiopianreporter.com/128057/

@tikvahuniversity
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የስምንተኛው ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲዎች የአምሳለ ችሎት ውድድር አሸናፊ ሆኗል።

ላለፉት ሦስት ቀናት ከ12 ዩኒቨርሲቲዎች በመጡ ተሳታፊዎች በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሲካሔደ የነበረው የአምሳለ ችሎት ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን አጊኝቷል።

ተወዳዳሪዎቹ "የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የባህር በር የማግኘት መብትና ዓለም አቀፍ ሕግ" በሚለው ጭብጥ ላይ ተከራክረዋል፡፡

የፍጻሜው ውድድር በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ መካከል የተደረገ ሲሆን የፋጻሜ ክርክሩን ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አሸንፏል።

ተማሪ ምህረት ወንድሙ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአጠቃላይ ውድድሩ ምርጥ ተናጋሪ በመሆን የሦስት ዋንጫዎች እና የሰርትፊኬት ተሸላሚ ሆናለች።

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለውድድሩ ከተዘጋጁት አምስት ዋንጫዎች አራቱን በማሸነፍ ውድድሩን በበላይነት በማጠናቀቅ የወርቅ ዋንጫ ተረክቧል።

ውድድሩ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ እና በፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት ትብብር መዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity
#MondayMotivation

ሜሮን አብርሃ በርኸ ትባላለች፡፡
በዘመናዊ የፋሽን ምርት የሚታወቀው 'ቢራቢሮ አልባሳት' የዲዛይን ኃላፊ ናት፡፡ ቢራቢሮ አልባሳት በአካባቢ ላይ ጉዳት የሌላቸው የሀገር ውስጥ ምርቶችን በመጠቀም በሚያመርታቸው ዘመነኛ አልባሳቱ ይታወቃል፡፡

ሜሮን አብርሃ ብሪቲሽ ካውንስል ኢትዮጵያ ለTechStitched የፋሽን ሬዚደንሲ ፕሮግራም ከመረጣቸው አምስት ዲዛይነሮች አንዷ ሆናለች፡፡ ፕሮግራሙ ከአምስት የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ዲዛይነሮች የሥራ እና የባህል ልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት ነው፡፡

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሰሞኑን "የተቋሙ የግዥ ሠራተኞች 882 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ይዘው እንደጠፉ" በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የተዘገበው ትክክል አለመሆኑን ገለፀ።

የተቋሙ ሠራተኞች ከ2004 እስከ 2007 ዓ.ም ለተፈፀሙ ግዢዎች የተፈፀመን የብር 882,000 ክፍያ አስመልክቶ የተሠሩ ዘገባዎች ላይ ዩኒቨርሲቲው መግለጫ አውጥቷል።

"ክፍያውን ያከናወኑ የተቋሙ ሠራተኞች ለፈፀሙት ክፍያ በሕጉ መሠረት የማወራረድ ሥራ ማከናወን ሲገባቸው ይህን ሳያደርጉ ከተቋሙ የለቀቁ መሆናቸውን" መግለጫው አስታውሷል።

በመሆኑም "ጉዳዩ በ2008 ዓ.ም በተደረገ የኦዲት ምርመራ በኦዲት ግኝትነት የተያዘ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲው ተገቢውን ዕርምጃ ለመውሰድ በጥረት ላይ እንደሚገኝ" የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) በሕ/ተ/ም/ቤት ለመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አብራርተዋል፡፡

"ይሁን እንጂ የፕሬዝዳንቱን ማብራሪያ የተለያዩ አካላት በማዛባት እና ከአውድ ውጭ በመተርጎም ለተለያየ የዜና ፍጆታ ሲጠቀሙት አስተውለናል" ብሏል መግለጫው፡፡

ክስተቱ ዛሬ ላይ የተፈፀመ ጉዳይ እንዳልሆነና በስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተይዞ ክትትል እየተደረገበት የሚገኝ ጉዳይ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

(የዩኒቨርሲቲው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት እና በቴክኒካል አሲስታንት የሥራ መደቦች ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

➤ የሥራ መደብ፦ በተለያዩ የሙያ መስኮች
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 22
➤ የትምህርት ደረጃ፦ ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ
➤ የሥራ ቦታ፦ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ
➤ የማመልከቻ ጊዜ፦ ይህ ማስታዎቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመጋቢት 21/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት

የምዝገባ ቦታ፦
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የብቃትና የሰው ሃብት አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ ቁ. 4

ተመዝጋቢዎች ለምዝገባ ስትሔዱ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ የተሟላ የትምህርት ማስረጃ ከማይመለስ ኮፒ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

የፈተና ቀን ወደፊት በማስታወቂያ የሚገለፅ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ጠቁሟል።

@tikvahuniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከመጪው ሰኞ መጋቢት 30/2016 ዓ.ም ጀምሮ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የተቋሙ ሙስሊም ተማሪዎች የኢድ አል ፈጥር በዓል ሚያዚያ 1 ወይም 2/2016 ዓ.ም ሊሆን እንደሚችል በመግለፅ ቅሬታቸውን አድርሰውናል፡፡

በጉዳዩ ላይ ዩኒቨርሲቲውን ጠይቀናል፡፡ "በዓሉ በሚከበርበት ዕለት (ሚያዚያ 1 ወይም 2/2016 ዓ.ም) ትምህርት የሌለ በመሆኑ፣ ፈተናም #የማይሰጥ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ "የአዲስ አበባ ከተማን ሥር የሰደደ የንፁህ ውሃ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ ፍኖተ ካርታ" የተሰኘ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡

በዓለም አቀፉ Research Triangle ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የውሃ ሃብት ኢንጂነር የሆኑት ፍቃዱ ሞረዳ (ዶ/ር) እንዲሁም በ Tampa Bay Water አመራር የሆኑት ጥሩሰው አሰፋ (ዶ/ር) በመድረኩ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡

ውይይቱ የሚካሔደው፦ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም ከሰዓት 8፡30

ውይይቱ የሚካሔድበት ቦታ፦ በአ.አ.ዩ. በተፈጥሮ እና ኮምፒዩቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ፣ አዲሱ ዲጂታል ቤ-መፃሕፍት፣ 5ኛ ወለል

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከል የ TOEFL iBT ፈተና ቅዳሜ መጋቢት 28/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

በኦንላይን የሚሰጠውን ፈተና በማዕከሉ ለመውሰድ ምዝገባ ያድርጉ 👇
https://www.ets.org/toefl/test-takers/ibt/register/how-to-register.html

ክፍያ፦ $235
የክፍያ መንገድ፦ በክሬዲት ካርድ
ለተጨማሪ መረጃ፦ +251-912685860
[email protected]

@tikvahuniversity
2024/09/30 23:36:00
Back to Top
HTML Embed Code: