Telegram Web Link
በትግራይ ክልል በትምህርት ገበታ ላይ ያለው የተማሪ መጠን 41 በመቶ ብቻ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በክልሉ በትምህርት ገበታ ላይ መሆን ከሚገባቸው 2.4 ሚሊዮን ተማሪዎች 994,369 ተማሪዎች (41.1 በመቶ) ብቻ በትምህርት ላይ እንደሚገኙ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመቐለ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡

ተማሪዎቹ በትምህርት ገበታቸው ላይ ያልተገኙት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት እንደሆነ ጽ/ቤቱ አስረድቷል፡፡

ጽ/ቤቱ በ22 ወረዳዎች በሚገኙ 794 ትምህርት ቤቶች ላይ በተደረገ ክትትል 112 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ፥ 595 በከፊል እንደተጎዱ ጠቁሟል፡፡

794 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ምንም ዓይነት ጉዳት ያልደረሰባቸው 47 ትምህርት ቤቶች ብቻ እንደሆኑ የጽ/ቤቱ ኃላፊ ፀሀዬ አንባዬ ለሸገር ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በክልሉ መዲና መቐለ ባደረገው ክትትልም በ24 ትምህርት ቤቶች ተፈናቃዮች መኖራቸውን አረጋግጫለው ብሏል፡፡ #SheferFM

@tikvahuniversity
#ይሳተፉ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ "የክብር ዶክትሬት ሽልማት እና የዶክትሬት ትምህርት በኢትዮጵያ" በሚል ጭብጥ ላይ የገለጻና የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡

መድረኩ በፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ አቅራቢነት እንዲሁም በፕሮፌሰር ሀብታሙ ወንድሙ አወያይነት ይካሔዳል።

መርሐግብሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እሸቱ ጮሌ መታሰቢያ አዳራሽ ነገ መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይካሔዳል፡፡ ውይይቱን በዙም መሳተፍም ይቻላል፡፡

Join Zoom Meeting:
https://us06web.zoom.us/j/83253374239...
Meeting ID: 832 5337 4239
Passcode: 921303

@tikvahuniversity
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ የሁለት ሚሊዮን ብር የሎተሪ ዕድለኛ ሆነዋል፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት አበበ ፍሬው በቆረጡት የዝሆን ሎተሪ የሁለት ሚሊዮን ብር ዕድለኛ መሆናቸውን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ገልጿል፡፡

መምህር አበበ ፍሬው በደረሳቸው ገንዘብ ከማስተማር ሥራቸው ጎን ለጎን የሚሠሩትን የእንጨት እና የብየዳ ሥራ ለማስፋፉት እንደሚጠቀሙበት ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአፈፃፀም ተጠያቂነት ስርዓት ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ተቋማት በፋይናንስ አጠቃቀማቸው እንጂ በአፈፃፀም ተጠያቂ የሚሆኑበት ስርዓት አልነበረም፡፡

ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተቋማት በአፈፃፀማቸው ተጠያቂ የሚሆኑበትን አሰራር መተግበር እንደሚጀምር በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

በዚህም በተጠያቂነት የአሰራር ስርዓት መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቁልፍ ውጤት አመላካቾች (KPI) ላይ ውል በማድረግ ሥራቸውን እንደሚያከናውኑ ገልፀዋል።

የአፈፃፀም ተጠያቂነት ስርዓቱ ተመዝነው የተሻለ አፈጻጻም ያስመዘገቡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዕውቅና እንዲያገኙ እንዲሁም ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው ደግሞ የማስተካከያ ዕርምጃዎች የሚወስዱበት አግባብ የሚፈጠርበት መሆኑንም አስረድተዋል። #ENA

@tikvahuniversity
🔔 ያመልክቱ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የ Education USA Scholars Program (ESP) 2024 ማመልከቻ ክፍት መሆኑን አሳውቋል።

ፕሮግራሙ በትምህርታቸው ጠንካራ የሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኙ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች እንዲያመለክቱ የሚረዳ የአራት ሳምንታት የሥልጠና መርሐግብር ነው።

ከአመልካቾች ውስጥ 20 የመጨረሻ ዕጩዎች የሚለዩ ሲሆን ከነሱ መካከል 15 ከፍተኛ ብቃት ያላቸው በኢኮኖሚ የተቸገሩ ተማሪዎች የፈተና ወጪ እና የቪዛ ክፍያ በሚሸፍነው የ Opportunity Program Fund ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ስኬታማ ዕጩዎች ወደ አሜሪካ የደርሶ መልስ ትኬት ያገኛሉ። ቀሪዎቹ አምስት ተማሪዎች በስልጠና ፕሮግራሙ ላይ በነጻ የሚሳተፉ ሲሆን የዝግጅት ወጪያቸውን ራሳቸው ይሸፍናሉ።

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ ሚያዚያ 2/2016 ዓ.ም ከሰዓት 11:00

ለማመልከት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፦
➧ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩና ትምህርታቸውንም እዚሁ የተከታተሉ
➧ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ/ች ኢትዮጵያዊ ተማሪ
➧ በዚህ የትምህርት ዓመት መጨረሻ 11ኛ ክፍልን ያጠናቀቁ
➧ ለአራት ሳምንታት የሚሰጠውን ESP መርሐግብር ሙሉውን መሳተፍ የሚችሉ

ለማመልከት የሚያስፈልጉ፦

➧ የሁለተኛ ደረጃ ትራንስክሪፕት (የ9፣ 10 እና 11ኛ ክፍል ውጤት)
➧ ከትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ
➧ የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸውና ለ Opportunity Fund Program የሚያመለክቱ ከትምህርት ቤት ወይም ከቀበሌ የቤተሰብን ዝቅተኛ የኢኮኖሚያ ሁኔታ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ ያስፈልጋል።

ለማመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ 👇
https://sites.google.com/amspaceseth.net/educationusa-esp2024

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ፡፡

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የብሪቲሽ ካውንስል IELTS አጋርነት ፕሮግራም አካል ሆኗል፡፡

በዚህም ዩኒቨርሲቲ IELTS ፈተና መስጠት የሚችል ሲሆን የመጀመሪያ ዙር የ IELTS ፈተና ሚያዝያ 5/2016 ዓ.ም በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡ ፈተናውን ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ በመከናወን ላይ ይገኛል።

በተከታዩ ሊንክ ምዝገባ ያድርጉ፦ https://bit.ly/3nPlT7V

ለበለጠ መረጃ፦
0915409297 / 0915196750 / 0920059550

ክፍያና ሌሎች መራጃዎች ለማግኘት 👇
https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts/dates-fees-locations

@tikvahuniversity
"ዲግሪ ለመያዝ ስምንት ዓመት መቆየት ፍትሃዊ አይደለም! በዚህ ዓመት ልንመረቅ ይገባል!" የሚሉ ጥያቄዎችን የያዙ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ተሰምቷል።

"በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ የሚሰጠው ትምህርት የፌደራል መንግሥት ባሰቀመጠው መመሪያ መሰረት እንዲከናወን" የዩኒቨርሲቲውን አስተዳደር በተደጋጋሚ መጠየቃቸውን ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ተማሪዎቹ በጥር 2017 ዓ.ም ሊመረቁ እንደሚችሉ በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እንደተነገራቸው ተሰምቷል፡፡

በክልሉ ከተማ በተለምዶ የተባበሩት የሚባለው አካባቢ ጥያቄዎቻቸውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ እያቀረቡ የነበሩት ተማሪዎቹ በጸጥታ ኃይሎች መበተናቸው ተነግሯል።

ፖሊስ አንዲት ሴትን (ተማሪ) ገፍትሮ አስፓልት ላይ ሲጥላት የሚያሳይ ቪዲዮ በማኅበራዊ ትስስር ገፆች ሲዘዋወር ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተመልክቷል፡፡ በተማሪዎቹ ላይ ጉዳት መድረስ አለመድረሱን ማረጋገጥ አልቻልንም፡፡

በጉዳዩ ላይ መቐለ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ትምህርት ሚኒስቴር የሚሉትን ወደፊት የምናደርሳችሁ ይሆናል፡፡

@tikvahuniversity
#ተጨማሪ

ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፖሊስ ድብደባ ተፈፀመባቸው። 10 ተማሪዎች መታሰራቸው ተገልጿል።

ተማሪዎቹ የተራዘመ የመመረቂያ ግዜን በመቃወም ሰልፍ የወጡ ሲሆን ፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት እንደፈፀሙባቸው ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ ዛሬ ረፋድ 4:00 ሰዓት ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ አሪድ ግቢ ተነስተው ያሏቸውን ቅሬታዎች ለማሰማት ወደ መቐለ ከተማ ጎዳናዎች ሰላማዊ ሰልፍ አካሒደዋል።

ተማሪዎቹ በተለያዩ ምክንያቶች ለዓመታት ትምህርታቸው ሲስተጓጎል ቆይቶ ዘንድሮ ለመመረቅ እየተጠባበቁ የነበረ ቢሆንም፤ ዩኒቨርሲቲው ሌላ ተጨማሪ ዓመት መማር እንደሚጠበቅባቸው መግለፁን ተከትሎ ተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ መገደዳቸውን ጠቁመዋል።

ፖሊስ ጥይት በመተኮስ፣ በድብደባ እና በአፈሳ
ሰልፉን በኃይል መበተኑን ተማሪዎቹ የገለፁ ሲሆን በተፈፀመባቸው ድብደባ አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች መኖራቸው ታውቋል። 10 ተማሪዎችም መታሰራቸው ተገልጿል። #ዶቼቬለ

@tikvahuniversity
የትግራይ መምህራን ማኅበር የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የመምህራንን የ2015 ዓ.ም የአምስት ወራት ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፍል ጥሪ አቀረበ፡፡

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ውዝፍ ክፍያውን ለመክፈል ቀደም ሲል ተስማምቶ እንደነበር የማኅበሩ ም/ፕሬዝዳንት ንግስቲ ጋረደ ለክልሉ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ አስተዳደሩ ለመክፈል ቃል የገባውን የአምስት ወራት ደመወዝ አለመክፈሉን ም/ፕሬዝዳንቷ ገልፀዋል።

በክልሉ የሚገኙ መምህራንን የ17 ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም ሲሉ ሰልፍ መውጣታቸው ይታወሳል።

@tikvahuniversity
የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥ

"ግልጽ የሆነ መመርያ እስከሚወጣ ድረስ የክብር ዶክትሬት እንዳይሰጥ ተከልክሏል።"
- የትምህርት ሚኒስትሩ

የተበታተነ አሠራርን ለመቅረፍ ግልጽ የሆነ መመርያ እስኪወጣ ድረስ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት የሚባል ነገር መስጠት እንዲያቆሙ እንደተነገራቸው የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለፁ፡፡

ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት ‹‹የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ "የዶክትሬት ዲግሪና የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሽልማት በኢትዮጵያ" በሚል ጭብት ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተካሔደ ምሁራዊ ውይይት ወቅት ነው።

በኢትዮጵያ የክብር ዶክትሬት ሲሰጥ በተበታተነ ሁኔታ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች መስጠት እንዲያቆሙ ውሳኔ መተላለፉን ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥን በተመለከተ መመርያ እያዘጋጀ መሆኑንና መመርያውንም በዚህ ዓመት አጠናቆ ለመጨረስ ሒደት ላይ እንደሆነ ሚኒስትሩ አክለዋል፡፡

በኢትዮጵያ እስካሁን 79 ሰዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንደተሰጣቸው አስረድተው ከነዚህም 68 በመቶ የሚሆነው ለክልል ሰዎች የተሰጠ እንደሆነ ገልጸዋል።

በመድረኩ የመነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት ፕ/ር ማስረሻ ፈጠነ በበኩላቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሲሰጥ አካዳሚያዊ ያልሆነ ዕውቅናን በመንተራስ እንደሆነና ተሸላሚዎችም ካላቸው ክህሎት፣ ስብዕና እንዲሁም ያበረከቱት አስተዋጽኦ ጋር በተያያዘ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥን የተመለከተ መመርያ እንዳላቸው አንስተዋል።

በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በርካታ ሰዎችን እያሳሰበ የመጣው ጉዳይ ዩኒቨርሲቲዎች የራሳቸው ሰው የሚሉትን ብቻ በመምረጥ የክብር ዶክትሬት እየሰጡ መሆኑ ነው ብለዋል፡፡

የክብር ዶክትሬት ዲግሪን ከዩኒቨርሲቲዎች የሚያገኙ ሰዎች ጭምር እንደመጠሪያ እንደሚጠቀሙበትና ይኼም በጣም የተሳሳተ ነገር እንደሆነ ገልጸው፣ በርካታ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችም ይኼንን ድርጊት እንደሚፈጽሙ አስታውሰዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ የሰጧቸው ሰዎች ያልተገባ ድርጊት ከፈፀሙ፣ የክብር ዶክትሬት ዲግሪውን መንጠቅ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡ #ሪፖርተር

@tikvahuniversity
📍 Dambi Dollo

ትላንት በደረሰ የመኪና አደጋ ሦስት የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች ህይወት አልፏል፡፡

በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ 'አይራ ቅርንጫፍ' የዕረፍት ቀናት (Weekend) ትምህርት አስተምረው ሲመለሱ የነበሩ መምህራን ባጋጠማቸው የመኪና አደጋ ሁለት መምህራን እና አንድ አሽከርካሪ ህይወታቸው ሲያልፍ፣ በ12 ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

በአደጋው ህይወታቸው ላለፈ የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ዛሬ ጠዋት የሽኝት ፕሮግራም ተደርጓል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሠራተኞቹ ህልፈት የተሰማውን ሐዘን በመግለፅ፤ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል።

@tikvahuniversity
#MoE

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ሽግግር የሚያሳልጡ ፍኖተ ካርታ እና መመሪያ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

የዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ መሆን ተቋማቱ በአስተዳደራዊ፣ አካዳሚያዊ እንዲሁም በሰው ሃብትና ፋይናንስ አስተዳደር ጉዳዮች ነፃነትን ከተጠያቂነት ጋር የሚያገኙበት የአሰራር ስርዓት እንደሆነ በሚኒስቴሩ የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ሽግግር ለማሳለጥ የሚያስችሉ የፍኖተ ካርታ እና የመመሪያ ዝግጅት በቅርቡ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንደሚገቡ ጠቁመዋል።

ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ እየተሠራ ሲሆን ተቋማቱ ከአደረጃጀት ጀምሮ ለሽግግሩ የሚያግዟቸውን ተግባራት እያከናወኑ እንደሆነ ኃላፊው አስረድተዋል።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ራስ ገዝ ለመሆን የሰው ኃይል፣ ሃብት የማመንጨት አቅም፣ የመሰረተ ልማትና የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓታቸው እንዲሁም ዓለም አቀፍ ትስስራቸው እንደሚታይ ገልፀዋል። #ENA

@tikvahuniversity
2024/11/05 19:12:14
Back to Top
HTML Embed Code: